ሰኔ 29 ቀን 2000 ዓም በብጹዕ አቡነ አብርሃም የሰሜን ምሥራቅ፣ የደቡብ ምሥራቅ እና የመካከለኛው አሜሪካ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት እና የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡
የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከትን ይበልጥ ለማጠናከር፣የራሱ ቢሮ እና የተሟሉ መሣርያዎች እንዲኖሩት ለማድረግ እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን ከእነዚህ እንቅስቃሴዎች አንዱ ሀገረ ስብከቱ ራሱን እና መላዋን ቤተ ክርስቲያን የሚያስተዋውቅባቸው ሚዲያዎች እንዲኖሩት ማድረግ ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ www.eotcdc.org በሚል ስያሜ የሀገረ ስብከቱ ይጆዊ ዌብ ሳይት የተከፈተ ሲሆን በመረጃዎች፣ በፎቶዎች፣ በትምህርቶች እና በመሳሰሉት ይበልጥ እየተጠናከረ ይሄዳል፡፡ በዚህ አገልግሎት ዕውቀቱ እና ፍላጎቱ ያላችሁም ትሳተፉ ዘንድ ሀገረ ስብከቱ ይጋብዛል፡፡
ለወደፊቱም የቴሌቭዥን እና የሬዲዮ ፕሮግራሞችን ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን እግዚአብሔር ፈቃዱ በሆነበት ጊዜ ለአገልግሎት ይበቃሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡
በዚህ ሥራ የተራዱንን ሁሉ በእግዚአብሔር ስም እናመሰግናለን፡፡
የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት
ዋሽንግተን ዲሲ