View in English alphabet 
 | Thursday, April 25, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
  

የትምህርተ ወንጌል ጉባኤ በሲያትል

በሲያትል እና ኣካባቢው ከተሞች የሚኖሩ የ ኢ. ኦ. ተ. ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንን ያሳተፈ ታላቅ የትምህርተ ወንጌል ጉባኤ በሲያትል ከተማ ታህሳስ 16 እና 17 2003 ዓ.ም. ተደረገ:: በጉባኤው ላይ በሲያትል ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የተጋበዙ አባቶች ካህናት ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና ምዕመናን የተገኙ ሲሆን ፤ የኣጥቢያዎቹ ኣብያተ ክርስቲያናት የሰንበት ት/ ቤት መዘምራን መዝሙራትን ኣቅርበዋል።

በሁለት ቀኑ ጉባዔ የአጥቢያው ካህናት እና በተጋባዥነት በተገኙት መላከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል፤ እንዲሁም ሊቀ መዘምር ይልማ የተለያዩ ዝማሬዎችን በማቅረብ ከታዳሚዎቹ ጋር እግዚአብሄርን አመስግነዋል። በጉባኤው ላይ የማህበረ ቅዱሳን ኣገልግሎት በተለይም የ 10 ኣመቱ የስብከተ ወንጌል የኣገልግሎት እቅድ ለታዳሚዎች ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በቀጣይም ይህን እቅድ በተመለከተ ተከታታይ መርሃ ግብሮች እንደሚዘጋጅ ተገልጧል:: ጉባኤውን በማህበረ ቅዱሳን የኣሜሪካ ማዕከል የሲያትል ቀጠና ማዕከል ባካባቢው ከሚገኙ ኣጥቢያ ኣቢያተ ክርስቲያናት ጋር በመቀናጀት እንዳዘጋጀው ታውቋል ::

በእለቱ የተሰጡ ትምህርቶችና ፎቶዎች

  • በመጣችሁበት ኣትመለሱ - በቀሲስ ፋሲል
  • ባልንጀራዬ ማነው - በመላከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ
  • መልካሙን ስራችሁን ኣይተው - በቀሲስ ዘሚካኤል
  • ወዬልኝ - በመላከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ
  • መዝሙራት በ ሊቀ መዘምር ይልማ

  • በኤፍራታ ምድር
  • በመጨረሻው እንነሳለን ከሙታን
  • የመርሃግበሩን ፎቶዎች ይመልከቱ::


    ረድኤተ እግዚኣብሄር ኣይለየን!


    Written By: host
    Date Posted: 1/1/2011
    Number of Views: 8347

    Return

      
    Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement