View in English alphabet 
 | Sunday, May 5, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
  

ስለ ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የሚገኘው የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ደን በመቃጠሉ መነሾ በሰሜን አሜሪካ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት ሦስቱ ማኅበራት ማለትም በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል፣ በሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ እና ማኅበረ በዓለ ወልድ ባደረጉት ጥሪ እጅግ አስደሳች ምላሽ መገኘቱን በዚህም እስካሁን በጠቅላላው $24,206.52 ዶላር መዋጣቱን የማኅበራቱ ኃላፊዎች ገለፁ።


ገዳሙን እና ገዳማውያኑን እንዲሁም ደኑን ከእሳት አደጋው ለመጠበቅ እና ለመልሶ ማቋቋሚያ ለምእመናን ስለተደረገው ጥሪ እና ስለ ሕዝቡ ምላሽ ያላቸውን ምሥጋና ያቀረቡት የማኅበራቱ ኃላፊዎች ይህንኑ ገዳም በዘላቂነት ሊረዳ የሚችል አንድ ትልቅ ተግባር ለመፈጸም እንዲዘጋጁ ጥሪ አድርገዋል። “የገዳሙን ደን ድጋሚ መትከል እንችላለን። እንዲህ ዓይነቱ ችግር ድጋሚ ቢፈጠር በቶሎ መከላከል የሚያስችል ጥርጊያ መንገድ ማውጣት እንችላለን። ሌሎችም ብዙ ተግባራትን መፈጸም እንችላለን” ያሉት ኃላፊዎቹ የማኅበረ ቅዱሳን የቅዱሳት መካናትና አብነት ትምህርት ቤቶች መርጃና ማቋቋሚያ ዘላቂ የመከላከልና የልማት ሥራዎችን ለመጀመር አምስት ባለሙያዎች የያዘ የጥናት ቡድን ወደ ዝቋላ ገዳም የላከ መሆኑን አውስተው ከገዳማውያኑ ጋር በመወያየት በሚወሰነው አቅጣጫ መሠረት ወደ ተግባሩ እንደሚገባ አስረድተዋል።

በዋነኝነት በፔይፓል አማካይነት በኢንተርኔት ክፍያቸውን ለፈፀሙ በጎ አድራጊዎች በሙሉ ባንኩ ከሚሰጣቸው የማረጋገጫ ቁጥር በተጨማሪ በኢ-ሜይል አድራሻቸው ለሁሉም “እናመሰግናለን፤ ልገሳችሁ ደርሶናል” የሚል ደብዳቤ መላኩን በኃላፊዎቹ ተጠቅሷል። ደብዳቤው በኢ-ሜይላቸው ያልደረሳቸው ካሉም “spam” ከሚለው የኢ-ሜይሎች ማጠራቀሚያ ክፍል እንዲመለከቱ፣ ደብዳቤው እንዳልደረሳቸው በስልክ ያሳሰቡ አንዳንድ ለጋሾች በዚህ ማሳሰቢያ መሠረት ደብዳቤያቸውን ከኢ-ሜይላቸው “spam” ውስጥ ማግኘታቸው ተጠቅሷል።

በተያያዘም “በፔይፓል መክፈል ላልተመቻቸው ወገኖች እንዲሆን ተደጋጋሚ በቀረበው ጥሪ መሠረት Bank of America 003938182709/ Routing: 054001204 ብላችሁ የድርሻችሁን መወጣት የምትችሉ መሆኑን ወይም ቼክ መላክ ለምትፈልጉ ደግሞ በፖስታ አድራሻችን መላክ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ገንዘቡ እንደደረሰን ምላሽ የምንሰጣችሁ መሆኑን እናስታውቃለን” በተባለው መሠረት በቼክ እና በተመሳሳይ ሁናቴ ለለገሱትም እንደ ፔይፓሉ ሁሉ የገንዘብ ልገሳው እንደደረሰ በደብዳቤ እንደሚያሳውቁ ኃላፊዎቹ ገልጸዋል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር


ለበለጠ መረጃ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ተጠቀሙ፦

240 899 5215  (ማኅበረ ቅዱሳን)
425 922 7182  (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት)
323 348 0820 (ማኅበረ በዓለ ወልድ)

በፔይፓል በኢንተርኔት ለምትለግሱ፦

http://zekuala.mahiberekidusan.org/
http://www.eotc-nassu.org/

ወይም በቀጥታ በባንክ መለገስ ለምትፈልጉ፦

Bank of America 003938182709/ Routing: 054001204

የፖስታ አድራሻ፦

Mahibere Kidusan

8115 Fenton St. Suite 302,
Silver Spring MD 20910


Written By: admin
Date Posted: 3/28/2012
Number of Views: 6771

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement