View in English alphabet 
 | Saturday, April 20, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
  

በአሜሪካ ማዕከል በተለያዩ ከተሞች ዓውደ ርእይና ሐዊረ ሕይወት ተካሄዱ።

«መጭው ዘመን እንዳይቀድመን እንነሳ» በሚል መሪ ቃል በኢ///ቤተ/ክን የማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከል የችካጎ ንዑስ ማዕከል በችካጎ ከተማ  እንዲሁም የዳላስ ንዑስ ማዕከል በሂውስተን ከተማ የአብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎችና በርካታ ምእመናን በተገኙበት ለእይታ ቀርቧል። በሂውስተን ከመስከረም 28 እስከ 29 ቀን /2009 ዓ.ም (October 1-2/2016) የቀረበ ሲሆን በችካጎ ደግሞ ከጥቅምት 19 እስከ 20 ቀን /2009 ዓ.ም (October 29-30/2016)።

ዐውደ ርዕዩ  በሰባት  አበይት ትዕይንቶች የቀረበ ሲሆን፤ -የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሠረተ እምነት ጀምሮ ፤ የቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮ እና ቤተ/ክ ለኢትዮጵያ እና ለአለም የበረከተችው አስተዋጾ እንዲሁም በሦስተኛው ሺህ አመት ልተገብራቸው ከሚገቡ ዋና ዋና መግለጫዎች የቀረቡ ሲሆን፡ በአሜርካ ሃገር ተወልደው ላደጉ እና ለሌሎች ማህበረስብ በእንግሊዘኛ ሙሉ ዐውደ ርዕይ ቀርቧል። በዚህ ዓውደ ርእይ የሕፃናት ትዕይንትም የተካተተበት ሲሆን በችካጎ ን/ማዕከል በተዘጋጀው ዐውደ ርእይ ህፃናት ባደጉበት ቋንቋ ያቀረቡበት ትእይንት የህዝቡን ትኩረት ስቧል።

በሁለቱም ከተሞች በዐውደ ርዕዩ ከታደሙ ምእመናን መካከልም አስተያየታቸውን ሲገልጹ ብዙ ቁም ነገር መጨበጣቸውን ጠቅሰው የተሰማቸውን ደስታ በዕንባም ጭምር ገልጸዋል። አክለውም ማኅበሩ እንደዚህ ዓይነት አስተማሪነት ያላቸውን መርሃ ግብራት ደጋግሞ እንዲያቀርብ አሳስበው ለዚህም የሚያስፈልገውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በተያያዘ ዜና የዲሲ እና የቨርጂኒያ /ማዕከል በጋራ መስከረም 21 ቀን 2009 ዓ.ም እንዲሁም የችካጎ ን/ማዕከል መሰከረም 14 ቀን 2009 ዓ.ም በርካታ ካህናትና ምእምናን የተሳተፉበት የሐዊረ ሕይወት የጉዞ መርሐ ግብር አድርገዋል። በዚህ መርሐ ግብር የምእመናንን መንፈሳዊና ማኅበራዊ ሕይወት የሚዳስሱ ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን ከምእመናን ለተነሱ መንፈሳዊና ሃይማኖታዊ ጥያቄዎች በመምህራን ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል። በተጨማሪም ማኅበረ ቅዱሳን በሀገር ቤት እየሰጠ ስላለው መንፈሳዊ አገልግሎት ሰፊ ገለጻ የተሰጠ ሲሆን በተለይም በችካጎ ን/ማ በተደረገው መረሃ ግብር ላይ በጠረፋማና ስብከተ ወንጌል ባልተስፋፋባቸው አህጉረ ስብከት እያከናወነ ስላለው የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሐ ግብር የሚገልጽ «መከሩ ብዙ ነው ሠራተኞቹ ግን ጥቂቶች ናቸው» በሚል ርዕስ ዶክመንተሪ ቪዲዮ ለምእመኑ ቀርቧል::


Written By: useducation
Date Posted: 12/1/2016
Number of Views: 7073

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement