በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል የተዘጋጀ ዐውደ ርእይ በዴንቨር በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰ/ት/ቤ/ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በሰሜን አሜሪካ ማዕከል የተዘጋጀውና ጥቅምት 1 እና 2 2ዐዐዐ ዓ.ም (Oct 11- 12, 2008) ለ2 ቀናት በዴንቨር ከተማ (በዴንቨር ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን) ለዕይታ የበቃው ዐውደ ርእይ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ፡፡ ፎቶ
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ታሪካዊና መንፈሳዊ ቅርሶች የሚያስተዋውቀው ይኸው ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትናንት፣ ዛሬ፣ነገ›› በሚል ርዕስ የቀረበው ዐውደ ርእይ የቤተክርስቲያን አባቶችና ምእመናን በተገኙበት ቅዳሜ ከጠዋቱ 4፡ዐዐ (10:00am) በደመቀ ሁኔታ ከተከፈተ በኋላ አያሌ ኢትዮጵያውያንና የሌላ ሀገር ዜጎች ለመጎብኘት ዕድል አግኝተዋል፡፡ በዓይነቱ ልዩ የሆነውና ዘጠኝ የትዕይንት ክፍሎችን የያዘው ይህ ዝግጅት ተመልካቾችን ያስተማረ መሆኑን በአስተያየት መስጫ ላይ ገልጸዋል፡፡
ፎቶ ክፍል 1 ክፍል 2
Written By: host
Date Posted: 10/14/2008
Number of Views: 9491
Return