View in English alphabet 
 | Thursday, March 28, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
  

የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ሥርጭት በሰሜን አሜሪካ ግዛቶች እያደገ መሆኑ ተገለጸ

በኢቢኤስ /EBS/ በመሠራጨት ላይ የሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን መርሐ ግብር በሰሜን አሜሪካ በሚገኙ ሦስት ግዛቶች በቦስተን፤ በካምብሪጅ እና ሲያትል ይተላለፍ የነበረውን ሥርጭት በማሳደግ አራተኛውንና አምስተኛውን ሥርጭት በመንትያ ከተሞች /twin cites/ በሚናፖሊስ እና ሴንት ፖል ግዛቶች የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ሥርጭት መጀመሩን የማኅበሩ የኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ዋና ክፍል ሓላፊ ዲያቆን ዶክተር መርሻ አለኸኝ ገለጹ፡፡

እንደ ዲያቆን ዶክተር መርሻ ገለጻ ዋና ክፍሉ ለአሜሪካ ማእከል በሰጠው አቅጣጫ መሠረት ከቤተ ክርስቲያን መዋቅር ጋር በመቀናጀት ሥርጭቱ በሁሉም ግዛቶች እንዲያድግና ተግባራዊ እንዲሆን የማእከሉ አባላት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፤ ዝግጅቶቹን ለማሰራጨት የግዛቶቹ ባለሥልጣናት ስቱዲዮ በመስጠት ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡


በአሁኑ ወቅት በኢቢኤስ የሚተላለፈው የማኅበሩ የቴሌቪዥን ሥርጭት ከአንድ ሰዓት በላይ ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ሲሆን፤ ከዚህ በተጨማሪም የኢንተርኔት ቴሌቪዥን መርሐ ግብር ለመጀመር ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ እንደሚገኙም ዲያቆን ዶክተር መርሻ ገልጸዋል::


Written By: host
Date Posted: 2/26/2015
Number of Views: 6839

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement