View in English alphabet 
 | Friday, April 26, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
  

በአሜሪካ ያሉ ማኅበራት በቃጠሎ የወደመውን ጉባኤ ቤት መልሶ ለማቋቋም ጥሪ አቀረቡ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምዕራብ ጐጃም ሀገረ ስብከት በቋሪት ወረዳ ቤተ ክህነት ልዩ ስሙ ፈንገጣ በሚባል ቀበሌ በጨጎዴ ሐና የተቋቋመው፤ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን ሲያፈራ የኖረውና እስከ አሁን ድረስም ሊቃውንትን የመተካት ተልእኮውን በመወጣት ላይ የሚገኘው የሊቀ ሊቃውንት ያሬድ ሽፈራው የቅኔ ምስክር ጉባኤ ቤት ጥር ፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም ረፋድ ላይ ድንገት በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ምክንያት ሁለት መቶ ሃያ አምስት የደቀ መዛሙርት መኖሪያ ጎጆዎች፣ ልዩ ልዩ መጻሕፍት፣ ምግብ እና አልባሳት በአጠቃላይ ከሰባት መቶ ስልሳ ሦስት ሺሕ አምስት መቶ ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙ ታውቋል፡፡ 

 

እነዚህን ጊዜ የማይሰጡና በእለት ተእለት ኑሯቸው በሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ለመርዳት ፥ጉባኤ ቤቱን ወደ ነበረበት ህልውና ለመመለስ፤ ደቀ መዛሙርቱን ከመበተንና የጉባኤውን ወንበርም ከመታጠፍ ለመታደግ፥ እንዲሁም ይህንን የቅኔ ምስክር ቤት መልሶ በዘላቂነት ለማቋቋም እንዲያስችል በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማእከል ፥ የማኅበረ በዓለወልድ እና በሰ/አሜሪካ የሰ/ት ቤቶች አንድነት ጉባኤ ምእመናንን የሚያሳትፍ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መንገድ አዘጋጅቷል።

 

ምእመናንም ይህንን ድረ-ገጽ ( https://www.gofundme.com/chegoden-enrda ) በመክፈት የገንዘብ ልገሳ እንዲያደርጉ ማኅበራቱ በእግዚአብሔር ስም ጠይቀዋል።


Written By: useducation
Date Posted: 1/19/2017
Number of Views: 2048

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement