(አትላንታ፤ ጆርጂያ)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሥር መንፈሳዊ እና ማሕበራዊ አገልግሎቶችን የሚሰጠው የማ/ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል 13ኛ ጠቅላላ ዓመታዊ ጉባኤውን በአትላንታ/ ጆርጂያ በመካሔድ ላይ ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና በአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ የሚገኙ አባላት በተገኙበት በመካሔድ ላይ ያለው ይህ ጉባኤ በቅዳሜ ከሰዓት በፊት ግንቦት 20/2003 ዓ.ም ውሎው የማዕከሉን የ2003 ዓ.ም ዓመታዊ የተግባር ድርጊቶች ሪፖርት ከማዳመጡም በላይ በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ውይይት አድርጓል።