View in English alphabet 
 | Thursday, March 28, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
  

የመጻሕፍት ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ሊዘጋጅ ነው

`አንድ መጽሐፍ ይለግሱ´ በሚል መሪ ቃል በገጠር እና ጠረፋማ አካባቢ ለሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት፤ ለሰንበት ት/ቤቶችና ለአብነት ት/ቤቶች የመጽሐፍ ድጋፍ ለማሰባሰብ የሚያስችል መርሐ ግብር በማኀበረ ቅዱሳን ሊጀመር ነው፡፡

በገጠር እና ጠረፋማ አካባቢ ለሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ፡ ሰንበት ት/ቤቶች እንዲሁም ለአብነት ት/ቤቶች የመጽሐፍት ድጋፍ ለማሰባሰብ የተዘጋጀ ፕሮጀክት

 

በማኀበሩ የማኀበራዊ አገልግሎትና ልማት ዋና ክፍል የቅስቀሳና የገቢ አሰባሳቢ ክፍል ያዘጋጀውን ይህንኑ መርሐ ግብር ለማስተዋወቅ ባለፈው አርብ ኀዳር 19 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ከማኀበሩ አባላት፤ ከተለያዩ መንፈሳዊ ማኀበራትና ሰንበት ት/ቤቶች ተወካዮች ጋር በተደረገው ውይይት እንደተገለጸው ከመላው ሀገሪቱ አልፎ በአውሮፖ፤ በአሜሪካና በካናዳ የሚከናወነው ይኸው መርሐ ግብር የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ታሪክ፤ ባህል፤ ትውፊትና ቅርስ ለማስጠበቅ የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ነው ተብሏል፡፡

 መርሐ ግብሩ በአዲስ አበባ ከታኀሣሥ 11 እስከ 12 2ዐዐ1 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን በሌሎች አካባቢዎች እንደ አመቺነቱ በተለያዩ ጊዜያት ይካሄዳል፡፡

 በዚሁ መርሐ ግብር ምእመናን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጀምሮ በቤታቸው ውስጥ ያላቸውን ሃይማኖታዊ መጻሕፍት መለገስ የሚችሉ መሆኑንና የሌላቸው ደግሞ ሊለግሱ ያሰቡትን መጻሕፍት ዋጋ ማበርከት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

 ልገሳው መጻሕፍትን ብቻ ሳይሆን ቴኘ ሪከርደርና የመጽሐፍ መደደርደሪያ ሸልፍን ያካትታል፡፡ የተሰበሰቡትም መጻሕፍትና ሌሎች ቁሳቁሶች/ቴኘ ሪከርደሮችና ሸልፎች/ ከጥር 1 እስከ ነሐሴ 3ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. ለተጠቃሚዎች እንደሚደርስ ተገልጿል፡፡ |…መጻሕፍቱን ይልቁንም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ´ 2ጢሞ. 4፤13፡፡ የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መሠረት በማድረግ ምእመናን በመርሐ ግብሩ እንዲሳተፉ አስተባባሪዎቹ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 


Written By: host
Date Posted: 12/5/2008
Number of Views: 6380

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement