በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል የተዘጋጀ ዐውደ ርእይ በቦስተን በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰ/ት/ቤ/ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በሰሜን አሜሪካ ማዕከል የተዘጋጀውና መስከረም 24 ዓ.ም እና 25/ 2ዐዐዐ ዓ.ም (Oct 4- 5, 2008) ለ2 ቀናት በቦስተን ከተማ (St Paul A.M.E Church Christian Life Center) ለዕይታ የበቃው ዐውደ ርእይ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ፡፡ ፎቶዎችን ይመልከቱ
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ታሪካዊና መንፈሳዊ ቅርሶች የሚያስተዋውቀው ይኸው ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትናንት፣ ዛሬ፣ነገ›› በሚል ርዕስ የቀረበው ዐውደ ርእይ የቤተክርስቲያን አባቶች፣ በማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ ማዕከል ጸሐፊና ምእመናን በተገኙበት ቅዳሜ ከጠዋቱ 4፡ዐዐ (10:00am) በደመቀ ሁኔታ ከተከፈተ በኋላ አያሌ ኢትዮጵያውያንና የሌላ ሀገር ዜጎች ለመጎብኘት ዕድል አግኝተዋል፡፡ በዓይነቱ ልዩ የሆነውና ዘጠኝ የትዕይንት ክፍሎችን የያዘው ይህ ዝግጅት ተመልካቾችን ያስተማረ መሆኑን በአስተያየት መስጫ ላይ ገልጸዋል፡፡
Written By: host
Date Posted: 10/4/2008
Number of Views: 10816
Return