View in English alphabet 
 | Saturday, April 20, 2024 ..:: ስብከተ ወንጌል ::.. Register  Login
  

ስለምን ጾምን አንተም አልተመለከትኸንም? (ኢሳ.58:3)

(በቀሲስ ስንታየሁ አባተ)
በኢሳይያስ ዘመን የነበሩ እስራኤላውያን የተናገሩት ቃል ነው:: እስራኤላውያን የሚጾሟቸው ብዙ አጽዋማት ነበሯቸው:: ለምሳሌ ያህልም ብናይ በሳምንት ሁለት ጊዜ በሳምንት ሁለት ቀን ይጾሙ እንደነበር በሉቃስ ወንጌል ምዕ. 18¸12 ላይ ያለው ቃል ያስረዳል:: ማክሰኞና ሐሙስ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ወደ ደብረ ሲና የወጣበትንና ከዚያ የወረደበትን ዕለት ለማሰብ እስራኤላውያን በሳምንት ሁለት ቀኖች ይጾሙ ነበR:: በነቢዩ በዘካርያስ ትንቢትም ላይ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን እንዲህ ብሎ አዝዟቸዋል::"የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአስረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሀሴትም በዓላት ይሆናል ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ወደዱ" ተብሎ ለእስራኤላውያን ከእግዚአብሔር ዘንድ በነቢዩ በኩል በተነገራቸው መሠረት የተጠቀሱትን ይጾሙ ነበረ:: ዘካ. 8 18ና19

በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈውን የእስራኤል ዘይቻ ታሪክ በምናይበት ሰዓት ብዙውን ጊዜ ሲጾሙ ብዙውን ጊዜ ሲጸልዩ በጾም ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ በጾም ችግራቸውንና ሐዘናቸውን ለእግዚአብሔር ለመግለጽ በጾም የልቡናቸውን መሻት ከእግዚአብሔር ዘንድ ለመቀበል ነበረ::

እኒህን ሁሉ አጽዋማት ጊዜያቱን ጠብቀው ቢጾሙም እግዚአብሔር በምህረት ዓይኖቹ አላያቸውም መራብ መጠማታቸውንም አልቆጠረላቸውም ስለዚህ በርዕሳችን እንደጠቀስነው "ስለምን ጾምን አንተም አልተመለከትኸንም ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን አንተም አላወቅህም” በማለት እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ዘንድ ምሬታቸውን ሲያቀርቡ እንመለከታለን:: እስራኤል ጾመዋል ደክመዋል ራሳቸውንም አዋርደዋል ሰውነታቸውንም አጎሳቁለዋል ይሁን እንጂ የልቡናቸው መሻት ስለአልተፈጸመላቸው የጾማቸው ዓላማ ግቡን ስለአልመታ ፍሬም ስላላፈራላቸው ወደ እግዚአብሔር ወደ አባታቸው ወደ እግዚአብሔር ወደ አምላካቸው ተመልሰው "ስለምን ጾምን አንተም አልተመለከትኸንም" ብለው እንደጠየቁት እናያለን::

ስለምን እግዚአብሔር አልተመለከታቸውም በእውነት አንዳንድ የዋሀን እንደሚያስቡት ጾም ፈቃደ እግዚአብሔር ሳይሆን ቀርቶ ነውንሕ እግዚአብሔር ጾምን የማይቀበል ሆኖ ነውንሕ አይደለም::

በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጠቀሰው ጾም ፈቃደ እግዚአብሔር ነው:: የሰው ልጆች እንዲጾሙ በጾምና በጸሎት ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርቡ የእግዚአብሔርፈቃድ ነው::ጾም ፈቃደ እግዚአብሔር ብቻም ሳይሆን ለሰው ልጆች ከእግዚአብሔር ዘንድ ከተሰጡት ትእዛዛት -ሕግጋት) መካከል የመጀመሪያው -ቀዳሜ) ትእዛዛት መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል:: ዘፍ 2፡16-17

እግኢአብሔር ለአዳም ሁሉን ይገዛ ዘንድ በሁሉ ላይ ባለሥልጣን ገዥ ንጉሥ እንዲሆን አድርጎታል:: ነገር ግን አዳምን ዓይኑ የተመለከተውን ሰውነቱ የፈቀደውን ሁሉ ያደርግ ዘንድ አላሰናበተውም:: ለዚህ ነው ሥርዓተ ጾምን /ሕገ ጾምን/ የሚሠራለ:: እግዚአብሔር አዳም እንዳይበላ የከለከለውን ዕፀ በለስን በምናይበት ሰዓት ለአዳም እንዲበላ ከተሰጡት ዕፅዋት መካከል ተለይታ ለዓይን የምታስጎመጅ ለጥበብም መልካም ሆና የተገኘች ነበረC:: ጾም አብልጠን የምንወደውን የሚያምረንና ለሰውነታችን እርካታና ምቾት የሚያስገኘውን ሁሉ ለተወሰኑ ጊዜያት ወይም በዘላቂነት መተውን የሚመለከት መልካም የሆነ ደገኛ የሆነ የሃይማኖት ሥርዓት ነው::

ጾም ከጥሉላት ምግቦች ወይም ከእንስሳት ተዋጽኦ ራስን ገትቶ መቆየት ብቻ አይደለም:: ይልቁንም ጾም የመላ ሕዋሳት ተግባር ነው::ጾም በዚህ ምክንያት መላ ሰውነትን ለእግዚአብሔር ማደሪያነት ቀድሶ ማቅረቢያ ነው:: እስራኤል ከዚህ ስላጎደሉ ነው እግዚአብሔር በነቢዩ በኢሳይያስ አድሮ "በውኑ እኔ የመረጥሁት ጾም ይኽ ነውን?" በማለት ለእስራኤል ጥያቄ መልስ የሰጣቸው::

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ያለዘርዓ ብእሲ በፍጹም ድንግልና ከተወለደ በኋላ ብርሃነ ክብሩን በገለጠበት በደብረ ታቦር ተራራ ከቅዱስን አበው መካከል የተመረጡ ሰዎች በዚያ ተገኘተው ነበR:: ሊቀ ነቢያት ሙሴ እንዲሁም ነቢዩ ኤልያስ በዚያ የክርስቶስ ክብር ብርሃነ መለኮቱ በተገለጠበት ተራራ ላይ ቆመው እናያቸዋለን:: ይህን ሰማያዊ ክብር ለማየት የታደሉት እኒህ አበው በዘመናቸው 40 ቀንና ሌሊት ጾመዋል:: በጾማቸውም በረከትን ተቀብለዋል:: ሊቀ ነቢያት ሙሴ በመጾሙ እስራኤል የሚመሩበትን ሕገ ኦሪት ሠርቶላቸዋል ሕዝበ እስራኤል የሚባረኩበትን ጽላት ተቀብሏል:: ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስም ፈራሽ ሆኖ ሳለ በመጾሙ በመጸለዩ ለእግዚአብሔርም ክብር በመቅናቱ ሰማየ ሰማያት እንዳረገ ቅዱሳት መጻሕፍት ይነግሩናል:: ዘፍ 5 ቅዱሳኑ በዘመናቸው በፈጸሙት መልካም ጾም የጌታችንን መለኮታዊ ክብር ለማየት በቅተዋል::ጾም በአግባቡ ቢጾሙትእግዚአብሔር እንደሚፈቅደው ሆነው ከተገኙ እግዚአብሔር ጾምን የሚቀበል ሐዘንን ከልቡና የሚያርቅ እንባን ከዐይን የሚያብስ መሆኑን እናያለN::

ጾም እንዲህ ያለ ታላቅ ዋጋ የሚያሰጥ ቢሆንም እስራኤል ግን ጾመው ያገኙት ጥቅም አልነበረምና "ስለምን ጾምን" በማለት እግዚአብሔርን ይጠይቁታል::

ምክንያቱም ጾማቸው የጎደለው ኖሮ ነው ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርባቸው ከእግዚአብሔር ሊያስታርቃቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ምህረት ቸርነትን ሊያመጣላቸው ያልቻለውና " ስለምን ጾምን" ብለው መጠየቃቸው አግባብ ነው::

በኢትዮጵያ ያኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ከዓመቱ ቀናት መካከል ከ235 ቀናት በላይ እንጾማለን:: ይሁን እንጂ እንደ እስራኤል ዘሥጋ ሁሉ "ስለምን ጾምን?" የሚያሰኙ ሁኔታዎች አሉን:: የበዛውን የዓመቱን ጊዜ በጾም አሳልፈናል በውኑ እግዚአብሔር ጾማችንን ተቀብሎአልን? ተመልክቶስ ቤታችንንና ሥራችንን፣ ልጆቻችንንና ሀብታችንን ባርኮአልን? ካልሆነስ ለምን? የጾምንበት ዓላማ ግቡን መምታቱንና አለመምታቱን ካየን በኋላ ለምን በሚል ጥያቄ አምላካችንን እንድናማርር መልካም ደገኛ የሆነውን ሥርዓተ ጾም ይዞ በእግዚአብሔር ፊት ራሱን የሚያዋርድ ሰው ሁሉ አጽዋጿሙ በእግዚአብሔር ፊት ምን እንደሚመስል ራሱን ሊጠይቅ ሕይወቱን ልቡናውን ሊመረምር ይገባል::

በሀገራችን በቤተ ክርስቲያናችንና በቤታችን ውስጥ ዛሬ እንደምናየው መከፋፈልና መለያየት፣ ረሃብና ድርቅ፣ በሽታና ስደት ነግሰው ዕለት ዕለት የምእመናንን ልቡና በትካዜ ተውጠው እናያቸዋለን:: በየቀኑ ከምትወጣዋ ፀሐይ ጀርባ መልካም ዕለትን ከመናፈቅ ይልቅ እያንዳንዱ ዕለት ምን ዓይነት መከራ ያመጣብን ይሆን? እያሉ የሚሰጉ ወገኖቻችን ብዙ ናቸው:: የዚህ ሁሉ መንስኤው እንደ እስራኤል ሁሉ መንፈሳዊነት የጎደለው ጾም ስለሆነ ነው:: የብዙዎቻችን ጾምእግዚአብሔር እንደሚፈልገው ሆኖ አለመገኘቱ ነው::

ከላይ እንዳየነው እስራኤላውያን በዓመት ውስጥ አራት ወራትን በሣምንት ሁለት ቀናትን ቢጾሙም ጾማቸው መንፈሳዊነት የጎደለው ነበር:: እስራኤል ሲጾሙ የሰዓቱን እርዝማኔ እንጂ በዚያ በረዘመው ሰዓት ውስጥ ምን እያደረጉ እንደሆነ አያውቁም ምን ማድረግ እንደነበረባቸውም አያስተውሉም ነበር:: ይህ ሁኔታ ዛሬ በምንጾመው ጾም ውስጥ የሚታይ ነው::
 
እስከ ስድስት እስከ ዘጠኝ እስከ አስራ ሁለት ሰዓት እየቆየን እንጾማለን እንጂ በዓመቱ ያሉትን ሰባት ዓበይት የዐዋጅ አጽዋማት ዛሬ ደግሞ በግልና በፈቃድ የምንጾማቸውን የጶጉሜንና የጽጌን ጾም ጨምሮ መጾማችንን እንጂ በአጽዋማቱ ወራት ወቅትና ዕለት እንደ ምእመን አንድ የእግዚአብሔር ሰው ሊያደርገው የሚገባውን ነገር እያደረግን ነው ወይ? የሚለውን ነገር አናስተውለውም:: የሚታየን መዋላችን ከምግብ መከልከላችንና ራሳችንን ማድከማችን እንጂ በነዚያ ሰዓታት ውስጥ በትሕትና ከወገኖቻችን ጋር በሰላምና በፍቅር መሄድ አለመሄዳችንን ስለማናስተውለው መንፈሳዊነት ይጎድለናል::

ከዚህ በተጨማሪ እስራኤላውያን ሲጾሙ ጥልና ክርክር ግፍ ማድረግን ከልቡናቸው አላራቁትም ነበር:: ይጾማሉ በሚጾሙበት ሰዓት ግን ይጣሉ ነበር:: ይጾማሉ በሚጾሙበት ሰዓት እርስ በርሳቸው ይከራከሩ ነበር:: ይጾማሉ በተለይ በሚጾሙበት ወቅት በሠራተኞቻቸው ላይ ግፍ ያደርጉ የሠራተኞቻቸውን ደመወዝ ያስቀሩ በግፍ ይበዘብዟቸው ያስጨንቋቸው ያስመርሯቸው ስለ ነበረ ይሄ ጾማቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ያቀርባቸው ዘንድ አልቻለም:: እስራኤል "ለምን አልሰማኸንም" በማለት ከእግዚአብሔር ጋር በተዋቀሱ ጊዜ እግዚአብሔር በነቢዩ በኢሳይያስ አድሮ እንዲህ ይመልስላቸዋል "በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ ሠራተኞቻችሁን ሁሉ ታስጨንቃላችሁ እነሆ ለጠብና ለክርክር ትጾማላችሁ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ ድምጻችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እንደምትጾሙት ጾም አትጾሙም" በማለት እግዚአብሔር ወቅሷቸዋል::

ጾም የምንጣላበት ሳይሆን ሰላምን የምናደርግበት ነው:: ጾም የምንከራከርበት ጊዜ ሳይሆን አንድ የምንሆንበት ጊዜ ነው:: ጾም ግፍን የምናደርግበት ሳይሆን የግፍን ማሰሪያ የምንበጥስበት ከክፉ አድራጊነት ወደ በጎነት የምንሸጋገርበት ጊዜ ነው:: ይሄን ሳያገናዛቡ መጾም ጾማችንና መንፈሳዊነት የጎደለው ያደርገዋል::

ከዚህ በተጨማሪ እስራኤላውያን ሲጾሙ ለወገኖቻቸው ምሕረትን አላደረጉም ነበር:: ጾም ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረት የምንለምንበት ምሕረትን የምንጠይቅበት ጊዜ ነው:: እግዚአብሔር ዓይነ ምሕረቱን ወደኛ እንዲመልስ እዝነ ልቡናውን ወደ እኛ እንዲያዘነብል የማያልቀውን የቸርነቱን ሥራ እንዲሠራልን የምንጠይቅበት ጊዜ ነው::

ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረትንና ይቅርታን እንደምንፈልግ ሁሉ እኛም በጾማችን ወቅት ከሌላው ጊዜ በበለጠ ሁኔታ ለወገኖቻችን ምሕረትን ልናደርግ ይገባናል:: ምሕረትን ማድረግ ስንል ሁለት ነገሮችን ያጠቃልላል እነዚህም ምሕረት ሥጋዊና ምሕረት መንፈሳዊ ናቸው::

ምሕረት ሥጋዋ፤ ለአንድ ሰው በሥጋ የሚያስፈልገውን ነገር ማሟላት ነው:: ቀዶ ማልበስ ቆርሶ ማጉረስ ወዘተ ነው:: የጎደለውን አይቶ መሙላት በተለይ በጾማችን ወቅት ከሌላው ወቅት በተለየ ሁኔታ ለሌሎች ምሕረት ማድረግ ይገባናል::

ምሕረት መንፈሳዊ፤ ማለትም አንድ ሰው ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብበትን ወደ እግዚአብሔር ሊቀርብ የሚችልበትን ሁኔታ ማመቻቸት:: በእርሱናበእግዚአብሔር መካከል የአባትና የልጅ ግንኙነት እንዲኖር ማድረግ፣ ኃጢአት ሠርቶ ከእግዚአብሔር የራቀውን በትምህርት በምክር በተግሳጽ ወደእግዚአብሔር ማቅረብ ነW:: ከባልንጀራው ጋር ተጣልቶ እግዚአብሔርን ያስቀየመውን በመካከላቸው እርቅ እንዲኖር ማድረግ በአጠቃላይ መንፈሳዊ ሕይወቱ እንዳይጎሰቁል እንደይደክምና ከጽድቅ እንዳይጎድል መርዳት ነው::

እንደ እስራኤል ሁሉ ከምሕረት የራቀ ጾም ይዘን እንደሆነ መልስ የማያስገኝ በመሆኑ በምንጾምበት ሰዓት ለወገኖቻችን ምሕረት ማድረግን የጾማችን ክፍል ልናደርግ ይገባል::

"እኔስ የመረጥሁት ይህ አይደለምን? የበደልን እሥራት ትፈቱ ዘንድ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ የተገፉትንስ አርነት ትሰዱ ዘንድ ቀንበርስ ሁሉ ትሰቅሉ ዘንድ አይደለምን እንጀራህንስ ለተራበ ትቆርስ ዘንድ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤት ታገባ ዘንድ የተራቆተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን? የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል ፈውስህ ፈጥኖ ይበቅላል ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል እግዚአብሔርም ይሰማሀል::የእግዚአብሔርም ክብር ከኋላህ ሆኖ ይጠብቅሀል የዚያን ጊዜ ትበራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል::” /ኢሳ58፤6-8/ ተብሎ የተነገረው ቃል በጾማችን ወቅት ምህረት ማደረግ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ያሳየናል::

እስራኤል ሲጾሙ ሥጋቸውን ከማስራብ በስተቀር ነፍሳቸውን በንስሐና በቃለ እግዚአብሔር አይመግቧትም ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት እንደእግዚአብሔር ቃል የጾም ትልቁ ዓላማ ሥጋን ማስራብ ደይሆን ነፍስን በበጎ ነገር ማርካት ነፍስን በበጎ ነገር ማጥገብን የግድ የሚመለከት ነገር ነው::

ጌታችን አርአያና ምሳሌ የሆነበት ዐቢይ ጾም ፈታኝ ወደእርሱ ቀርቦ እንዲመገብ ባዘዘው ጊዜ "ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖኃጋ ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ጭምር እንጂ" በማለት እንደመለሰ በማቴ 4፡4 ተጠቅሶ እናገኛለን::
 

በጾማችን ወቅት ምግበ ሥጋ በማጣት የደከመ ሥጋ ብቻ ሳይሆን ቃለ እግዚአብሔርን የጠገበች ነፍስም ልትኖረን ያስፈልጋል:: ያለዚያ ግን ምንም እንኳ ሥጋ ቢደክምም ነፍስ ከተራበች ኃጢአት ይሰለጥንባታል:: በዚህም ምክንያት ጾማችን ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርበን ምህረትና ቸርነትንም ሊያስገኝልን አይችልም::"የተራበች ነፍስ የመረረ ነገር ሁሉ ይጣፍጣታል የጠገበች ነፍስ ግን የማር ወለላን ትረግጣለች" /ምሳ27፤7/ ጽድቅን ቃለ እግዚአብሔርን ንስሐን የተራበች ነፍስ በሁሉም በጎ የሆነውም ፈቃደ እግዚአብሔር በመማር ያላወቀችና ከፈቃደ እግዚአብሔር የራቀች ነፍስ የመረረ ነገር ኃጢአት በደል ክፋት ይጣፍጣታል በኃጢአት በበደል በክፉ ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ፈቃድ ባልሆነ ነገር ሁሉ ታስራ መከራዋን ታያለች በቃለ እግዚአብሔር በፍቅረ እግዚአብሔር በንስሐ በሥጋወደሙ የጠገበች ነፍስ ግንኧ የዚህን ዓለም ተድላ ደስታ ምቾትንቃ ትጠየፈዋለች ከእግዚአብሔር ጋር አንድነቷን ታጠነክራለች::

በቅዱሳት መጽሐፍት ዜና ሕይወታቸው ተዘግቦ የምናገኘው ቅዱሳን ራሳቸችውን አሳልፈው ለሞት እስከ መስጠት ዓለምን ንቀው ወደ በረሓ እስከ መመነን የሚደርሱት ነፍሳቸው በቃለ እግዚአብሔር የጠገበች በመሆኗ ነው::

ሊቀ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ በዱዲያኖስና በሰብአ ነገሥታት ፊት በተጋደለበት ዘመን ዱድያኖስ ቅዱስ ጊዮርጊስን ሊያታልለው ሞክሮ ነበር:: በዚህ ዓለም የብዙዎች ሰዎችን ልቡና የሚያነሆልሉ የሚያታልሉ- ታላላቅ ገፀ በረከቶችን አቅርቦለት ነበር:: ከነዚህም መካከል መኳንንቱና መሳፍንቱ የሚመኟት አንዲት ሴት ልጁን ሊድርለት ቃል መግባቱ ነበር:: የመንግሥቱን እኩሌታም እንደሚሰጠውና ከእርሱ በታች ታላቅ ባለሥልጣን እንደሚያደርገው በሰባ ሀገሮች ላይም እንደሚሾመው ቃል ገብቶለት ነበር:: ይሁን እንጂ ነፍሱን በእግዚአብሔር ቃል ያጠገበ አባት ነበርና ዱድያኖስ ያቀረበለትን ማባበያ ንቆ በሃይማኖት ጸንቶ ተገኝቷል::

እስራኤላውያን በጾማቸው ወቅት ሥጋቸውን ከማስራብ በስተቀር ነፍሳቸውን ያጠገቡበት ሁኔታ አልነበረም:: ነፍሳቸውም ሥጋቸውም የተራበች ነበረች:: ከዚህ የተነሳ ነው እግዚአብሔር ሊጎበኛቸው ሊመለከታቸው ያልቻለው:: ስለዚህ የእኛም ጾም እንዲህ እንዳይሆን በምንጾምበት ጊዜ ጾማችን የግድ ከንስሐ፣ ከሥጋ ወደሙ፣ ከቃለ እግዚአብሔር ጋር አንድነት፣ ሕብረት ያለው ሊሆን ይገባዋል ሥጋን ብቻ አስርቦ ነፍስን የማያጠግባት ጾም መልስ የማያስገኝና የምሬት ጾም ይሆንብናል::

በነቢዩ በኤርምያስ ዘመን የነበሩ እስራኤላውያን የተወቀሱበትን ሁኔታ ስንመለከት አንድ ነገር እንድናስተውል ያደርገናል:: እንዲህ ትላቸዋለህ እግዚአብሔርእንዲህ ይላል የወደቁ አይነሱምን የሳተስ አይመለስምን እንግዲህ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ስለምን ወደ ኋላው ይመለሳል? ተንኮልን ይዟል ሊመለስም ዕንቢ ብሏል::አደመጥሁ ሰማሁም ቅንን ነገር አልተናገሩም ማናቸውም ምን አድርጌአለሁ ብሎ ከክፋቱ ንስሐ የገባ የለM:: ወደ ሰልፍም እንደሚሮጥ ፈረስ እያንዳንዱ በየመንገዱ ይሄዳል ሽመላ በሰማይ ጊዜዋን አውቃለች ዋኖስና ጨረባ ዋልያም የመውጣታቸውን ጊዜ ይጠብቃሉ ሕዝቤ ግን የእግዚአብሔርን ፍርድ አላወቁም ኤር8፤4-7::

እስራኤል በጾማቸው ወራት ወደ እግዚአብሔር የሚያደርሳቸውን ንስሐ አልተጠቀሙበትም ነበርና ነው እግዚአብሔር ያልሰማቸው:: ስለዚህ በጾማችን ወቅት ከመብል መከልከልን ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር ምሕረትና ቸርነት ወደ እኛ እንዳይመጣ ያገደውን ኃጢአት በንስሐ ልናስወግደው ይገባል::

የእስራኤል ጾም በልማድና በግብዝነት የተሞላ ነበር:: ይህ ነው የልቡናቸው መሻት እንዳይፈጸም አንቆ የያዘው:: ጾም ዓላማ ሊኖረው የሚገባ ድርጊት ነW::የሚጾም ሰው በጾሙ አማካኝነት ወደ እግዚአብሔር ሊቀርብ፣ የእግዚአብሔር ምሕረትና ቸርነት እንዲደረግለትና፣ ለልዩ ልዩ ዓላማ ሊጾም፣ የጾሙ ማዕከላዊ ዓላማጋ እግዚአብሔር ክጨጅቃ ይገባል::

ሥርዓቱ ስለተደነገገ ብቻ የሚጾም ጾም ዓላማውን ግብ ማድረስ አይችልም:: ልማዳዊ ብቻ ስለሚሆንም ዋጋ አያስገኝም:: በመጽሐፍ ቅዱስ የጾሙ ሕዝቦችና ግለሰቦችን ታሪክ በምናይበት ጊዜ ለጾማቸው ዓላማ ነበራቸው::

በዘመነ አስቴር የነበሩ አይሁድ ከክፉ ሀማ ምክር ይድኑ ዘንድ፣ የነነዌ ሕዝቦች ከቁጣ እግዚአብሔር ያመልጡ ዘንድ፣ እነ ዳንኤል ምስጢር እንዲገለጥላቸው ጾመዋል:: ዳን10፤3:: ስለዚህ እኛም በምንጾምበት ወቅት እግዚአብሔር በእኛና በእርሱ መካከል ያለውን የአባትነትና የልጅነት መንፈስ እንዲያጠናክርልን፣ ኃጢአታችንን ይቅር እንዲለን፣ ቀሪው የሕይወት ዘመናችንን እንዲባርክልን፣ በጾማችን ወቅት ሀገራችንን እንዲጎበኝልን፣ ቤተ ክርስቲያናችንን እንዲጠብቅልን፣ ለቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሰላምና ፍቅር አንድነትን አድሎ ሕዝቡን በአንድ ልቡና እንዲመሩልን የሚሉ ይህን የመሳሰሉ ዓላማዎች ሊኖሩን ይገባል::

ከዚህ ውጪ በልማድ ብቻ የሚደረግ ጾም ዋጋ የማያስገኝ ከንቱ ነው::ቅዱስ ጳውሎስ &የምታደርጉትን ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አድርጉ በማለት እንዳሳሰበን ጾማችን እግዚአብሔርን ዓላማ ባደረገ ሁኔታ ይህ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛል:: ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረት ቸርነትና በረከትን ያሰጠናል በማለት ሊሆን ይገባL::

እስራኤል ከሌላው ጊዜ የጾማቸውን ወቅት የሚገልጠው *የሚያሳየው- አስቀድመው በፍስክ ወቅት ይበሉት የነበረውን ነገር ትተው የምግብ ለውጥ ማድረጋቸው ብቻ ነው::ሌላ የሕይወት ለውጥ አይተይበትም በቤተ ክርስቲያን ያለን ምእመናንም ጾማችንን በምናይበት ሰዓት ከዚህ የተለየ ሆኖ አናገኘውም ከፍስኩ ወቅት ሥጋና የሥጋ ተዋጽኦዎችን እንመገብ የነበርን ሰዎች በጾማችን ትተነዋል ይሁን እንጂ በእርሱ ፈንታ ሥጋችንን ሊያዳብሩ የሚችሉ ምትክ ምግቦችን ምናልባትም በፍስኩ ወቅት በተሻለ ሁኔታ እንመገባለንዕዕ ያም ሆኖ ከምግብ ከመከልከል ውጪ ሌላ ለውፌ በሕይወታችን አይታይም:: የጾም ወቅት ግን የአስተሳሰብ ለውጥ ልናሳይ የሚገባበት ወቅት ነው::

የጾም ወቅት ከሌሎች ጊዜያት ይልቅ ለአንደበታችን ልጓም የምናበጅበት ወቅት ነው:: ባልንጀራን የሚያሳዝን ሰዎችን የሚያስከብር ዓለማዊ ሕይወትን የሚያደፈርስ በእግዚአብሔር ዘንድ ኃጢአት ሊሆን የሚችል ንግግርን ከአንደበታችን ልናርቅ የሚገባበት ወቅት ነው:: የጾም ወቅት ንግግርን ብቻ አይደለም የአሠራርም ጭምር ለውጥ የምናመጣበት ነው:: አስቀድመን እንሠራቸው የነበሩ የኃጢአት ሥራዎችን ትተን አባቶቻችን ቅዱሳን አበውንና እናቶቻችንን ቅዱሳት አንስትን በቅድስና የምንመስልበት ወቅት ነው:: የጾማችን ወቅት ፈቃደ ሥጋችንን ለፈቀደ ነፍሳችን የምናስገዛበት መልካዊ ባሕሪያችን የሚያይልበት ወቅት ነው:: 1ቆሮ 9፤26-27::

በአጠቃላይ እንደ እስራኤል ዘሥጋ ዓይነት ጾም ጾመን “ስለምን ጾምን አንተም አልተመለከትኸንም” በማለት እንዳናማርር ጾማችን የምሕረትና የቸርነት ፍሬያት የሚገኙበት እንዲሆን የአጿጿማችንን ሁኔታ ልናየው ልንመረምረው ይገባናል::

እግዚአብሔር አምላካችን በነቢዩ በኢዮኤል አድሮ “ጾምን ቀድሰ#” ብሎ እንደ ነገረን ጾማችንን ከአሕዛብ ልማድ፣ ከግብዝነት አካሄድ፣ ለይተን እግዚአብሔርየሚገኝበትና ወድዶ ፈቅዶ የሚቀበለው ጾም ልናደርገው ይገባናል:: ኢዮ 2¿$15:: ለዚህም የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን::

ወስብሐት ለእግዚአብሔር


Written By: host
Date Posted: 2/8/2010
Number of Views: 7634

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement