ዜና
በሲያትል እና ኣካባቢው ከተሞች የሚኖሩ የ ኢ. ኦ. ተ. ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንን ያሳተፈ ታላቅ የትምህርተ ወንጌል ጉባኤ በሲያትል ከተማ ታህሳስ 16 እና 17 2003 ዓ.ም. ተደረገ:: በጉባኤው ላይ በሲያትል ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የተጋበዙ አባቶች ካህናት ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና ምዕመናን የተገኙ ሲሆን ፤ የኣጥቢያዎቹ ኣብያተ ክርስቲያናት የሰንበት ት/ ቤት መዘምራን መዝሙራትን ኣቅርበዋል።
በሁለት ቀኑ ጉባዔ የአጥቢያው ካህናት እና በተጋባዥነት በተገኙት መላከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል፤ እንዲሁም ሊቀ መዘምር ይልማ የተለያዩ ዝማሬዎችን በማቅረብ ከታዳሚዎቹ ጋር እግዚአብሄርን አመስግነዋል። በጉባኤው ላይ የማህበረ ቅዱሳን ኣገልግሎት በተለይም የ 10 ኣመቱ የስብከተ ወንጌል የኣገልግሎት እቅድ ለታዳሚዎች ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በቀጣይም ይህን እቅድ በተመለከተ ተከታታይ መርሃ ግብሮች እንደሚዘጋጅ ተገልጧል:: ጉባኤውን በማህበረ ቅዱሳን የኣሜሪካ ማዕከል የሲያትል ቀጠና ማዕከል ባካባቢው ከሚገኙ ኣጥቢያ ኣቢያተ ክርስቲያናት ጋር በመቀናጀት እንዳዘጋጀው ታውቋል ::
በእለቱ የተሰጡ ትምህርቶችና ፎቶዎች
ተጨማሪ ያንብቡ
|
ንቁ
ኢትዮጵያ ያላት ክብርና ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ የታሪክ ሰነዶች የተመሰከረ፣ በታላላቅ ማራኪ ቅርሶችም የታጀበ ነው። የነበራት ክብርና ገናናነት ከምዕራብ እስከ ምስራቅ፣ ከሰሜንም እስከ ደቡብ የታወቀ ነው። ከዚህ ጉልህ ታሪክ ውስጥ የበለጠ ጎልቶ የሚታየው ደግሞ የሀገራችን የሃይማኖት ታሪክ ነው። ኢትዮጵያ ከእስራኤል ወገን ቀጥሎ ብሉይ ኪዳንን በመቀበል ቀዳሚ ሀገር ናት። በመሆኑም በዘመነ ብሉይ ሕግና ነቢያትን በመቀበልና በመፈጸም እንዲሁም የተስፋውን ቃል በመጠበቅ ኖራለች። ጊዜው ሲደርስም የሐዋርያትን ስብከት ተቀብላ የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነትና ጌትነት አምና ጥምቀትን ወደ ምድሯ አምጥታለች። በመሆኑም ወንጌልን ተቀብላ አምና ስትሰብክ ኖራለች። አሕዛብ ሕግና ነብያትን በናቁበት ጊዜ ከአሕዛብ ወገን ቀድማ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ኦሪትን በመቀበሏ እንዲሁም ደግሞ እስራኤል ወንጌልን በናቁበት፣ ክርስቶስን በጠሉበት ጊዜ ከአሕዛብ ጋር ሐዲስ ኪዳንን በጊዜው በመቀበሏ ሁለቱንም ኪዳናት በጊዜያቸው ያስተናገደች ብቸኛ ሀገር ናት ማለት ይቻላል። ስለዚህ በዓለምም ሆነ በአፍሪካ መድረክ የሚያስከብር የሃይማኖት ታሪክ ባለቤት ናት። ከዚያም በመነጨ ሊሻሩ ከማይችሉት ከሕግና ከነቢያት እንዲሁም ከክርስቶስ ወንጌል፣ ከሐዋርያት ትምህርት፣ ከሊቃውንቱም ትርጓሜ የመነጨ ሰውንም እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኝ ሥርዓተ አምልኮ ባለቤት ለመሆን አስችሏታል።
ተጨማሪ ያንብቡ
|
ዜና
የሃይማኖት አባቶች የቀድሞ የደርግ ባለሥልጣናትን ወክለው ይቅርታ አቀረቡ። የአራት የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች የቀድሞ የደርግ ባለሥልጣናትን የይቅርታ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት አቀረቡ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሃይማኖት መሪዎች ቅዳሜ ታኅሳስ 9 ቀን 2003 ዓ.ም በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ተገኝተው በሰጡት የጋራ መግለጫ ይህን የታሪክ ጠባሳ በአገራዊ ይቅርታና ዕርቅ መጨረስ ከሁሉ በላይ ታላቅ መንፈሳዊ አንድምታ ይኖረዋል ብለዋል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ጉባኤውን ወክለው ባቀረቡት መግለጫ ላለፉት ሁለት ዓመታት ለጉዳዩ ስኬታማነት ሲሠሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል። ከኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት በሚያገኙት ይሁንታ ታኅሣሥ 21 ቀን 2003 ዓ.ም አጠቃላይ ሀገራዊ እርቅ እንደሚካሄድ ተናግረው፥ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህንኑ መንፈሳዊ ጥሪ ተቀብሎ በጎ ምላሽ እንደሚሰጠን በመተማመን ይህን የሰላምና የዕርቅ ሐሳብን ይዘን ቀርበናል በማለት አስረድተዋል። «ብፁዓን ገባርያነ ሠላም፥ እስመ እሙንቱ ውሉደ እግዚአብሔር ይሰመዩ። የሚያስታርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና» ማቴ 5፥9 ሙሉውን መረጃ እዚህ በመጫን ያንብቡ
|
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
የቤተ ክርስቲያን አባቶች እንዴት ይሾማሉ?
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ካህናት አባቶችን ለአገልግሎት የምትሾምበት ሰማያዊ ሥርዓት አላት፡፡ እነዚህን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ማብራራት የዚህ ጽሑፍ ዓላማ አይደለም፡፡
ጠቅለል ባለ መልኩ ግን በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚሾሙ አባቶች መንጋውን ለመጠበቅ፣ ሕይወታቸውን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ለመስጠት፣ ለመለየት፣ በቤተ ክርስቲያንና በምእመናን ፊት ቃል ይገባሉ፡፡ ቃል ኪዳናቸውም በእግዚአብሔርና በሰማያውያን ፊት መሆኑ ይታወቅ ዘንድ በሰማያዊው መሰዊያ ፊት በአባቶች አንብሮተ እድ ፀጋ መንፈስ ቅዱስን ይቀበላሉ፡፡ በዚህ መልኩ ይህን ሰማያዊ የአገልግሎት ሹመት ይቀበላሉ፡፡
የቤተ ክርስቲያን አባቶች አገልግሎታቸውን በአግባቡ እንዲፈጸሙ ምን ያስፈልጋቸዋል?
ተጨማሪ ያንብቡ
|
ዜና
የማኀበረ ቅዱሳን የኣብነት ት/ቤት ኣገልግሎት ሪፖርታዥ በ VOA
|
|