View in English alphabet 
 | Friday, April 26, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
  

የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡቦንግና የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተጠመቁ

በ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የተገነባው ቤተክርስቲያን ተመረቀ፡፡                   


የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮምሽነርና የካቢኔ ጉዳዮች ጽ/ቤት ሓላፊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን እምነት ተቀብለው ተጠመቁ፡፡ በጋምቤላ ሀገረ ስብከት በአንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የደብረ መድኃኒት ቅድስት ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ተጠናቆ ቅዳሴ ቤቱም ተከብሯል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳዉሎስ ¬ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ምክር ቤት የክብር ፕሬዝዳንት የክልሉን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ካጠመቁ በኋላ እንደ ተናገሩት፣ ልጆቻችን የኢትዮጵያን ኦርቶዶስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓተ እምነት ተምረው በመጠመቃቸው ቤተክርስቲያን እጅግ የላቀ ደስታ ይሰማታል፡፡

«ቤተክርስቲያን ከበረቱ ውጪ ያሉ ብዙ በጎች አሏት» ያሉት ቅዱስነታቸው፤ እንደነ ጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና ከፍተኛ ባለሥልጣናት ያሉ ብዙ ታላላቅ ሰዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን እምነትና ሥርዐት ተቀብለው ሀገራቸውን በተረጋጋ ሰላምና ልማት መምራታቸውን በመጥቀስ አስረድተዋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡቦንግ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስ ቲያንን እምነት መሠረታዊ ትምህርቶችን ከሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅና ከሊቃውንቱ ዘንድ በሚገባ በመከታተል ከነመላ ቤተሰባቸው መጠመቃቸውን ገልጸዋል፡፡ 

በዚህም ከፍተኛ ደስታና መረጋጋት እንደተሰማቸው የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ቤተክርስቲያኒቱ ከምታስ ተምራቸው መሠረታዊ የእምነቱ ሥርዓቶች በተጓዳኝ በልማቱና በሰላሙ መስክ ኅብረተሰቡን ለማገልገል የምታደርገው እንቅስቃሴ ወደ ክርስትናው እንደሳባቸው አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት በመጽናትና በሥነ ምግባር በመታነጽ የሰላም አምባሳደር ለመሆን እንደሚጥሩ የጠቆሙት አቶ ኡሞድ፤ በቤተክርስቲያኒቱ የልማት ሥራ ላይ በመሳተፍ ሃይማኖታዊ ግዴታቸውንም እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

በዕለቱ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና ቤተሰቦቻቸው ጋር በመጠመቅ የእግዚአብሔርን ልጅነት ካገኙት ወን ድሞች መካከል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኡቲያንግ ኡቻንና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የካቢኔ ጉዳዮች /ቤት ሓላፊ አቶ አሙሉ ኡቻን ይገኙበታል፡፡

በዚሁ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት አንዳንድ ምእመናን በሰጡት አስተያ የት፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና ከፍተኛ ባለሥልጣናት የእግዚአብሔርን ልጅነት በማግኘታቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

«የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ሥርዓትና እምነት ተቀብለው ለመኖር ብዙ የሚፈልጉ ወገኖች አሉ» ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ እነዚህን ወገኖች ለማምጣት ምእመናንም ሆኑ የቤተክርስቲ ያኒቱ አገልጋዮች ሁሉም በየደረጃው ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡

ከጥምቀተ ክርስትና ሥነ ሥርዓቱ በኋላም በአንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ብር የተገነባው የደብረ መድኃኒት ቅድስት ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ቤት በቅዱስ ¬ፓትርያርኩ ከብሯል፡፡ ቅዱስነታቸው በዚሁ ጊዜ እንደ ተናገረሩት፤ የጋምቤላ ምእመናን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ይሔንን የመሰለ ቤተክርስቲያን አጠናቀው ለአገልግሎት ማብቃታቸው ለእምነታቸው ያላቸውን ጽናት እንደሚያሳይ ገልጸዋል፡፡ ምእመናኑ ይህንን የእምነት ጽናት በማሳደግ ቤተክርስቲያናቸውን መጠበቅ እንደሚገባቸው ቅዱስነታቸው አሳስበው፤ በልማቱም ዘርፍ እያደረጉት ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በሥነ ሥርዓቱ ላይ ከጋምቤላ ከተማና ገጠራማ አካባቢዎች የመጡ በርካታ ምእመናንና ጥሪ የተደረገላ ቸው እንግዶች መገኘታቸውም ታውቋል፡፡ 

ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ 17 ዓመት ቁጥር 4/ቅጽ 17 ቁጥር 189 ከኅዳር 1-15 2002 . 

 


Written By: host
Date Posted: 11/12/2009
Number of Views: 10173

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement