View in English alphabet 
 | Thursday, October 3, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
  

ነገረ ድኅነት

መቅድም 

የመዳን ትምህርት የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ማዕከል ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ የሌሎች መጻሕፍት ዋና ዓላማ ሰው የሚድንበትን መንገድ ማሳየት ነው፡፡ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስም የሞተው የሰወን ልጅ ለማዳን ነው፡፡

ነገረ ድኀነትይህ ትምህርት የተዘጋጀው ለግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች ሊረዳ በሚችል መንገድ የአበውን ትምህርት መሠረት በማድረግ ነው፡፡ የሚያስተምረው መምህር፡ 

· ምሥጢረሥጋዌን ምሥጢረ ሥላሴን አስቀድሞ ቢማርና በሚገባ ቢያውቅ

· ሃይማኖተ አበውን ቢያነብና የአበውን ይትበሃልና ትርጉም ለቅሞ ቢይዝ

· የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክን ቢያነብና ማስታወሻ ቢይዝ ትምህርቱን በሚገባ ለማስተማር ይረዳዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ነገረ ድኀነት መሠረታዊውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት/አምስቱ አዕማደ ምሥጢር፤ ሰባቱን ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን፤ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ/ ከተማሩ በኋላ ሊሰጥ የሚገባው መሆኑን ልንጠቁም እንወዳለን፡፡

 «ነገር» የሚለው ቃል በቤተ ክርስቲያን ትምህርት የአንድን ትምህርት መስክ መግለጫ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ለምሳሌ «ነገር ማርያም» ሲል ስለ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለሰው ልጅ በእግዚአብሔር ፈቃድ የገለጸውን ሁሉ የምንማርበት ትምህርት ማለት ነው፡፡ በዚህ ይዘቱ /LOGY/ የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል ይመስላል፡፡ 

ድኅነት

በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ድኀነት ማለት ከኀጢአት ተፈውሶ የእግዚአብሔር መንግሥት ወራሽ መሆንማለት ነው፡፡

«ሕዝቡንከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ» ማቴ. 1፤21፡፡ የነገረ ድኀነት ትምህርት ባንድ ወገንአባታችን አዳም ከወደቀበት የኀጢአት ማጥ ወጥቶ እንዴት ዳነ በሌላው ወገን ደግሞ እኛ ልጆቹስ እንዴት እንድናለን የሚሉትን ነጥቦች የምናይበት ትምህርት ነው፡፡

 የነገረ ድኀነት መነሻው የአዳም ውድቀት ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ኃጢአትን የሠራ፤ ይድን ዘንድም ቃል ኪዳን የተገባለት የመጀመሪያው ሰው እርሱ ነውና፡፡ በመሆኑም ትምህርታችንን የምንጀምረው ከዚሁ ነው፡፡

 የመናፍቃን የክህደት መነሻ ትክክለኛውን የመዳን መንገድ በመሳትና በማሳት በመሆኑ የቀድሞ ዘመን ጀምሮ አበው ምሥጢረ ሥጋዌን አምልተውና አስፍተው በማስተማርና በመጻፍ ነገረ ድኀነትን የትምህርታቸው መነሻና መድረሻ አድርገውታል፡፡

 


Written By: host
Date Posted: 2/1/2008
Number of Views: 12076

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement