View in English alphabet 
 | Friday, March 29, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
  

Tewahedo የiPhone አፕ

Tewahedo የiPhone አፕ

ተዋሕዶ (Tewahedo) የተሰኘ የስልክ አፕ በማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ አይቲ ክፍል ተዘጋጅቶ ቀረበ:: ይህ የቤተክርስቲያን አገልግሎት ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን የቤተክርስቲያኒቷ ልጆች ሊያበረክቱ ለሚችሉት አገልግሎት ፋና ወጊ እንደሚሆን የታመንበት አፕ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች በጥቂቱ:-

 

1.     የኢትዮጵያ እና የጎርጎሮሳዊያንን አቆጣጠር አጣምሮ የያዘ የዘመን መቁጠሪያ:: የፈለጉትን ዓመት የበዓላት እና አጽዋማት ቀናት በቀላሉ ማየት ያስችላል:: የየቀናቱን የቅዳሴ ምንባብ በመጽሐፈ ግጻዌ መሠረት ያሳያል::

 

2.     በመቶዎች የሚቆጠሩ የቤተክርስቲያኒቱን ስርዓት የጠበቁ መዝሙራት፣ ስብከቶች፣ ትረካዎች እና የሬዲዮ ስርጭቶች ለአድማጭ እንዲመቹ በዓይነት ከፋፍሎ ያቀርባል:: አፑን በመጠቀም የቤተክርስቲያንን ድምጽ በየትኛውም ጊዜና ቦታ (በመንገድ ላይ፣ ሥራዎትን እያከናወኑ፣ በእረፍትና በመዝናኛ ስፍራ) ሆነው ከስልክዎ ሊያዳምጡበት ይችላሉ!

3.     በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናትን መርጃ ያሳያል:: ከፈለጉም ወደ ቤተ ክርስቲያናቱ የሚውስድ አቅጣጫ ይሰጥወታል!

የiPhone/iPod/iPad ተጠቃሚዎች አሁኑን ወደ አፕስቶር (App Store) በመግባት “tewahedo” ብለው ቢፈልጉ አፑን በነጻ መጫን ይችላሉ። ሥራው የመጀመሪያ በመሆኑ ጉድለቶችን በመጠቆም ይርዱን። የAndroid አቻዎን በቅርቡ እናቀርባለን::

 


Written By: admin
Date Posted: 10/24/2013
Number of Views: 6698

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement