· ‹‹ኃጢአትን በመቃወም ለእግዚአብሔር ያለህን ፍቅር አሳይ›› ብ.ወ.አ.ሺኖዳ 3ኛ
· ‹‹ከመውደቅህ በፊት ዲያብሎስ ‹እግዚአብሔርኰ መሐሪ› ነው ይልሃል፣ በኃጢአት ከጣለህ በኋላ ግን እንድትጨነቅና ተስፋ እንድትቆርጥ የእግዚአብሔርን ይቅርታ እያዘናጋ ንስሐ ከመግባት ያግድሃል፡፡›› ቅድስት ዮሐና ኢልድራጊ፡፡
· ‹‹ፈሪሃ እግዚአብሔር ከሌለ ንስሐም የለም›› ቅዱስ ይስሐቅ
· ‹‹ሰው ልጅ በወደቀ ጊዜ እግዚአብሔርን መምሰል ተነጥቆ ነበር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው ያጣነውን መልክ ሊመልስልን ነው፡፡›› ቅዱስ አትናቴዎስ
· ‹‹የሰውነት መሞት የነፍስ ከሥጋ መለየት ነው፣ የነፍስ መሞት ማለት ግን የነፍስ ከእግዚአብሔር መለየት ነው፡፡›› ቅዱስ አውግስጢኖስ
· ‹‹በራሳችን ላይ ከፈረድንበት እግዚአብሔር በኛ ይደሰታል፡፡›› ቅዱስ እንጦንስ
· ‹‹ኃጢአታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል፣ ኃጢአታችንን እኛ ረስተን የምንዝናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል፡፡›› ቅዱስ እንጦንስ