በአትላንታ ጆርጂያ የተዘጋጀ ዐውደ ርእይ በደመቀ ሁኔታ ተጠናቀቀ
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰ/ት/ቤ/ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በአሜሪካ ማዕከል አዘጋጅነት በአትላንታ ጆርጂያ ኅዳር 13 እና 14 ለሁለት ቀናት ክፍት ሆኖ የቆየው ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን፡- ትናንት - ዛሬ - ነገ›› ዐውደ ርእይ በደመቀ ሁኔታ ተጠናቀቀ፡፡ ፎቶዎችን እዚህ ይመልከቱ፡፡
በመላከ ፅዮን ቆሞስ አባ ዘሊባኖስ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአትላንታ ደብረ ፅዮን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ አስተዳዳሪ ጸሎት የቤተ ክርስቲያን አባቶች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ምእመናን በተገኙበት ቅዳሜ ኅዳር 03 ከጠዋቱ 4፡ዐዐ (10:00 am) በደመቀ ሁኔታ ከተከፈተ በኋላ አያሌ ኢትዮጵያውያንና የሌላ ሀገር ዜጎች ለመጎብኘት ዕድል አግኝተዋል፡፡ በዓይነቱ ልዩ የሆነውና አስራ አንድ የትዕይንት ክፍሎችን የያዘው ይህ ዝግጅት ተመልካቾችን ያስተማረ መሆኑን ተገልጸል፡፡
Written By: host
Date Posted: 11/27/2008
Number of Views: 8764
Return