View in English alphabet 
 | Saturday, December 21, 2024 ..:: ዜናዎች ::.. Register  Login
ዜና

በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል የ15ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 17፣ 2005 /May 25, 2013/ በሚኒሶታ ንዑስ ማዕከል አዘጋጅነት ተጀመረ።
ጉባኤው በጸሎት የተጀመረ ሲሆን፣ ከመክፈቻ ጸሎቱ በኋላ የዲሲ ንዑስ ማዕከል ”እንዘ ይነብር ለአብ በየማኑ ወይረፍቅ ውስተ ህድኑ የማኑ ለአብ“ የሚል ያሬዳዊ ዜማ ካቀረቡ በኋላ መልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው “ናሁ ሰናይ ወናሁ አዳም” በሚል ርእስ ሰፊ ትምህርት ሰጥተዋል። መልአከ ሰላም በሰጡት ሰፊ ትምህርት በረከተ ነፍስ እና በረከተ ሥጋን ለማግኘት ከወንድሞች ጋራ በመከባበር በመፈቃቀር መኖር እንደሚገባ አስረድተዋል። ቃየል ከወንድሙ ጋር መኖር አለመቻሉ እንደጎዳው፣: ዛሬም ከወንድሞች ጋር ስንኖር መቻቻል፣ መበረታት እንደሚገባ፣ በፍፁም ትህትና መኖር እንዲሁም የወንድምን ወይንም የባልንጀራን ጥቅም ማስቀደም እንደሚገባ ሰፊ ትምህርት ሰጥተዋል።
  


ዜና

በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል “በእንተ ስማ ለማርያም” (ስለ እመቤታችን ማርያም ! ) በሚል መሪ ቃል ያሰናዳው በአብነት ትምህርት ቤቶች ዙሪያ ላይ ያተኮረው ብዙኃን የቤተክርስቲያን ልጆች የተሳተፉበት ዐውደ ርዕይ በሲያትል ንዑስ ማዕከል አዘጋጅነት መጋቢት 7 እና መጋቢት 8 2005 ዓ/ም በሲያትል የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ለሕዝብ እይታ ቀርቧል::  

ዐውደ ርዕዩ ቅዳሜ መጋቢት 7 2005 ዓ/ም በሲያትልና በአቅራቢያው ካሉ ከተሞች በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፣ የሰባካ ጉባኤ አባላት፣ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው  እንግዶች በተገኙበት ደመቅ ባለ ሥነ ሥርዓት ተከፍቷል::
በዚሁ ወቅት  በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል  መልእክት በዲ/ ተገኔ ተክሉ  የቀረበ ሲሆን በመክፈቻው ላይ በተገኙ ካህናትና ተጋባዥ እንግዶች የተለያየ አስተያየት ተሰጥቷል።
ለሁለት ቀን ክፍት ሆኖ የቆየውን ዐውደ ርዕይ  ከ300 በላይ ምእመናን የተመለከቱት ሲሆን ከተሰበሰበውን አስተያየት  የብዙኃኑን ስሜት የነካ እንደነበረ ለመረዳት ተችሏል። ዓውደ ርእዩን የተመለከቱ ምእመናን በዕለቱ ቀረበው ከነበሩት ፕሮጀክቶችን  መካከል እየመረጡ የወሰዱ ሲሆን በኦንላይን በተዘጋጀው የልገሳ ድረ ገጽ (http://www.gedamat.org)  ላይ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

  ተጨማሪ ያንብቡ


ዜና

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተከርስቲያንማኅበረ ቅዱሣን የአሜሪካ ማዕከል፣ በሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ እና  በሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከት በዓለ ወልድ ማኅበር በሲያትል ከሚገኙት አራት ቤተክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ጋር በመተባበር በሲያትል እና አካባቢዋ የሚገኙ ካህናት አባቶች እና ምዕመናን ያሳተፈ የሁለት ቀን የትምህርት እና የውይይት ጉባኤ አካሄዱ።

  ተጨማሪ ያንብቡ


ዜና

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ማኅበረ ቅዱሳን ከጥቅምት 4 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በየሳምንቱ እሑድ ጧት ከ3፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት የሚቆይ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ብሮድ ካስቲንግ ሰርቪስ ቴሌቪዠን (EBS TV) ለመጀመር ሙሉ ዝግጅት ማጠናቀቁ ተገለጠ፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ


ዜና

ቅዱስ ሲኖዶስ ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ ወሰነ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ነሐሴ 30/2004 ዓ.ም. ለመገናኛ ብዙኅን በሰጠው መግለጫ ከጳጉሜ 1 ቀን 2004 ዓ.ም. እስከ መስከረም 10/2005 ዓ.ም. ድረስ ምእመናን ለሁለት ሱባኤያት በመላዋ ኢትዮጵያና በውጭ ሀገር በሚገኙ አህጉረ ስብከቶች በሚገኙ ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት  ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ ወስኗል፡፡


ቅዱስ ሲኖዶስ ጸሎተ ምኅላውን ያወጀበት ምክንያት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በነበሩበት ዘመን በሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ  ሰፊ ሥራ የሠሩ አባት እንደነበሩ ጠቅሶ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ፤ ለሀገሪቱ ሰላምና አንድነት የሚበጅ ተተኪ አባት(ፓትርያርክ) እግዚአብሔር ባወቀ መርጦ እንዲያስቀምጥ ካህናትና ምእመናን  በጸሎተ ምኅላው እንዲሳተፉ አሳስቧል፡፡

ምንጭ፦ http://www.eotc-mkidusan.org/site/
  


Page 4 of 13First   Previous   1  2  3  [4]  5  6  7  8  9  10  Next   Last   

Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement