የማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ ማዕከል የትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል በየዓመቱ ነሐሴ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የፍልሰታ ጾም በሊቃውንተ ቤ/ክን አባቶች አማካኝነት የእመቤታችንን ውዳሴና ቅዳሴ ትርጓሜ ሲያቀርብ ቆይቷል። ዘንድሮም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከዋዜማው ማክሰኞ ሐምሌ 30 2005 ዓም አንስቶ ይጀምራል።
ስለዚህ እርስዎም በሰዓቱ በስልክ ጉባኤው ላይ በመሳተፍ ነፍስዎን ቃለ እግዚአብሔር ይመግቡዋት፡ ከወላዲተ አምላክ ውዳሴና ቅዳሴ ይሳተፉ፡ ስለሀገር፡ ወገንና ስለቅድስት ቤ/ክንዎ በጋራ ይጸልዩ። ሌሎች ወንድሞችና እህቶችም እንዲገኙ ይጋብዙ።
ቀናት፡ ከማክሰኞ ሐምሌ 30 - ረቡዕ ነሐሴ 15 ቀን 2005 ዓ.ም/ August 6-21, 2013
ሰዓት፡ ከምሽቱ 9:00 PM - 10:00 PM PST(ሲያትል ሰዓት)
12፡00AM - 1:00AM EST (ዲሲ ሰዓት)
የኮንፈረንስ ቁጥር፦ 1-559-726-1200 መግቢያ ኮድ፦ 24-81-12
ማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ ማዕከል የትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎትክፍል
ወስብሐት ለእግዚአብሔር