View in English alphabet 
 | Thursday, April 18, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
  

በ«ተሐድሶ» መሰሪ እንቅስቃሴ ላይ ዛሬም እንንቃ!

ኢትዮጵያ ያላት ክብርና ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ የታሪክ ሰነዶች የተመሰከረ፣ በታላላቅ ማራኪ ቅርሶችም የታጀበ ነው። የነበራት ክብርና ገናናነት ከምዕራብ እስከ ምስራቅ፣ ከሰሜንም እስከ ደቡብ የታወቀ ነው። ከዚህ ጉልህ ታሪክ ውስጥ የበለጠ ጎልቶ የሚታየው ደግሞ የሀገራችን የሃይማኖት ታሪክ ነው። ኢትዮጵያ ከእስራኤል ወገን ቀጥሎ ብሉይ ኪዳንን በመቀበል ቀዳሚ ሀገር ናት። በመሆኑም በዘመነ ብሉይ ሕግና ነቢያትን በመቀበልና በመፈጸም እንዲሁም የተስፋውን ቃል በመጠበቅ ኖራለች። ጊዜው ሲደርስም የሐዋርያትን ስብከት ተቀብላ የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነትና ጌትነት አምና ጥምቀትን ወደ ምድሯ አምጥታለች። በመሆኑም ወንጌልን ተቀብላ አምና ስትሰብክ ኖራለች። አሕዛብ ሕግና ነብያትን በናቁበት ጊዜ ከአሕዛብ ወገን ቀድማ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ኦሪትን በመቀበሏ እንዲሁም ደግሞ እስራኤል ወንጌልን በናቁበት፣ ክርስቶስን በጠሉበት ጊዜ ከአሕዛብ ጋር ሐዲስ ኪዳንን በጊዜው በመቀበሏ ሁለቱንም ኪዳናት በጊዜያቸው ያስተናገደች ብቸኛ ሀገር ናት ማለት ይቻላል። ስለዚህ በዓለምም ሆነ በአፍሪካ መድረክ የሚያስከብር የሃይማኖት ታሪክ ባለቤት ናት። ከዚያም በመነጨ ሊሻሩ ከማይችሉት ከሕግና ከነቢያት እንዲሁም ከክርስቶስ ወንጌል፣ ከሐዋርያት ትምህርት፣ ከሊቃውንቱም ትርጓሜ የመነጨ ሰውንም እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኝ ሥርዓተ አምልኮ ባለቤት ለመሆን አስችሏታል።

ይህ ብዙዎችን የሚያስደስተውን ያህል አንዳንዶች ደግሞ በቅናት የሚመለከቱትና ለራሳቸው ፍላጎት ማሰፈጸሚያ አበላሽተው ሊጠቀሙበት ሲቋምጡ ታይተዋል፤ እየታዩም ነው። ይህንንም ታሪክ ለማጥፋት ወይም ባለበት በርዞ ከልሶ የራሳቸውን ኑፋቄና የክህደት አጀንዳ ለማስፈጸም ይሻሉ። በተለይ የምዕራቡ ዓለም «የካህኑ ንጉሥ» ሀገር እያለ የሚጠራትን ኢትዮጵያን ከመስቀል ጦርነት ጀምሮ በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ ለሚከተሉት ለየትኞቹም አጀንዳዎቻቸው መንደርደሪያ የማድረግ ጽኑ ፍላጎት እንዳላቸው ግልጽ ነው። ይህ እውን እንዲሆን ደግሞ ለሀገሪቱ አንድነት፣ ሉዓላዊነት፣ ለባህላዊና ማኅበራዊ ትስስር መሠረት ነች የሚሏትን የኦርቶዶክስ ቤተክስቲያን መቆጣጠር፤ በእነርሱም ርዕዮት ማራመድ፤ ካልሆነም ማዳከም፤ ከተቻለም መከፋፈል ይፈልጋሉ።

ይህንንም ከሱስንዮስ ዘመን ጀምሮ ለማድረግ የሚችሉትን ያህል ጥረዋል። ይህንን መሰል ቅሰጣና ሰርጎ ገብነት በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን በመሰሉ ሌሎችም አብያተ ክርስቲያናት ላይ ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል። ለዚህም በሕንድ ቅኝ ገዢ የነበሩት ፖርቱጋሎችና እንግሊዞች ዋነኞቹ ተጠቃሾች ናቸው። በሚገርም ሁኔታ ኢትዮጵያም ውስጥ ተቀራራቢ በሆነ ጊዜ እነዚሁ ኃይሎች የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ለማዳከም ለማጥፋት ተንቀሳቅሰዋል። ለዚህም በሱስኒዮስ መንግሥት ጊዜያዊ ድጋፍ አግኝተው በነበሩት በነፔድሮ¬ኤዝ የሚመራው የፖርቹጋል ሚሲዮናውያን ጥማታቸውን ለማርካት ቢተጉም በኢትዮጵያውያን ሊቃውንትና ምእመናን ጥረት ከሽፏል።

ሕንድ ውስጥ ይንቀሳቀስ የነበረው ቸርች ሚሽነሪ ሶሳይቲ /CMS/ የተባለው የአንግሊካን ፕሮቴስታንቶች ሚሽን በንጉሥ ሳህለ ሥላሴ ዘመን አይዘንበርግና ክራፕፍ የተባሉ ግለሰቦችን ወደ ኢትዮጵያ ከመላክ ጀምሮ በተከታታይ በሌሎችም ሚሽነሪዎች ጥረት ቢያደርግም ከስለላ ያለፈ ፋይዳ አልነበረውም። ቅኝ አገዛዙም ሆነ ቤተክርስቲያኒቱን ካቶሊካዊ ወይም ፕሮቴስታንት የማድረግ ወይም የመከፋፈሉ ሁኔታ ሕንድ ውስጥ እን ደያዘላቸው በዚህ ሀገር ሊሳካ አልቻለም፤ ሌላ በኦርቶዶክሳዊነት ስም የተመሠረተ የተለየ የእምነት ተቋም የለምና።

በቤተክርስቲያኒቱ በእነርሱ ምክንያት ወይም በሌላ ምክንያት የሚፈጠሩ ልዩነቶችን በነገሥታቱና በሊቃውንቱ ከፍተኛ ጥረት በጉባኤዎች እየተፈቱ ያለምንም የውጭ ኃይሎች ጣልቃገብነት አንድነታችንን ጠብቀን ኖረናል። ይህም ለቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለሀገር አንድነትም መሠረት ሆኗል።

የሀገሪቱ ነጻነትና አንድነት እንዲሁም ለረጅም ዘመን የኖረ የሃይማኖት ታሪክ ባለቤትነት በተለይ አፍሪካውያንንና የዓለምን ጥቁር ሕዝቦች እየሳበ መምጣቱ ለእነዚህ ኃይሎች የበለጠ የሚያ ንገበግብ ሆኖባቸውል። ስለዚህ መላውን አፍሪካና ሌላውንም ሕዝብ ለመማረክ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን መቆጣጠር፤ የተለየና የተወገዘ አስተምህሮአቸውን መጫን ወይም አንሸራቶ ማስገባት፤ ካልሆነም አዳክሞና አጥፍቶ ሌላ መሠረት በመሥራት ወደሌላው ወገን የመዝመት ብርቱ ዓላማ አላቸው።

በተለይ በአሁን ጊዜ ማንኛውም ወገን በሀገሪቱ የራሱን ሃይማኖት በነጻነት የማ ራመድ መብት ያለው በመሆኑ የራሳቸውን አምልኮ የሚፈጽሙበት በዓይነት ብዙ ድርጅት ቢኖራቸውም የአትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዓለም ላይ ያላትን የሃይማኖት ታሪክ ክብርና ትኩረት ያህል የማግኘት ምንም እድል እንደሌላቸው ተገንዝበዋል። በመሆኑም ሌላ ዘርፈ ብዙ መላ መዘየድ ጊዜው ጠይቁአቸዋል። ለዚህ የመረጡት አካሔድ «ተሐድሶ» የተባለውን የመናፍቃን ተላላኪ ኃይል በቤተክርስቲያን ውስጥ ማስረግ ነው።

«ተሐድሶ» የተባለው በተለያዩ መና ፍቃን የሚደገፍ፣ ተቋማዊ ሆኖ ያል ተደራጀ፣ ወጥ አስተምህሮ የሌለው፤ ነገር ግን ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ብሎ የተሰለፈ፤ በየትኛውም መንገድ የቀጠሩትን የተለያዩ የመናፍቃን ፍላጎት ለማርካት ቤተክርስቲያንን ለመቆጣጠር በውስጥና በውጭ ያሸመቀ ኃይል ነው። ከዚህ ቀደም ማኅበራችን ይህንኑ በኅቡዕ የተደራጀ የተወሰኑ መነኮሳት፣ መርጌቶችና የዲያቆናት የተላላኪነትና የምንፍቅና አካሔ ድን ካጋለጠ ጀምሮ ግን ካህናትና ምእመናን ጉዳዩን ወደ ማጤን እንዲገቡ አስገድዱአል። ይሁን እንጅ በጊዜው ለአንዳንዶች እነዚህ አካላት የቤተክርስቲያን ጠላቶች ሳይሆኑ የማኅበረ ቅዱሳን የአገልግሎት ተገዳዳሪዎች ተደርገው ይታሰቡ ነበር። ይህን ድብቅ እንቅስቃሴያቸውን የሚከታተል ታዛቢ፣ ተመልካች በየሰንበት ትምህርት ቤቱ መኖሩን፤ ካህናቱም እያንዳንዱን እንቅስቃሴ መፈተሽ በመጀመራቸው ለስውር እንቅስቃሴአቸው በር እይተዘጋ መምጣቱን ተረዱ። በመሆኑም ያላቸው ብቸኛ አማራጭ ግእዝ ተናጋሪ መናፍቅ ሆነው፡ የቤተክርስቲያንን መዓርጋት በስማቸው እየቀጸሉ፡ ለመጻሕፍት፣ መጽሔትና ጋዜጦቻቸው ኦርቶዶክሳዊ ገጽታ እያላበሱ በግልጽ ፕሮቴስታንታዊ አስተምህሮን መዝራት ጀመሩ። ይህ ደግሞ የ«ተሐድሶ»ን እንቅስቃሴ እውነተኛ ምንነትና በቤተክርስቲያን ጠላትነት የተሰለፈ ኃይል እንጂ የማኅበረ ቅዱሳን የአገልግሎት ተገዳዳሪ አለመሆኑን በራሱ እንቅስቃሴ ግልጽ አደረገ።

በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ላይ የተመሠረተው ኑፋቄን የመዝራት ስልት በመምህራንና በሊቃውንቱ በተደረገው ለእምነት ጠበቃ የመሆን ተከታታይ እንቅስቃሴ ዋጋ እያጣ ሲመጣ ክርክራቸውን ወደ ገድላትና ድርሳናት በማዞር የነርሱን የኑፋቄ ዘር ከማምከኑ እንቅስቃሴ ሊቃውንቱ ዞር ብለው ቤተክርስቲያኒቱ ብቻ በምትጠቀምባቸው በራሷ መጻሕፍት ላይ በመከራከር ሊቃውንቱ ጊዜ እንዲያጠፉ፤ ከተቻለም በቤተክርስቲያን መከፋፈል እንዲፈጠር ተንቀሳቅሰዋል። ይህንን ለማድ ረግም ግእዝ ጠቃሽ ነን የሚሉ፤ በማኩረፍ፣ ጥቅምን በመፈለግና በመታለል ወዘተ ወጥተው በየጥጋጥጉ የሚወራጩ መርጌቶችን በመጠቀም ነው። ይህ ደግሞ ከመቶ ዓመት በፊት ከሁለት ምዕተ ዓመታት ላላነሰ ጊዜ የቤተክርስቲያኒቱን ሊቃውንት ሲያተራምሱበት እንደቆዩት የቅባትና የጸጋ አስተምህሮ የቤት ሥራ ዓይነት ለሊቃውንቱ የመስጠት ስልት ነው። እነዚሁ «ተሐድሶ» ብለው ራሳቸውን የሚጠሩት የመናፍቃን ተላላኪዎች ቤተክርስቲያናችንን ለመቆጣጠር ያስችለናል የሚሉትን የትኛውንም ስልት ከመጠቀም ወደኋላ የማይሉ አካላት ናቸው። ጎሳና ጎጥን ለማናከስ፣ በፖለቲካ ጉዳዮች በማስመሰል ለመክሰስ፣ ስም በማጥፋት አንዱን በአንዱ ላይ ለማነሣሣት ወዘተ ይጥራሉ፤ እየጣሩም ነው።

የ«ተሐድሶ» ኃይል ከውጭ ተበታትኖ ያለ ፈታኝ ይምሰል እንጂ በሁለት መልኩ ተሰልፎ የሚሠራ እርስ በእርሱ የሚተዋወቅም የማይተዋወቅም ኃይል ያለው ነው። በአንድ ገጽ ከውጭ ኦሮቶዶክሳዊ ነኝ እያለ በግእዝ እየጠቀሰ፣ አሉባልታ እያራባ፣ የሊቃውንቱን ትምህርት እያጣመመ፤ ስልት በመሰለው መንገድ ሁሉ ከአርዮሳውያን ጀምሮ እስከ ንስጥሮሳውያን፣ ከሊዮን እስከ ሉተር የተነሡ መናፍቃንን ትምህርት በተለያዩ መንገዶች /መጻሕፍት በመጻፍ፣ መጽሔትና ጋዜጣ በማሳተም፣ በራሪ ወረቀት በማሳተም/ እየዘራ፡ ከቤተክርስቲያን ውጡ እያለ ወደ ውጭ የሚስብ በፈሪሳውያን መንገድ የቆመ ጎታች ኃይል /pulling power/ ነው። ሌላው ደግሞ ከውስጥ ሆኖ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ለዓላማው ተባባሪ ከሆኑ የቤተክርስቲያኒቱ የውስጥ አካላት ጋር በተለያየ መንገድ ምእመናንን እያ ስደነበረ የሚያስወጣ ገፊ ሃይል /pushing power/ ሆኖ በአስቆርቱ ይሁዳ መንገድ የቆመ ነው።

በዚሀ ይሁዳዊ ግብር ውስጥ የሚሳ ተፈው ተላላኪ ቤተክርስቲያንን አሳልፎ ለመስጠት በሚያስችለው መመሳሰል ውስጥ ያለ ሲሆን በምእመናንና በሊቃውንቱ ፊት ተጨባጭ መረጃና ማስረጃ እስከሚቀርብብኝ ድረስ ተሰውሬ እሠራለሁ ብሎ የሚያስብ በተናጠልና በቡድን የሚሹለከለክ ኃይል ነው።

ይሄ ወገን በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ሆኖ በተለያዩ የቤተክርስቲያኒቱ መዋ ቅሮች ውስጥ እንቅፋት እየፈጠረ ቤተ ክርስቲያኒቱ ብቁ አገልግሎት እንዳ ትሰጥ ያዳክማል። የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር የበቃና የነቃ አገልግሎት ፈጽሞ ካህናትና ምእመናንን እንዳያረካ፤ በምእመናንና በሊቃውንቱ በቤተ ክርስቲያኒቱም አስተዳደር መካከል መለያየትና መጠራጠር እንዲነግሥ የበኩሉን ሚና ይጫወታል። የካህናትን ስምና ክብር በማጉደፍ ምእመናን ለክህነት ክብር እንዳይኖራቸው፤ የንስሐ አባትና ልጅ ግነኙነታቸው እንዲላላ ያደርጋል። በካህናት ወይም በሊቃውንት አባቶች በኩል የሚታዩ ግድፈቶች ወይም ጥፋ ቶችን በማጯጯኽ አጠቃላይ የቤክር ስቲያኒቱ ድክመት አድርጎ በማወራረድ የሚያታልል፤ ምእመናን በቤተ ክርስቲያኒቱ አካሔድ ተስፋ እንዲቆርጡ በጋዜጣና በመሳሰሉት ብዙኃን መገናኛዎች በመዝራት ትርፍ ለማግ ኘት የሚጥር ነው። ብርቱ አገልግሎት በመፈጸም የቤተክርስቲያኒቱን ተልእኮ ለመወጣት ጥረት የሚያደርጉ ማኅበራትን፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን፣ መም ህራንን፣ አባቶችን ስም በማጥፋት ከምእ መናን ለመለይት ይንቀሳቀሳል። «ተሐድሶ» ለዚህ ግብሩ ከምእመናን ጀምሮ እስከ ታላላቅ አባቶች ድረስ አውቀ ውም ሳያውቁም የአጀንዳው አስፈጻሚ ወይም መሰላል የሚሆኑ ድጋፍ ሰጭ ዎችን ለመመልምል ጥረት ያደርጋል:: እነዚህም አካላት የቤተክርስቲያኒቱን አሠራር እንዲያውኩ ብቻ ሳይሆን ገጽታዋን በማበላሸት መንጋው ደንብሮ እንዲበተን መሣሪያ ለማድረግ ነው:: የቤተክርስቲያኒቱን አገልጋዮች መለያ ለብሰው ወይም መስለው፣ በማይገባ ጊዜና ቦታ የማይገባ ነገር ሲያደርጉ በመ ታየት ምእመናንን በማስቆጣት ላይ ያሉ ሐሳዌ መነኮሳት፣ ቀሳውስት፣ ባህ ታውያን ወዘተ የዚህ ስልት አስፈጻ ሚዎች ናቸው:: በመልካም ግብር ለመ ጽናት ባለመቻላቸው ተስፋ ቆርጠው አላግባብ በእንዝህላልነት የሚራመዱ አንዳንድ አገልጋዮችም የዚህ የጥፋት ዓላማ ተባባሪዎች እየሆኑ ነው:: ተግባራቸው ምእመናንን ከቤተክርስቲያን አስወጥቶ የሚጥል በመሆኑ በውስጥ እየ ሠራ ያለው የ«ተሐድሶ» ገፊ ኃይል መሣሪያ ሆነዋል:: ቢያንስ ምእመናንን ላለማሰናከል ጥንቃቄ ሲያደርጉ አታይምና::

ከሁሉም በላይ አሳሳቢው አካሔድ ግን የቤተክርስቲያኒቱን ሐዋርያዊ ተልእኮ ወዴትም እንዳይራመድ አሳስሮ ለማስቀመጥ፤ ይህንን የ«ተሐድሶ» መረብ በጥሰው በማለፍ ለስብከተ ወንጌል አገልግሎት የሚንቀሳቀሱ አካላትንም ከአስተዳደሩ በማ ጋጨት ወይም ለመከፋፈል በመሞከር ወዘተ ምንም ዓይነት ውጤታማ የአገልግሎት እንቅስቃሴ እንዳይደረግ የሚችለውን ያህል ጥረት ማድረግ ነው:: ቤተ ክርስቲያን ያላትን ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ አውላ መንፈሳዊ አገልግሎቱን ማቀላጠፍ እንዳትችል ለማድረግ፡ ከዚያም አልፎ የካህናቱን የኑሮ ሁኔታ ሊያሻሽሉ የሚችሉ ውጤታማ ፕሮጄክቶች ስልታዊ በሆነ መንገድ ተግባራዊ እንዳይደረጉ፤ የቤተክርስቲያን የአገልግሎት ተቋማት የመፈጸም አቅም እንዳይጎለብት የተለያዩ መሰናክሎችንና ውዥንብሮችን ለመፍጠር ይጥራል:: ይህን ውዥንብር «ተሐድሶ» የሚፈልግበት ወሳኝ ምክንያት በቤተክርስቲያኒቱ አጠቃላይ አካሔድ አለመርካት እንዲኖር፤ ተስፋ መቁረጥም በምእመናንና ካህናቱ ዘንድ እንዲሰፍን፤ ከዚያም መከፋፈል እንዲፈጠር ለማድረግ ነው::በቤተክርስቲያን አካባቢ አልፎ አልፎ የሚፈጠሩ ውዝንብሮችና ዓላማና ግባቸው የማይታወቁ መጠላለፎች በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ገፊ ኃይሎች ሆነው በስውርና በግልጽ የሚንቀሳቀሱ የ«ተሐድሶ» መረብ አባላትና ተባባሪዎቻቸው የሚፈጥሯቸው ውዝግቦች ናቸው::

እነዚህ ገጽታን በማጉደፍና ቁሳዊ ጥቅሞቻቸውን ለማርካት ቤተክርስቲያኒቱን እስከመሸጥ የተሰለፉ አካላት በሕግና በቀኖና መሠረት ቤተክርስቲያን እንዳትሠራ፤ በየትኞቹም ጉዳዮች ለቁጥጥር የሚያመች ማዕከላዊ አሠራር እንዳይዘረጋ ይታገላሉ:: ይህንንም የሚያደርጉበት ምክንያት አዲስ የኑፋቄ ትምህትን አንሸራቶ ለማ ስገባት ለሚተጉበት እንቅስቃሴያቸው የተመቹ ሁኔታዎችን ለመትከልና ለ«ተሐድሶ» እንቅስቃሴ አውቀውም ሳያውቁም ገፊ ኃይል በመሆን ለተሰለፉ ግለሰቦችና ቡድኖች ወረታ የሚሆን፣ ለሥጋዊ ፍላጎታቸው የሚጠቀሙበትን ንግድ በስብከተ ውንጌል ስም ለማስፋፋት ነው::

«ተሐድሶ» ቤተክርስቲያኒቱ ያላትን አሠራር በማስረጀት፣ ፕሮቴስታንታዊ አስ ተምህሮን ወደቤተክርስቲያን ለማንሸራተት ሲተጋ ለቤተክርስቲያን የሚያስፈልጋትን የአሠራር የመዋቅር እና የመፈጸም አቅም ተሐድሶ /Renaissance/ ግን ለመቅበር ይታገላል:: ቤተክርስቲያናችን በራሷ ሉዓላዊ አስተዳደር መመራት የጀመረች በት ጊዜ መቶ ዓመት ያልሞላው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እንዲሁም ከዚያም በኋላ የተፈጠሩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ለውጦች ባስከተሉት ጫና በአሠራር፣ በመዋቅርና በመፈጸም አቅም በተከታታይ ሊደረጉ የሚገባቸው የእድገትና የለውጥ እንቅስቃሴዎች ሳይታሰቡ፤ ሳይተገበሩም ቆይተዋል:: «ተሐድሶ» የተባለው ይህ የመናፍቃን ተላላኪ ደግሞ አስፈላጊውን የለውጥና የማሻሻያ እርምጃ በማፈን በአውሮ¬ በመካከለኛው የታሪክ ዘመን እንደተደረገው በተሐድሶ ስም ሌላ የእምነት አስተምህሮን አንሸራቶ ለማስገባት ይሠራል::

ተፈላጊውን ማሻሻያ የሚጠላበት ምክንያት ቤተክርስቲያን በአፈጻጸም ደካማ እየሆነች ስትሔድ ምናልባትም በሚያስቆጣ ደረጃ ምእመናን ያልተደራጀና ከክርስትና ሥነምግባር ውጭ የሆነ ዐብዮታዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ገብተው በካህናቱ ላይ እንዲነሡ፤ ቤተክርስቲያንም እንድትበታተን ለማድረግ የታለመ ነው:: አሁንም በግልጽ እየታየ ያለው የአባቶች መወጋገዝና መከፋፈል እየጨመረ በጎጥና በዘር ላይ የተመሠረተ የተበታተነ አደረጃጀት እንዲኖር ለማድረግ ነው:: ይህንንም አሁን «ተሐድሶ» በግልጽ እየጻፈ በሚያወጣው መጻሕፍት ከእነ እገሌ ወገን ጳጳሳት ለምን አይሾሙም እያለ የሚያነሣው ከንቱ ልፍለፋ ይህን ያሳያል:: የካቶሊክ ቤተ እምነት በመካከለኛው የአውሮ¬ የታሪክ ዘመን በነበረበት የጊዜውን ማኅበረሰብ ያለማርካት ችግር በተፈጠረው ተቃውሞ ቤተ እምነቱን ከሁለት የከፈለ ድንገተኛ ክስተት በ«ተሐድሶ» ስም ማስተናገዱ ይታወቃል:: በዚህ ያለው የመናፍቃን ተላላኪ «ተሐድሶ» ያንን መሰል ተከፍሎ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዲፈጠር ያልማል:: ለዚህም ለተቃውሞ የሚያነሣሡ ብልሹ አሠራሮች በየደረጃው ባሉ የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር ውስጥ እንዲሰፍን ገፊ ኃይል ሆኖ በውስጥ በሚሹለከለከው መረቡ በኩል ይጥራል:: ማኅበረ ቅዱሳን ከዚህ በፊት በመል እክቱም ደጋግሞ እንደጠቀሳው ቤተ ክርስቲያን ጠፍረው የያዙአትን ኋላቀርና ብልሹ አሠራሮች በተሻለና ሰውና እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ፣ መተማ መንንና አንድነትን በሚያጸና አሠራር መተካተ እንዳለባቸው ያምናል:: ይህንን ማድረግ ካልቻልን «ተሐድሶ» «ለውጥ! ለውጥ!» በሚለው ድምፅ ውስጥ እነዚህን የአሠራር ችግሮቻችንን ሽፋን አድርጎ በግልጽ የጀመረውን ፕሮቴስታንታዊ አስተምህሮ በሒደት አንሸራቶ ማስገባት የሚችልበት እድል እንሰጠዋለን:: ስለዚህ ያሉብንን የአሠራር ውስንነቶች በሁሉም ካህናትና ሕዝበ ክርስቲያን ተሳትፎ መቅረፍና ወደተፈላጊው ትንሣኤ ልቡና መድረስ አለብን:: ለዚህም ሁሉም የክርስቲያን ወገን ሓላፊነት ቢኖርበትም የብፁዓን አባቶች ድርሻ የጎላ ነው::

ብፁዓን አባቶቻችን በታሪክ አጋጣሚ ይህ የ«ተሐድሶ» መሰሪ ኃይል በውስጥም በውጭም በተደራጀበት ዘመን ላይ ይህቺን በብዙዎች መንፈሳዊ ተጋ ድሎ እዚህ የደረሰች ቤተክርስቲያን ባለ ደራዎች ናቸው:: አባቶች ለመንጋው የማይራሩ «ተሐድሶ»ን የመሰሉ ጨካኞች በታዩ ጊዜ ሁሉ ለራሳቸውና ለመንጋው እንዲጠነቀቁ መንፈስ ቅዱስ የዘወትር ማሳሰቢያን የሰጣቸው ናቸው:: በመሆኑም ጊዜው የሚጠይቀውን የጥንቃቄ እርምጃ ከሀገረ ስብከቶቻቸው ጀምሮ እስከ መን በረ ¬ትርያርክ ድረስ የሚወስዱበት፣ ለመንፈሳዊ ተጋድሎ ራሳቸውን የሚያዘጋጁበት ወቅት ነው:: ከምንም በላይ «ተሐድሶ» በአባቶችና በልጆች መካከል መለያየትን ለማስፈን የሚሠራ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮችን ሁሉ ያሉት ብፁዓን አባቶች የመፍታተት አቅም የሌላቸው፣ ለእውነትም የመቆም ቁርጠኝነት የሌላቸው አድርጎ ስለሚያሳይ ውጤቱ ቤተክርስቲያንን መጉዳቱ ብቻ ሳይሆን የብፁዓን አባቶችን ክብርና ስብእና የሚጎዳ ሁኔታ ሊከተል ይችላል::

የ«ተሐድሶ» ግብና ዓላማ መንጋውን ከበረቱ መበተን በመሆኑ አባት የምንሆ ንላቸውን ልጆች ከማሳጣቱም ሌላ በታሪክ ተወቃሽ ሊያደርግ የሚችል ነው:: ከዚያም አልፎ በአሠራሮቻችን ድክመት ክብረ ክህነቱ ሊጎዳ ስለሚችል «ተሐድሶ» ለሚፈልገው ሁሉም ሰው ካህን ነው ወደሚለው ፕሮቴስታንታዊ ጸረ ሃይማኖት አቋም ያሻግራል:: ስለዚህ በቤተክርስቲያን ውስጥ ተሸሽገው ለሚሠሩ የትኞቹም ገፊ ኃይሎች እንቅስቃሴ የሚመቹ ክፍተቶችን መድፈን፤ በነገሮች ሁሉ የጸናና የተጠና ማዕከላዊ አሠራርን ማስፈን፤ የቤተክርስቲያኒቱ ቀኖናና ሕግጋት ተጠብቆ እንዲሠራ ቁርጠኛ አቋም መያዝ ይገባዋል::


ማኅበረ ቅዱሳን አባቶች እንዲረዱለት የሚፈልገውም ወሳኝ ቁም ነገር እነርሱ ጳጳሳት ሆነው የተሾሙላት ቤተክርስቲያን የሃይማኖት ትምህርት ክብርና ታሪክ ተጠብቆ፡ በብዙ ሊቃውንት ተጋድሎ ተጠብቆ ዘመናትን ተሻግሮ የተቀበልነው ማራኪ ሥርዓትም ቀጣዩ ትውልድ የማየትና የመሳተፍ እድል እንዲኖረው ማድረግ ነው:: የሃይማኖት ትምህርት በዚህ ረገድ አባቶች ለሚኖራቸው እርምጃ ሁሉ በየትኛውም መልክ ቢሆን ድጋፍ መስጠት ማኅበራችን የተቋቋመበት ዓላማ መሆኑንም ያምናል:: በመሆኑም ይህ እውን እንዳይሆን የሚታገሉ የ«ተሐድሶ» መናፍቃንን ሰርጎ ገብ የጥፋት አካሔድ ለመመከት ከአባቶች ቁርጠኛ አቋምና ተከታታይ ሥራዎች ሊኖሩ ይገባል::

ቆሞሳት ቀሳውስት ዲያቆናትና በአጠቃላይ ከብፁዓን አባቶች ቀጥሎ ሓላፊነት ያለባቸው የቤተክህነቱ ወገን ሁሉ ከአጥቢያ እስከ ጠቅላይ ቤተክህነት ባለው አገልግሎት ውስጥ የዚህች ታሪካዊት ቤተክርስቲያን ባላደራዎች እንዲሆኑ መንፈስ ቅዱስ በጳጳሳት እጅ የሾማቸው የመንጋው ጠባቂ ዎች ናቸው:: በመሆኑም መንጋውን ለመበተን በውስጥና በውጭ ተደራጅቶ በዓይነት ብዙ ፈተናዎችን ለማስከተል እየሠራ ያለውን የ«ተሐድሶ» የኑፋቄ ፍላጻ በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ በጸሎት በጾም ከማምከን ጀምሮ ባልንጀሮቻችን በተለያዩ ምክንያቶች በ«ተሐድሶ» ገፊ ኃይል መረብ ውስጥ እየተጠለፉ የጥፋቱ ተባባሪ እንዳይሆኑ መጠ በቅ ይገባናል:: የ«ተሐድሶ» እንቅስቃሴ በዋናነት ምስጢረ ክህነትን የሚክድ፣ ሁሉን እንደ ካህን የሚቆጥረውን ፕሮቴስታንታዊ አስተምህሮ አንሸራቶ የማስገባት ፍላጎት ያለው መሆኑን በግልጽ በሚጽፋቸው መልእክቶች መረዳት ይቻላል:: በመሆኑም «ተሐድሶ» በተባለው የመናፍቃን ተላላኪዎች ተንኮል በሃይማኖት፣ በአካልም ሆነ በሥነልቦና የመጀመሪያው ተጎጂዎች የቤተክህነቱ ወገኖች መሆናቸው አሌ የማይ ባል ነው:: ስለዚህ በየደረጃው ባሉ የቤተክርስቲያናችን የአስተዳደር መዋቅሮች የሚፈጠሩ ችግሮች ዘገምተኛና ስልታዊ ያልሆኑ ኋላቀር አሠራሮች ሌሎችም ችግሮች የሚያስከትሉብንን ተጽእኖዎች ተስፋ ሳያስቆርጡን ወደተሻለ አሠራር ለመግባት እየጣርን የእነዚህን መናፍቃን የውስጥና የውጭ እንቅስቃሴ በእግዚአብሔር ረድኤት በብቃት መቋቋም አለብን:: ፈተናውንም ልንሻገረው ይገባል:: ቤተክርስቲያኒቱ ያላትን ሀብት ስልታዊ በሆነ መንገድ ማኅበረ ካህናቱንና ከዚያም አልፎ ለሀገር እድገት ትርጉም ባለው መልክ ባለመጠቀ የካህናቱ ኑሮ እየተጎዳ ገዳማትና አድባራት እየተፈተኑ ቢሆንም፤ ይህንን ውስጣዊ ችግር የሚ ፈታ ጠንካራና ዘመናዊ የአስተዳደር መዋ ቅር ተግባራዊ ለማድረግ ከመታገል ጋር የ«ተሐድሶ»ን መሰሪ መረብ መበጣጠስ አለብን::

ይልቁንም የችግሮቻችን ሁሉ ምንጭ ቤተክርስቲያናችንን ለማዳከም ከአሁኑ የበለጠ ጠንካራ አሠራር ዘርግታ ቀድሞ ከነበራት ክብርና ታሪክ በላይ መሥራት እንዳትችል የሚፈልጉ በዓይነት ብዙ የሆኑ አጽራረ ቤተክርስቲያን በግልጽና በስውር የሚሠሩት ደባ በመሆኑ በፍጹም ክርስቲያናዊ ወንድማማችነት ተያ ይዘን መርዛቸውን ማርከስ አለብን:: በተለየ ከውስጥ ሆኖ ገጽታን በማጉደፍ ክርስቲያኖችን በየምክንያቱ በማስደንበር ገፍቶ ለማስወጣት የሚሠራውን የ«ተሐድሶ» ገፊ ሃይል እንቅስቃሴ ለማምከን ተባብረን መቆም አለብን:: ይህ ኃይል በጎ የሚመስሉ ገጽታዎችን ተላብሶ የሚጫዎት የጥፋት ተዋናይ በመሆኑ ከመቼውም ጊዜ በላይ ካህናት ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል:: «ተሐድሶ» በሚፈ ጠሩ ጥፋቶችም ሁሉ ምእመናን በካህ ናቱ እየፈረዱ፣ በጥላቻም ካህናቱን እያዩ እንዲሄዱ የማለያየት ተልእኮም ስላለው በነገር ሁሉ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል:: በየመዋቅሮቻችን ያሉ አስተዳደራዊ ዘይቤዎችንም ፈጣንና አርኪ ለማድረግ ተገቢ የአሠራር ማሻሻያ ልናደርግ ይገባል:: ለዚህም መተባበር አለብን:: ይህ ንን ደግሞ የግድ የሚያደርገው ወቅቱ ነው:: ወቅቱ ግድ የሚለን «ተሐድሶ» እንደሚለው ሃይማኖታችንን እንድንለውጥ ሳይሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ሃይማኖ ታችንን የምናስተምርበት፣ የምናጸናበት፣ ያሉንን ሥርዓተ አምልኮ ለቀጣዩም ትው ልድ የምናስተላልፍበትን የተሻለ አስተዳደራዊ ሁኔታ ማስፈን ነው:: ለዚህም ካህናት ሁሉ ሊተባበሩ ይገባል እንላለን::

ሰንበት ትምህርት ቤቶችም «ተሐድሶ» ቤተክርስቲያኒቱን ለማዳከም መሣሪያ ሊያደርጋቸው የሚፈልጋቸው የቤተክርስቲያኒቱ የአገልግሎት ተቋማት ናቸው:: በመሆኑም ይህንን ደባ ከማክሸፍ አንጻር የአገልግሎት አሰጣጣቸ ውን እየቃኙ ወደ ከፍተኛ የስብከት ወንጌል መድረክነት ሊለወጡ ይገባል:: ሰንበት ት/ቤቶች መረዳት ያለባቸው ወሳኝ ነጥብ የአገልግሎት አሰጣጣችን ወደሚፈለገው ደረጃ አለማደግ በምእመናን ዘንድ ከፍተኛ የቃለ እግዚአብሔር ጥማት ይፈጥራል:: ይህ ደግሞ የራሳቸውን ንግድ ሊያጧጡፉ ለሚፈልጉ አንዳንድ ሰባክያንና ዘማርያን በር ከፍቱአል::«ተሐድሶ» ፕሮቴስታንታዊ አስተምህሮን አንሸራቶ በማለማመድ ሊያስገባበት የሚፈልገው ክፍተት ይህ ነው::ስለዚህ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ከነበረው በተሻለ አፈጻጸም ውስጥ ሊገኙ ይገባል:: በአጥቢያ ቤተክርስቲያናቸው ውስጥ የሚደረጉ የትኞቹንም እንቅስቃሴዎች የመከታተል፣ የአጥቢያውን ሰበካ ጉባኤ በሚያከናውናቸው መንፈሳዊና ልማታዊ ተግባራት ውስጥ ድጋፍ መስጠት የአጥቢያውንም ምእመናን ማስተባበር በአጥቢያው ውስጥ እንግዳ ትምህርትና ተገቢ ያልሆኑ ሥርዓቶችን ለማስረግ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በግልጽ የመቃወም ሓላፊነትም አለባቸው:: አሁን አሁን በአንዳንድ ጠንካራ ሰንበት ትምህርት ቤቶች እንደሚደረገው የአብነት ትምህርቶችን ለሕፃናትና ወጣቶች በመስጠት፣ ካህናትን የሚደግፉና የሚተኩ ወጣቶችን ማፍራት፣ ወቅቱን የሚዋጅ አጽራረ ቤተክርስቲያንን የሚያስታግስ ተከታታይ ትምህርቶችን አርኪ በሆነ መንገድ በዓይነትና በደረጃ ለይቶ መስጠት፣ ስልታዊ በሆኑ የመረጃ ቅብብሎሽ እየታገዙ የ«ተሐድሶ»ን ገፊና ጎተች ኃይል እንቅስቃሴ ለመግታት መተባበር አለባቸው:: በተለይ ወቅቱ ተራ በሆኑ የወጣትነት ስሜቶች የምንዘናጋበት ባለመሆኑ ቤተክርስቲያን ለዚህ ትውልድና ለዚህች ሀገር ማበርከት ያለባትን አስተዋጽኦ ማበርከት እንድትችል የማያቋርጥ ተሳትፎ ልናደርግ ይገባል::

ምእመናን የዚህች የእግዚአብሔር የጸጋ ግምጃ ቤት በሆነች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ተወልደው በቃሉ ወተት እያደጉ ያሉ፤ የአገልግሎቱ ደጋፊ፣ ተቀባይ፣ ተሳታፊም በመሆናቸው ቤተክርስቲያን ማለት እነሱ ራሳቸው እንደሆኑ መረዳት ይገባቸዋል:: አባቶቻችን የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ሆኖ ለመባረክ ክርስቶስ ያደረገልንን ማዳንም አምነው፤ በየዘመናቱ የምንነሣ እኛ ልጆቻቸውም በዚያ ጸንተን ለቀጣዩም ትውልድ ባለአደራ እንድንሆን አድርገዋል:: ይህንን ሓላፊነት የተረዱ በየዘመኑ የተነሡ ምእመናን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ድረስ ዋጋ በመክፈል ቤተክርስቲያናቸውን ሊያፈርስ ከመጣ የዲያብሎስ ሠራዊት ጋር ተጋድለዋል:: አሸናፊም ሆነዋል:: በዚህም ምክንያት ምዕተ ዓመታትን ተሻግሮ የመጣን ማራኪ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ ሕይወትን የሚ ሰጥ ሃይማኖትን ለማየትና ለመመስ ከር በቅተናል:: የያሬድን ዜማ፣ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን ሰዓታት የበርካታ ሊቃውንትን ትምህርትና ቅዳሴ የመስማት እድል አግኝተናል::

ይህንን እድል ለቀጣዩ ትውልድ የማ ስተላለፉ አደራ በእኛ ትውልድ ላይ በወደቀበት በዚህ የታሪክ አጋጣሚ ውስጥ ደግሞ በቀጣዩ ትውልድ ውስጥ በሚ ሰበሰበው መንጋ ላይ መጨከን የለብንም:: በየዘመናቱ ቤተክርስቲያንን ከአገልግ ሎት ለማዘግየት የሚወረወረው የሰይጣን ፍላጻ ዓይነቱ ይለያይ እንጂ ይኖራል:: አባቶቻችንም በእግዚአብሔር ረድኤት ያ ፍላጻ ቤተክርስቲያንን ከአገልግሎት እንዳያስተጓጉላት ዋጋ ከፍለዋል:: አሁን ደግሞ ከውስጥም ከውጭም የሚንበለበል «ተሐድሶ» የተባለ ፍላጻ እየወጋን ይገኛል:: የዚህ ሁሉ ውጊያው ዓላማ እናንተን ምእመናንን ከመንጋው ኅብረት ለይቶ ለምድ ለለበሰ ተኩላ ለመስጠት፤ ከተቻለም ራሳቸው ምእመናን የምታገለግላቸውን ቤተክርስቲያን በማጥፋቱ ሒደት እንዲሳተፉ ለማድረግ ነው:: ስለዚህ ምእመናን በዚህ አካሔድ ላይ በመንቃት ጥንቃቄ በተሞላበት እርምጃ ውስጥ እንድንገባ ያስፈልጋል:: በተለይ ትኩረት የሚስቡ የተለያዩ ሁኔታዎችን በስብከተ ወንጌል አገልግሎት ሒደት ውስጥ በማስገባት ብዙ መንጋ ከሰበሰቡ በኋላ ገንዘቡን ከመብላት አልፈው በሒደት አዲስ ትምህርትን አምጥቶ በማለማመድ ወደ ፕሮቴስታንታዊ አስተምህሮ ማንሸራተት ይፈልጋሉ:: በዚህም ግማሹን መንጋ ይዞ ለመንጎድ ቀውንም በመምህራንና ዘማርያን ላይ እምነት በማሳጣት በቤተክርስቲያኒቱ የትኛውም የስብከተ ወንጌል ማዕድ ላይ እንዳይሳተፉ ለማድረግ ነው:: በመሆኑም ምእመ ናን ክርስቶስን ትኩር ብሎ ከማየት አዘንብለው በዓለም እንዳለው የግለሰ ቦች ዝና ገንቢና ሳያውቁት ለሥጋዊና ቡድናዊ ፍላጎታቸው መጠቀሚያ እን ዳይሆኑ፤ ብሎም ውሎ አድሮ ለሚያስ ከትሉት ቤተክርስቲያንን የማዳከም ዘመቻ ተባባሪ እንዳንሆን ልንጠነቀቅ ይገባል:: ቤተክርስቲያን በአገልግሎት ሒደት ውስጥ ያሉባት ክፍተቶች እንዲሞሉ በጸሎት ከመትጋት ጋር የ«ተሐድሶ» ዘርፈ ብዙ ወጥመድ ለመበጣጠስ መቆም አለብን::
በአጠቃላይ «ተሐድሶ» ትናንት ሲያ ደርግ የነበረውን የተላላኪነት ሤራ ተል እኮ የሰጡት አካላት የሚሰጡትን የገን ዘብና የቀሳቁሰ ሰፊ ድጋፍ በመጠቀም ከውጭ ፈሪሳዊ በሆነ መንገድ ከውስጥ ይሁዳዊ በሆነ ስልት ለመዝመት እየጣረ ነው:: ሰይጣን በርካታ ጠላቶችን በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እያዘመተ ቢሆንም ከውጭ ያለውን ለማስታገስ እንዳትችል አንቆ የያዛትን የ«ተሐድሶ»ን መሰሪ ኃይል መለየትና በቤተክርስቲያናችን ውስጥ አገልግሎቱን በቅልጥፍና የሚመራ አስተዳደራዊ ትንሣኤ እንዲኖር ማድ ረግ ግን ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን ማኅበረ ቅዱሳን የጸና እምነት አለው:: ጉዳዩም የህልውና ጉዳይ መሆኑን ያምናል፡፡ ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችልም ያስባል:: ነገር ግን በተናጠልም ይሁን በኅብረት ክርስቲያናዊ ግዳጃችንን መወጣት ለነገ የማይባል ነው:: የራሳችንን ቤተክርስቲያን እንዳንጠብቅ የሚከለክለን ወይም በቁማችን ዓይናችንም እያየ ስትፈርስ እዩአት የሚለን አካል አለ ብለን አናምንም:: ምክንያቱም ቤተክርስቲ ያኒቱ ወልድ ዋሕድ ብለው የሚያምኑ፣ የቤተክርስቲያኒቱን ቀኖናና ሕግ ጠብቀው፣ አስከብረው የሚሔዱ ብፁዓን አባቶች፤ ቀን ከሌሊት በሚሰጡት የማያቋርጥ አገል ግሎት መንጋውን የሚጠብቁ ካህናት፤ በዝማሬ በውዳሴ የሚተጉ ሰንበት ተማሪ ዎች፤ ሕይወት የሚያገኙባትን ኅብረት በሚሰጡት ዐሥራት በኩራት የሚጠብቁ ምእመናን ቤተክርስቲያን ነችና:: በተለይም ቅጥረኛ ሆኖ በውስጣችን ለመሸመቅ የሚጥረውን ጨካኝና መሰሪ የ«ተሐድሶ» እንቅስቃሴ መታገስ የማይቻል ነው:: ክቡር ዳዊት «ጠላትስ ቢሰድበኝ በታገስሁ ነበር፤ የሚጠላኝም አፉን በላዬ ከፍ ከፍ ቢያደርግ ከእርሱ በተሸሸግሁ ነበር፤ አንተ ሰው አንተ ግን እንደራሴ ነበርህ» /መዝ.4÷02/ እንዳለ የ«ተሐድሶ» ፍላጻ ከውስጥ የሚወረወር በመሆኑ የከፋ ነው:: ስለዚህ እኛ ሁላችን ቤተክርስቲያናችንን ተባብረን የመጠበቅ ሓላፊነት አለብን:: ማኅበረ ቅዱሳን በዚህ ረገድ ያለበትን ሓላፊነት በእግዚአብሔር ረድኤት ከሚ መለከታቸው ሁሉም አካላት ጋር በመመካከር በተከታታይ ለመወጣት ያለውን ዝግጁነት በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጽ ይወዳል::

Share |

Written By: host
Date Posted: 12/18/2010
Number of Views: 12086

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement