View in English alphabet 
 | Saturday, December 21, 2024 ..:: ዜናዎች ::.. Register  Login
ዜና

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የሚገኘው የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ደን በመቃጠሉ መነሾ በሰሜን አሜሪካ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት ሦስቱ ማኅበራት ማለትም በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል፣ በሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ እና ማኅበረ በዓለ ወልድ ባደረጉት ጥሪ እጅግ አስደሳች ምላሽ መገኘቱን በዚህም እስካሁን በጠቅላላው $24,206.52 ዶላር መዋጣቱን የማኅበራቱ ኃላፊዎች ገለፁ።

  ተጨማሪ ያንብቡ


ዜና

በዝቋላ እየተካሄደ ላለው የእሳት ማጥፋት እንቅስቃሴ ርዳታ በማድረግ ላይ ላላችሁ በሙሉ

Zekuala Fireማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል፣ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ እና ማኅበረ በዓለ ወልድ በአንድነት እያስተባበሩት ባሉት እና ዓላማው በአሁኑ ወቅት እሳቱን ለማጥፋት ከየአካባቢው በነቂስ ለወጣው ኢትዮጵያዊ ወገናችን ጉሮሮውን ማርጠቢያ ውኃ፣ ጉልበቱን መደገፊያ ዳቦ ማቅረቢያ እንዲሆን እንዲሁም በገዳሙ ጥሪታቸውን አሟጠው እንግዶቻቸው እሳት ተከላካዮችን  በማስተናገድ  ላሉት ገዳማውያን ርዳታ ማድረግ በሆነው ታላቅ እንቅስቃሴ እስካሁን በፔይፓል (http://zekuala.mahiberekidusan.org/) አካውንታችን (ይህ ጽሑፍ በተዘጋጀበት ወቅት) ሁለት መቶ ሰላሳ ወንድሞች እና እህቶች በዚህ የአጭር ጊዜ አፋጣኝ ጥሪ ምላሽ ሰጥተዋል። ሌሎችም በመለገስ ላይ ይገኛሉ። እናመሰግናለን።

  ተጨማሪ ያንብቡ


ዜና

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

 

በዝቋላ ገዳም እና አካባቢው ደን ላይ የተነሣውን እሳት ለማጥፋት ለሚደረገው ጥረት የግል ልገሳዎን ይስጡ በሚል ሐሳብ በማ/ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል፣ በሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ እና በማኅበረ በዓለ ወልድ አስተባባሪነት በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ ኦርቶዶክሳውያን አስቸኳይ የገንዘብ ማሰባሰብ ሒደት ላይ እንገኛለን። ዓላማው በአሁኑ ወቅት እሳቱን ለማጥፋት ከየአካባቢው በነቂስ ለወጣው ኢትዮጵያዊ ወገናችን ጉሮሮውን ማርጠቢያ ውኃ፣ ጉልበቱን መደገፊያ ዳቦ ማቅረቢያ እንዲሆን የታሰበ ነው። በባዶ እጁ፣ በቅጠል እና በአፈር ቋያ እሳት ለማጥፋት እየታገለ ላለው ወገን አለኝታነታችንን ለመግለጽ ነው። ስለዚህም በሚከተለው አድራሻ እየገባችሁ የግላችሁን ልገሳ መስጠት የምትችሉ መሆኑን በትህትና እናስታውቃለን።
http://zekuala.mahiberekidusan.org/
  


ዜና

መጋቢት 12/2004 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ

 


ከሥፍራው በደረሰን መረጃ መሠረት ምእመናን የመዳከም ሁኔታ የሚታይባቸው ሲሆን የአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ሌሎችም ምእመናን ደየመጡበት በመመለስ ላይ ናቸው፡፡ የፌደራል ፓሊስና የኦሮሚያ ፖሊስ ከቀሩት ምእመናን ጋር በመሆን የሚጨሰውን ፍም በማጥፋት ሥራ ላይ ተጠምደዋል፡፡ ወደ ዝቋላ ገዳም ከተለያዩ አቅጣጫዎች ምእመናን እየሔዱ ሲሆን በሥፍራው የሚገኙ ምእመናን አሁንም ተጨማሪ የሰው ኀይል እንዲደርስላቸው በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡

  


ዜና

በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል የሲያትል ቀጣና ማዕከል በዘንድሮው ዓመት በዕቅድ ከያዛቸው ሦስት ዐቢይ የስብከተ ወንጌል ጉባኤያት የመጀመርያውን ጉባኤ ቅዳሜ ኅዳር 23 2004 ዓ/ም (December 3, 2011) እና እሑድ ኅዳር 24 2004 ዓ/ም (December 4, 2011)  በተሳካ ሁኔታ አካሄደ።

  ተጨማሪ ያንብቡ


Page 6 of 13First   Previous   1  2  3  4  5  [6]  7  8  9  10  Next   Last   

Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement