በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል የ15ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 17፣ 2005 /May 25, 2013/ በሚኒሶታ ንዑስ ማዕከል አዘጋጅነት ተጀመረ።
ጉባኤው በጸሎት የተጀመረ ሲሆን፣ ከመክፈቻ ጸሎቱ በኋላ የዲሲ ንዑስ ማዕከል ”እንዘ ይነብር ለአብ በየማኑ ወይረፍቅ ውስተ ህድኑ የማኑ ለአብ“ የሚል ያሬዳዊ ዜማ ካቀረቡ በኋላ መልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው “ናሁ ሰናይ ወናሁ አዳም” በሚል ርእስ ሰፊ ትምህርት ሰጥተዋል። መልአከ ሰላም በሰጡት ሰፊ ትምህርት በረከተ ነፍስ እና በረከተ ሥጋን ለማግኘት ከወንድሞች ጋራ በመከባበር በመፈቃቀር መኖር እንደሚገባ አስረድተዋል። ቃየል ከወንድሙ ጋር መኖር አለመቻሉ እንደጎዳው፣: ዛሬም ከወንድሞች ጋር ስንኖር መቻቻል፣ መበረታት እንደሚገባ፣ በፍፁም ትህትና መኖር እንዲሁም የወንድምን ወይንም የባልንጀራን ጥቅም ማስቀደም እንደሚገባ ሰፊ ትምህርት ሰጥተዋል።