View in English alphabet 
 | Thursday, April 18, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
  

በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል የተዘጋጀ ዐውደ ርእይ በቦስተን በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰ/ት/ቤ/ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በሰሜን አሜሪካ ማዕከል የተዘጋጀውና መስከረም 24 ዓ.ም እና 25/ 2ዐዐዐ ዓ.ም (Oct 4- 5, 2008) ለ2 ቀናት በቦስተን ከተማ   (St Paul A.M.E Church Christian Life Center) ለዕይታ የበቃው ዐውደ ርእይ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ፡፡ ፎቶዎችን ይመልከቱ

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ታሪካዊና መንፈሳዊ ቅርሶች የሚያስተዋውቀው ይኸው ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትናንት፣ ዛሬ፣ነገ›› በሚል ርዕስ የቀረበው ዐውደ ርእይ የቤተክርስቲያን አባቶች፣ በማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ ማዕከል ጸሐፊና ምእመናን በተገኙበት ቅዳሜ ከጠዋቱ 4፡ዐዐ (10:00am) በደመቀ ሁኔታ ከተከፈተ በኋላ አያሌ ኢትዮጵያውያንና የሌላ ሀገር ዜጎች ለመጎብኘት ዕድል አግኝተዋል፡፡ በዓይነቱ ልዩ የሆነውና ዘጠኝ የትዕይንት ክፍሎችን የያዘው ይህ ዝግጅት ተመልካቾችን ያስተማረ መሆኑን በአስተያየት መስጫ ላይ ገልጸዋል፡፡ 


Written By: host
Date Posted: 10/4/2008
Number of Views: 10640

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement