በየዓመቱ በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የሚካሄደው በማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከል ጠቅላላ ጉባኤ በዘንድሮው ዓመትም ለአሥራ ስድስተኛ ጊዜ “አገልግሎትህን ፈጽም” በሚል መሪ ቃል በቺካጎ ኤሊኖይ ተካሄዷል ::
ከግንቦት ፳፬ - ፳፮ ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ለሦስት ቀናት የቆየው ይህ ጉባኤ ዓርብ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 5:00pm በቺካጎ ደብረ ኤዶም ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ካቴድራል በኒውዮርክና አካባቢው ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ዘካርያስ እና በካህናት አባቶች ጸሎተ ኪዳን በማድረስ የመክፈቻ መርሐግብሩ ተከናውኗል:: በማስከተልም ብፁዕነታቸው ቃለምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል:: በመቀጠልም ሕጽበተ እግር እና የእራት መስተንግዶ ከተከናወነ በኋላ እንግዶች ወደየተዘጋጀላቸው ማረፊያ ተጉዘዋል።