View in English alphabet 
 | Friday, April 19, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
  

የመሐል ዘጌ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በእሳት ቃጠሎ ወደመ

በጣና ሐይቅ ዙሪያ ከሚገኙት የዘጌ ገዳማት መካከል አንዱ የሆነው የመሐል ዘጌ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን  የካቲት 5 ቀን 2002 ዓ.ም ከቀኑ  12፡00 ሰዓት ጀምሮ የአደጋዉ ምክንያት ባልታወቀ እሳት ሙሉ በሙሉ ወድሟል። እሳቱን  ለማጥፋት በገዳሙ ዙሪያ የሚገኙ ምዕመናን፣ በአካባቢው የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል እና ከባሕር ዳር ከተማ በጀልባ ተሳፍረው የሄዱ ምዕመናን ጥረት ቢያደርጉም የእሳቱን ቃጠሎ ለመከላከል እና ለማጥፋት ሳይቻላቸው ቀርቷል።

እሳቱ ከሰው ቁመት በላይ  በመንደድ የአቡነ በትረ ማርያምን ገዳም እንዳያወድም የገዳሙ ማህበረሰብና ምዕመናን በከፍተኛ ሥጋት ላይ ጥሎ ነበር። ይህም ሆኖ በቦታው የተገኘው የመከላከያ ኃይልና ምዕመናን በአንድነት ሆነው በመካከል የሚገኙ ዛፎችን በመቁረጥ የአቡነ በትረ ማርያምን ገዳም ለማዳን መቻላቸውን መረጃውን የሰጠን በማኀበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማዕከል ገልጿል።



Written By: host
Date Posted: 2/12/2010
Number of Views: 11112

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement