View in English alphabet 
 | Saturday, December 21, 2024 ..:: ዜናዎች ::.. Register  Login
ዜና

በ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የተገነባው ቤተክርስቲያን ተመረቀ፡፡                   


የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮምሽነርና የካቢኔ ጉዳዮች ጽ/ቤት ሓላፊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን እምነት ተቀብለው ተጠመቁ፡፡ በጋምቤላ ሀገረ ስብከት በአንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የደብረ መድኃኒት ቅድስት ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ተጠናቆ ቅዳሴ ቤቱም ተከብሯል፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ


ዜና

 በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በደብረ ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና በመካነ ጎለጎታ ቅድስት ማርያም ጠበል ሰሞኑን ከአንዲት እኅት ከሆዷ ጥቁር ወፍ ወጣላት፡፡ በክርስትና ስሟ መንበረ ማርያም ተብላ የምትጠራው እኅት ለ20 ዓመታት ያህል በሆድ ሕመማት ስትሰቃይ መቆየቷን የምትናገረው መንበረ ማርያም፤ ስቃይዋን በዘመናዊው ሕክምና ለማስታገስ ያልሔደችበት ቦታና ያልወሰደችው መድኃኒት የለም፡፡ ይሁንና የምትወስደው ሕክምና ለጊዜው ስቃይዋን ከማስታገስ በስተቀር ከሕመሟ ልትድን ባለመቻሏ ከዚህ በኋላ ይግደለኝ እንጂ ሕክም ናም ሆነ መድኃኒት መጠቀም የለብኝም፤ ብላ ጠበል ለመጠመቅ እንደ ወሰነች ትናገራለች፡፡ በውሳኔዋም መሠ ረት ወደ ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ጠበል በመሄድ ስትጠመቅ በላይዋ ላይ የሰፈሩ 681 አጋንንት እንዳሉ በላይዋ ላይ ያደሩት የሰይጣን ሠራዊት ለፍልፎ በጥቁር ወፍ አምሳል ከሆዷ ውስጥ ሊወጣላት ችሏል፡፡ ምእመናን በዕለቱ ከሆዷ ውስጥ በትውከትነት እንደ ጥይት ተወርውሮ የወጣውን ጥቁር ወፍ ከነሕይወቱ በማየት በቪዲዮ በመቅረጽ የእግዚአብሔርን ድንቅ ተአምር እንደ መሰከሩ ተገልጿል፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ


ዜና

በጀርመን ፍራንክፈርት የተካሄደው ዐውደ ርዕይ ተጠናቀቀ
                      በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል መዝሙርና ሥነ ጥበባት ክፍል
 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትላንት ዛሬና ነገ በሚል ርዕስ ከግንቦት 21 እስከ 24 ቀን 2001 ዓ.ም በፍራንክፈርት ከተማ ተዘጋጅቶ የነበረው ዐውደ ርዕይ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ።
በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ጀርመን ቀጠና ማእከል ተዘጋጅቶ በፍራንክፈር ኢኮነን ሙዚየም የቀረበውን ይህንን ዐውደ ርዕይ መርቀው የከፈቱት ብፁዕ አቡነ እንጦንስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው።
  ተጨማሪ ያንብቡ


ዜና

በብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ የሰሜን ምዕራብ አሜሪካ ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሚያዝያ 3 ቀን 2001 ዓ.ም. ተከፍቶ ለ2 ቀናት ለሕዝብ ሲታይ የቆየው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትናንት - ዛሬ - ነገ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ዐውደ ርዕይ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ በማኀበረ ቅዱሳን የሲያትል ቀጣና ማዕከል አስታወቀ፡፡ ብፁዕነታቸው በአውደ ርዕዩ የመዝጊያ ስነሥርዓት ላይ "ያየነው ዝግጅት በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ ተብሎ ለቤተክርስቲያን የተነገረውን ቃለ ትንቢት እየተፈጸመ መሆኑን ያስታውሰናል፡፡" በማለት የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

 

  ተጨማሪ ያንብቡ


ዜና

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተሕዋዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል ልሳነ ተዋሕዶ የተሰኘ መንፈሳዊ የፓልቶክ አገልግሎት ጀመረ።

ማዕከሉ የአዲሱን የፓልቶክ አገልግሎት የሙከራ ስርጭት ከኅዳር ፲፭ እስከ ፳፱ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም. ሲያደርግ  ቆይቶ ታኅሳስ ፩ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም. ምሽት ለሦስት ሰዓታት በቆየ  የመክፈቻ ሥነ ስርዓት መደበኛ ስርጭቱን በይፋ ጀምሯል

  ተጨማሪ ያንብቡ


Page 11 of 13First   Previous   4  5  6  7  8  9  10  [11]  12  13  Next   Last   

Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement