በትራክት መልክ የተዘጋጀውን መልእክት ለማግኘት እዚህ ይጫኑ
“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ ” ማቴ 28፥19-20
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !
ለተወደዳችሁ የክርስቶስ ቤተሰቦች !
ሠላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን !
ጉዳዩ : ለ10 ዓመቱ የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮጀክት ድጋፍ ስለመጠየቅ
ማኅበራችን ማኅበረ ቅዱሳን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠውን ሓላፊነት ለመወጣት በተለያዩ መንገዶች ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፤ እያደረገም ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን ሁሉንም የቤተክርስቲያን አባላት ባሳተፈ እና ሁሉም ምዕመናን የድርሻቸውን እንዲወጡ በማድረግ ችግሩን ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ፤ ስብከተ ወንጌል አገልግሎት ባልተስፋፋባቸው ገጠርና ጠረፋማ ቦታዎች፤ አኅዛብና መናፍቃን በበዛባቸው አካባቢዎች ወንጌልን ለማዳረስ የአሥር ዓመት የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ማስፋፊያ ኘሮግራም በመቅረጽ በግንቦት 19/2002 ዓ.ም. አገልግሎቱን ጀምሯል፡፡