View in English alphabet 
 | Friday, April 19, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
  

በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል የተዘጋጀ ዐውደ ርእይ በዴንቨር በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰ/ት/ቤ/ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በሰሜን አሜሪካ ማዕከል የተዘጋጀውና ጥቅምት 1 እና 2 2ዐዐዐ ዓ.ም (Oct 11- 12, 2008) ለ2 ቀናት በዴንቨር ከተማ   (በዴንቨር ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን) ለዕይታ የበቃው ዐውደ ርእይ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ፡፡ ፎቶ

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ታሪካዊና መንፈሳዊ ቅርሶች የሚያስተዋውቀው ይኸው ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትናንት፣ ዛሬ፣ነገ›› በሚል ርዕስ የቀረበው ዐውደ ርእይ የቤተክርስቲያን አባቶችና ምእመናን በተገኙበት ቅዳሜ ከጠዋቱ 4፡ዐዐ (10:00am) በደመቀ ሁኔታ ከተከፈተ በኋላ አያሌ ኢትዮጵያውያንና የሌላ ሀገር ዜጎች ለመጎብኘት ዕድል አግኝተዋል፡፡ በዓይነቱ ልዩ የሆነውና ዘጠኝ የትዕይንት ክፍሎችን የያዘው ይህ ዝግጅት ተመልካቾችን ያስተማረ መሆኑን በአስተያየት መስጫ ላይ ገልጸዋል፡፡ 

ፎቶ ክፍል 1 ክፍል 2


Written By: host
Date Posted: 10/14/2008
Number of Views: 9306

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement