View in English alphabet 
 | Thursday, April 18, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
  

የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ ሀገረ ስብከት አዲስ ዌብ ሳይት ከፈተ

www.eotcdc.org

 

የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ ሀገረ ስብከት የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት፣የመንበረ ፓትርያርኩን እና የሀገረ ስብከቱን የሥራ እንቅስቃሴ፣አስፈላጊ የሆኑ ቤተ ክርስቲያናዊ መረጃዎችን እና ዜናዎችን የሚያቀርብበት አዲስ ዌብ ሳይት ከፍቷል፡፡

ሰኔ 29 ቀን 2000 ዓም በብጹዕ አቡነ አብርሃም የሰሜን ምሥራቅ፣ የደቡብ ምሥራቅ እና የመካከለኛው አሜሪካ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት እና የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡

 

የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከትን ይበልጥ ለማጠናከር፣የራሱ ቢሮ እና የተሟሉ መሣርያዎች እንዲኖሩት ለማድረግ እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን ከእነዚህ እንቅስቃሴዎች አንዱ ሀገረ ስብከቱ ራሱን እና መላዋን ቤተ ክርስቲያን የሚያስተዋውቅባቸው ሚዲያዎች እንዲኖሩት ማድረግ ነው፡፡

 

በአሁኑ ጊዜ www.eotcdc.org በሚል ስያሜ የሀገረ ስብከቱ ይጆዊ ዌብ ሳይት የተከፈተ ሲሆን በመረጃዎች፣ በፎቶዎች፣ በትምህርቶች እና በመሳሰሉት ይበልጥ እየተጠናከረ ይሄዳል፡፡ በዚህ አገልግሎት ዕውቀቱ እና ፍላጎቱ ያላችሁም ትሳተፉ ዘንድ ሀገረ ስብከቱ ይጋብዛል፡፡

 
ለወደፊቱም የቴሌቭዥን እና የሬዲዮ ፕሮግራሞችን ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን እግዚአብሔር ፈቃዱ በሆነበት ጊዜ ለአገልግሎት ይበቃሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡
በዚህ ሥራ የተራዱንን ሁሉ በእግዚአብሔር ስም እናመሰግናለን፡፡
 
የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት
ዋሽንግተን ዲሲ



Written By: host
Date Posted: 7/13/2008
Number of Views: 8551

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement