View in English alphabet 
 | Thursday, April 25, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
  

በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል አዲስ መንፈሳዊ የፓልቶክ አገልግሎት ጀመረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተሕዋዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል ልሳነ ተዋሕዶ የተሰኘ መንፈሳዊ የፓልቶክ አገልግሎት ጀመረ።

ማዕከሉ የአዲሱን የፓልቶክ አገልግሎት የሙከራ ስርጭት ከኅዳር ፲፭ እስከ ፳፱ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም. ሲያደርግ  ቆይቶ ታኅሳስ ፩ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም. ምሽት ለሦስት ሰዓታት በቆየ  የመክፈቻ ሥነ ስርዓት መደበኛ ስርጭቱን በይፋ ጀምሯል

በፓልቶክ በተዘጋጀው በዚህ የመክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ከለንደን እንዲሁም ብፅዕ አቡነ ዮሴፍ የደቡብ ምሥራቅ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ከሮም ተገኝተው ቡራኬና ምክር የሰጡ ሲሆን የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም ከአዲስ አበባ የእንኳን ደስ አላችሁና የማበረታቻ መልዕክት አስተላልፏል።

አኃት ማዕከላትን በመወከል ከአሜሪካና ከካናዳ ማዕከላት ተወካዮች መልዕክት የተላለፈ ሲሆን ስለ አውሮፓ ማዕከል እንቅስቃሴ መረጃ በማዕከሉ ጽሕፈት ቤት እንዲሁም ስለ ልሳነ ተዋሕዶ አገልግሎት ዓላማና ይዘትም በማዕከሉ የቴክኖሎጂ ክፍል ማብራሪያ ተሰጥቷል። 

በማብራሪያው ልሳነ ተዋሕዶ መንፈሳዊ የፓልቶክ አገልግሎት ለጊዜው ሰኞና ረቡዕ ለሁለት ሰዓታት ያህል በመካከላኛው አውሮፓ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ፳ ሰዓት እስከ ፳፪ ሰዓት እንደሚተላለፍ የተጠቆመ ሲኾን በመላው ዓለም የሚገኙ አነው ካህናትና ሰባክያነ ወንጌል ማእከሉ በከፈተው በዚህ መድረክ እንዲያገለግሉ ምእመናንም እንዲገለገሉ ጥሪ ቀርቧል፡፡ 

በመጨረሻም በመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ ላይ ለተገኙት ወገኖች ”የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል” በሚል ርዕስ በመልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው ትምህርት ተሰጥቶ የመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ ተጠናቋል።  

የልሳነ ተዋሕዶ ስርጭት በቀጥታ ላልተከታተሉ በ http://www.lisanetewahedo.org/paltalk/  ይገኛል። 


Written By: host
Date Posted: 12/16/2008
Number of Views: 8234

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement