ዜና
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከል የትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል አስተባባሪነት እና በኮሎምበስ፣ ኦሀዮ ደብረ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ አስተናጋጅነት በሰሜን አሜሪካና ካናዳ የተለያዩ ግዛቶች ውስጥ የሚያገለግሉ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ካህናት ሰባክያነ ወንጌልና መዘምራን የተሳተፉበት ዓርብ ጥቅምት ፲፯ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም (October 28, 2011) እና ቅዳሜ ጥቅምት ፲፰ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም (October 29, 2011) የተካሄደው የምክክር ጉባኤ የጋራ መግለጫ
ተጨማሪ ያንብቡ
|
ዜና
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከል የትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል አስተባባሪነት ከጥቅምት ፲፯ እስከ ፲፰ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. በኮሎምበስ፣ ኦሃዮ ደብረ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀው የመምህራንና ዘማርያን የምክክር ጉባኤ በታላቅ ድምቀት ተካሒዷል።
ተጨማሪ ያንብቡ
|
ዜና
|
ዜና
“የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው” በሚለው የቅዱስ ዳዊት መዝሙር መነሻነት ሐምሌ ፳፬ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም. “ዝክረ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ” በሚል ርዕስ ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ያረፉበት ፳፩ኛ ዓመት (ሐምሌ ፳፪) በልዩ መርሐ ግብር ታስቦ ውሏል። በማ/ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል የትምህርት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል የተዘጋጀው ይኸው የመታሰቢያ ዝግጅት ሁለት ሰዓት ተኩል የፈጀ የስልክ መርሐ ግብር ሲሆን በአሜሪካ ማዕከል ውስጥ ባሉ አስራ አንድ ቀጣና ማዕከላት የሚገኙ የማኅበሩ አባላትና ምዕመናን ተሳትፈውበታል:: በዝግጅቱ ላይ የብፁዕ አባታችን አጭር የሕይወት ታሪክ ከተነበበ በኋላ እና ብፁዕነታቸው ባቋቋሙት በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የካህናት ማሰልጠኛ በመግባት ከእግራቸው ሥር ቁጭ ብለው ወንጌልን በሕይወት ከተማሩት፣ የአባታችንን የሕይወት እና የአገልግሎት ፍሬዎች በዓይናቸው ከተመለከቱት እና መጽሐፎቻቸውን በጥልቀት ካነበቡት አባቶች እና ወንድሞች መካከል መልአከ ጽዮን ቀሲስ በላቸው ወርቁ፣ መልአከ ሰላም ቀሲስ ያሬድ ገ/መድኅን እና ዲ/ን ኤፍሬም እሸቴ ምስክርነታቸውን ጥልቅ በሆነ የፍቅር ስሜት ገልጸዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ
|
ዜና
በብፁእ አቡነ ፊሊጶስ የጠቅላይ ቤተ ከህነት ስራ አስኪያጅ እና የኢሊባቡርና የጋምቤላ ሊቀ ጳጳስ ለማተሚያ ቤቶች እና ለቤተ ክህነት የተለያዩ መምሪያዎች በግልባጭ በተላከ ደብዳቤ በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሃላፊ በአባ ሠረቅ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ለማተሚያ ቤቶች የተላከው የእግድ ደብዳቤ ተነሳ::
ይህን በመጫን ሙሉ ደብዳቤውን ይመልከቱ።
|
|