View in English alphabet 
 | Friday, March 29, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
  

ለአዳም መሳሳት ተጠያቂው ማነው?

የዕፀበለስ መኖር ነውን?

ዕፀ በለስ በራስዋ ማድረግ የምትችል ፍጥረት አይደለችም፡፡ ወደ አዳም ተጉዛ ብላኝ አላለችም፡፡ ደግሞም ዕፀ በለስ በአዳም ላይ ሞት ያመጣችው መርዛማ በመሆንዋ አይደለም፡፡ ዕፀ በለስ ከላይ እንዳየነው የምልክት ዛፍ ናት፡፡ ...

1.              የዕፀበለስ መኖር ነውን?

ዕፀ በለስ በራስዋ ማድረግ የምትችል ፍጥረት አይደለችም፡፡ ወደ አዳም ተጉዛ ብላኝ አላለችም፡፡ ደግሞም ዕፀ በለስ በአዳም ላይ ሞት ያመጣችው መርዛማ በመሆንዋ አይደለም፡፡ ዕፀ በለስ ከላይ እንዳየነው የምልክት ዛፍ ናት፡፡

መታዘዝና አለመታዘዝን የምትገልጥ፡፡ አዳም ዕፀ በለስን ከበላህ ሞት ይመጣብሃል ካልበላህ በሕይወት ትኖራለህ ተብሏልና፡፡ ከሕይወትና ሞት እንዲመርጥ ምርጫ ተሰጥቶታል፡፡ አዳም ሞትን መርጦ ዕፀ በለስን ቀጠፈ፡፡ «ልሙት» ብሎ ወሰነ እንጂ ማንም አልወሰነበትም፡፡ እናም ዕፀ በለስተጠያቂ አይደለችም፡፡

2.             ዲያብሎስ  ነውን?

«አንተየንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፤ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ? አንተም በልብህ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ፡፡ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ድንኳኖች በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፡፡ ከደመናዎችም ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፡፡ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ» ኢሳ. 14፤12-14፡፡

«በሰማይምሰልፍ ሆነ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉት፡፡ ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፡፡ አልቻላቸውም፡፡ ከዚያም ወዲያ በሰማይ ሥፍራ አልተገኘላቸውም፡፡ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱ የቀደመው እባብ ወደ ምድር ተጣለ፡፡» ራእይ 12፤7-1ዐ፡፡ 

ሰይጣን ራሱን ከክብር አዋርዶ ለሰይጣንነት የበቃ ነው፡፡ እንጨትና እንጨት ተፋጭቶ እሳት እንዲያመነጭ ሰይጣንም ትዕቢትንና ሐሰትን በራሱ አፍልቆራሱን አጠፋ፡፡ ዲያብሎስ እርሱ ያጣውን ክብር እኛም እንድናጣ ፈለገ፡፡ ስለሆነም ወደ ሔዋን መጣ፡፡ ክፉ ምክርንም መከራት፡፡ እግዚአብሔርን ውሸተኛ አድርጐ አቀረበላት፡፡ ሔዋንም ዕፀ በለስን ቀጠፈችና በላች፡፡

ታዲያ ዋናው ተጠያቂው ዲያብሎስ ነው? አይደለም፡፡ዲያብሎስ ሔዋንን ክፉ ምክር መከራት፡፡ ዕፀ በለስን ብትበሉ አምላክ ትሆናላችሁ ብሉ፡፡ ሐዋን ዕፀ በለስን በተመለከተ ይህ ሁለተኛ ትምህርት ነው፡፡ 

የመጀመሪያው ዕፀ በለስን ብትuሉ ትሞታላችሁ( እግዚአብሔር ሁለተኛ ዕፀ በለስንብትuሉ አምላክትሆናላችሁ( ሰይጣን፡፡

እግዚአብሔር የታመነ አምላክ መሆኑን የሰው ልጅ ፈትኖ ለማወቅ ችሏል፡፡ ለሰባት ዓመታት ሞትን ሳያይ በመኖሩ፡፡ ነገር ግን የዲያብሎስን ቃል ሰሙ እርሱ እግዚአብሔርን ውሸተኛ አድርጐ ሲያቀርብላቸው ተቀበሉት፡፡ አዳምና ሔዋን ወስነው ፈቅደው ሕገ እግዚአብሔርን ጥሰው በዲያብሎስ ምክር ተመሩ፡፡ ዲያብሎስ እጃቸውን ይዞ አላስቆረጣቸውም፡፡ ቆርጦም አላጐረሳቸውም፡፡ መከራቸው እንጂ አመዛዝኖ መወሰን የአዳምና የሔዋን ድርሻ ነው፡፡ ዲያብሎስ ምክንያተ ስህተት እንጂ ስህተት እንድናደርግ የማስገደድ መብት የለውም፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ በመልእክቱ «ለእግዚአብሔርተገዙ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፡፡ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል፡፡ » ያዕ. 4፤8፡፡ እንዳለን ዲያብሎስን የመቃወም መብቱም ሥልጣኑም ነበራቸው፡፡ እነርሱ ግን መብታቸውንና ሥልጣናቸውን አሳልፈው ሰጡት፡፡ በመሆኑም ለአዳምና ለሔዋን መሳሳት ዲያብሎስ ተጠያቂ አይደለም፡፡ ዋና ተጠያቂው ራሱ የሰው ልጅ ነው፡፡ ለዚህም ነው ሔዋን በእባብ ያመካኘችውን ምክንያት እግዚአብሔርያልተቀበላት፡፡


Written By: host
Date Posted: 2/1/2008
Number of Views: 10091

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement