ዐውደ ርዕዩን የሲያትል ከተማ ነዋሪዎች፣ ከፖርትላንድ ኦሪገንና ከካናዳ ቫንኮቨር በህብረት የመጡ ምእመናን እንዲሁም ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ዜጐች ተመልክተውታል፡፡ ከፖርትላንድና ከቫንኮቨር የመጡ ካህናትና ምእመናን ዝግጅቱ ለወደፊቱ በከተሞቻቸው እንዲታይ ሁኔታዎች እንዲመቻቹላቸው ጠይቀዋል፡፡
በአጠቃላይ የዐውደ ርዕዩ ይዘት ደረጃውን የጠበቀና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን መጠነ ሰፊ መንፈሳዊ ሀብቶች፣ ወቅታዊ ሁኔታና የወደፊት ርዕይ በሚገባ ያመላከተ መሆኑ እንዳስደሰታቸዉ ከተመልካቾች ከተሰጠው አስተያየት ለመገንዘብ ተችሏል፡፡
በዚህ ዐውደ ርዕይ ላይ በሲያትል ከተማ ከሚገኙ አድባራት የመጡ የሰ/ት/ቤት ወጣቶች በገለፃ ስላደረጉት ተሳትፎ እንዲሁም ምእመናንን በገንዘባቸው፣ በምክር፣ በፀሎትና በእውቀታቸው ስላደረጉት አስተዋጽኦ ቀጣና ማዕከሉ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡ፎቶዎችን ይመልከቱ