View in English alphabet 
 | Saturday, December 21, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
አማርኛ




ላክ   ተወው
ነገረ ቅዱሳን

In the Name of the Father, and of the Son, and of the Holy Spirit, One God, Amen

በአማርኛ የተዘጋጀውን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ


Feast of the Nativity of Our Lady,
Holy Virgin Mary

Yom fissiha kone be’inte lideta leMariam (There was great joy in the birth of Mary!)

“Her foundations are upon the holy hills.” (Psalm [86]87:1)

When we look back 2019 years ago, we find a marvelous, history changing event that occurred. This was the birth of our Lady, Holy Virgin Mary. It is also Her that God’s prophet David, known as a man after God’s own heart, refers to by saying, “Her foundations are upon the holy hills.” (Psalm [86]87:1). Those described as the holy hills are our Lady’s parents and ancestors such as Noah and Abraham for all these are saints. Joachim and Anne are among the holy hills and they are also the father and mother of our Lady. They used to be sad since they were barren although they lived in a faithfully holy marriage. They made a vow at an old age so that God would give them a child. The vow was, “If we have a son, we will not say let him go up and down, plough, dig, trade, make profit and help us but rather be a guard and servant of the house of God; if we have a daughter, we will not say let her gather wood, bake bread, fetch water, grind   ተጨማሪ ያንብቡ



ስብከተ ወንጌል

“ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃህ እምንዋም”

እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሳ መዝ( ፸፯÷፷፭)

በቀሲስ አድማሴ መኮንን

 

በትራክት መልክ የተዘጋጀውን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ።

ታላቁ አባት ቅዱስ ኤፍሬም ሃይማኖተ አበው በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ ፵፯ ክፍል ፩ ቁጥር ፮ ላይ ልዩ በሚሆን ድንቅ በሚያሰኝ መለወጥ ይስማማው በነበረ ሥጋ በተወለደው ልደት ወደ አልተለመደው ነገር /ወደ ሞት/  ወደ መስቀል ደረሰ ( ኢሣ ፱÷፮ _ ፯)::  እኛን የሚመስል ሥጋን ገንዘብ አደረገ ይኸውም ከሁሉ ጋራ አንድ ነው ከባህርያችን የተገኘው አንድ አካል አንድ ባህርይ የሆነ እርሱ ሕማም ሞት የሌለበት ሲሆን በሥጋ ባህርይ ኃጥያት ሳይኖርበት ታመመ ሞተ እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጥያት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጥአት አደረግነው(፪ኛቆሮ ፭÷፳፩)“ በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ ኃሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሣለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማትን እንደሚገባ ነገር አልቆጠረውም ነገር ግን የባርያውን መለክ ይዞ በሰው ምሣሌ ሆኖ ራሱን ዝቅ አደረገ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ “(ፊልጵ፪÷፭ _ ፱)“

  ተጨማሪ ያንብቡ


ስብከተ ወንጌል

«አንች የጽዮን ልጅ አትፍሪ፤ እነሆ ንጉሥሽ በእህያ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ይመጣል» ተብሎ እንደተጻፈ ኢየሱስ የአህያ ውርንጫ አግኝቶ በእርሱ ተቀመጠ ዮሐ.12፥15፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመምጣቱ አስቀድሞ 1400 ዓመታት በፊት እግዚአብሔር በአብርሃም የእምነት ቃል ኪዳን ሕዝቡ ያደረጋቸውን እስራኤላውያንን በጽኑ  ክንድ ከባርነት ቀንበር አውጠቶ ቀን በደመና ሌሊት በብርሃን አምድ እየመራ በመገናኛዋ ድንኳን ውስጥ አድሮ እርሱ ንጉሣቸው ሆኖ እነርሱ ደግሞ ህዝቡ ሆነው በምድረ በዳ መራቸው፤ ወደ ተስፋይቱ ምድር ከነዓንም አገባቸው፡፡ እስራኤል ግን ምድራዊ ንጉሥ በመፈለግ ንጉሣቸው እግዚአብሔርን በመተዋቸው እግዚአብሔርን በደሉ፤ በምድር ላይ ያለች የመንግሥቱ ማሳያ ሊሆኑ የመረጣቸው ሕዝቡ ምድራዊ ንጉሥ ፈልገዋልና፡፡ መልከ መልካምና ያማረ የሆነው ሳኦል እስራኤል የመረጡት ምድራዊ ንጉሥ ውጫዊ ክብር ብቻ ያለው መሆኑን አስመስከረ፡፡ እግዚአብሔር ግን ከዚህ ዓለም ያልሆነች በቁሳዊው ኅብር ያላጌጠች፣ የትህትናና የፍቅር የምሥጋና የሆነች መንግሥቱን ሊያመለክት ሲወድ ከወንድሞቹ ሁሉ ያነሰውንና በገና ደርደሪውን የእሴይን ልጅ ዳዊትን መረጠ፡፡ የዳዊት መንግሥት ብታልፍም « ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ» ያለውን ቃልኪዳን ግን አላጠፋም ፡፡ ስለዚህም በአምላክነቱ ለዘላለም የነገሥታት ንጉሥ የሆነ ወልድ ከዳዊት ዘር ሰው ሲሆን የዳዊት ተስፋ ተፈጸመ፤ በመለኮታዊ ስልጣኑ በእግዚአብሔር እሪና ያለው ወልደ እግዚአብሔር የዳዊት ልጅ ሆኗልና፡፡

ሉውን ማንበብ ይህን ይ
  


ትምህርተ ሃይማኖት

ደብረ ዘይት
/ማቴ. ፳፬፥፩-ፍጻሜ/

በትራክት መልክ የተዘጋጀውን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ

በሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ከፈለኝ ወልደጊዮርጊስ

 

ደብረ ዘይት ማለት ቃሉ “ደብር” ሲል ተራራ ሲሆን “ዘይት” ሲል የወይራ ዛፍን ያመለከታል። ባጠቃላይ ደብረ ዘይት የወይራ ዛፍ (የዘይት ዛፍ) የበዛበት ተራራ ማለት ነው። ቦታው በቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ከጎለጎታ (ቀራንዮ) ተራራ በስተምስራቅ በግምት ፪ ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ታላቅ ተራራ ነው። በሁለቱ ተራሮች መካከል ጌቴሴማኒ የሚባለው ለምለም ስፍራ ይኸውም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የመቃብር ስፍራ ይገኛል።

የደብረ ዘይት ተራራ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ የሚያድርበት፣ የሚያስተምርበት፣ ውሎ የሚያርፍበት ሥፍራ ነው። ሉቃ ፳፩፥ ፴፯፣ ሉቃ ፳፪፥ ፴፱፣ ዮሐ ፰፥ ፩ ከዚሁ ተራራ ላይ ነው ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያረገው። ኋላም በዳግም ምጽአት እዚሁ ተራራ ላይ ነው ለፍርድ የሚመጣው። /ሐዋ ፩፥፲፫/።
  ተጨማሪ ያንብቡ


ስብከተ ወንጌል

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

“አላ ሰብእ አልብየ” ሰው የለኝም (ዮሐ 5፥7)


በሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ከፈለኝ ወልደጊዮርጊስ


ቤተ ሳይዳ ወይም ቤተሰዳ ማለት የምህረት ቤት ማለት ነው አምስትም መመላለሻ ያላት ማለትም አምስቱ አዕማደ ምሥጢር የሚገኝባት በነዚህ ሁሉ ድህነትን የምትሰጥ ናትና ቤተሳይዳ የምህረት ቤት ናት። አምስቱ አዕማድም የተባሉትም 1) ምስጢረ ሥላሴ 2) ምስጢረ ሥጋዌ 3) ምስጢረ ጥምቀት 4) ምስጢረ ቁርባን እና 5) ምስጢረ ትንሳኤ ሙታን የሚባሉ ናቸው። እንግዲህ ወደዚች የምህረት ቦታ፣ የፀበል ቦታ በመጀመሪያ ሄዶ የተገኘ፣ ገብቶ የተጠመቀ፣ ካለበት ሕመም ሁሉ ፍጹም ጤነኛ ይሆናል። ይህም ሰው 38ዓመት ሙሉ በደዌ ዳኛ፣ በአልጋ ቁራኛ ተይዞ ወደ ጸበሏ የሚወስደው፣ በርትቶ ጸንቶ ጠብቆ በሰው ፊት የሚያስገባው ሰው አጥቶ ለብዙ ዘመናት በተስፋ መቁረጥ ላይ ይገኝ የነበረ ነበር።

 

  ተጨማሪ ያንብቡ


Page 10 of 41First   Previous   5  6  7  8  9  [10]  11  12  13  14  Next   Last   

 የ10 ዓመት የስብከተ ወንጌል ማስፋፋፊያ ፕሮጀክት Minimize

ስለ ፕሮጀክቱ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እና ለመርዳት ይህንን ይጫኑ።


  
 ገዳማትን ይርዱ Minimize

 

Help Monastries


  
 ሶሻል ኔትወርኪንግ

Share |

  
 ግጻዌ


  
 የተላለፉ የቴሌቪዥን እና ሬዲዮ መርሃ ግብር ለመከታተል Minimize


  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement