የትምህርተ ወንጌል ጉባኤ በሲያትል
በሲያትል እና ኣካባቢው ከተሞች የሚኖሩ የ ኢ. ኦ. ተ. ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንን ያሳተፈ ታላቅ የትምህርተ ወንጌል ጉባኤ በሲያትል ከተማ ታህሳስ 16 እና 17 2003 ዓ.ም. ተደረገ:: በጉባኤው ላይ በሲያትል ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የተጋበዙ አባቶች ካህናት ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና ምዕመናን የተገኙ ሲሆን ፤ የኣጥቢያዎቹ ኣብያተ ክርስቲያናት የሰንበት ት/ ቤት መዘምራን መዝሙራትን ኣቅርበዋል።
በሁለት ቀኑ ጉባዔ የአጥቢያው ካህናት እና በተጋባዥነት በተገኙት መላከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል፤ እንዲሁም ሊቀ መዘምር ይልማ የተለያዩ ዝማሬዎችን በማቅረብ ከታዳሚዎቹ ጋር እግዚአብሄርን አመስግነዋል። በጉባኤው ላይ የማህበረ ቅዱሳን ኣገልግሎት በተለይም የ 10 ኣመቱ የስብከተ ወንጌል የኣገልግሎት እቅድ ለታዳሚዎች ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በቀጣይም ይህን እቅድ በተመለከተ ተከታታይ መርሃ ግብሮች እንደሚዘጋጅ ተገልጧል:: ጉባኤውን በማህበረ ቅዱሳን የኣሜሪካ ማዕከል የሲያትል ቀጠና ማዕከል ባካባቢው ከሚገኙ ኣጥቢያ ኣቢያተ ክርስቲያናት ጋር በመቀናጀት እንዳዘጋጀው ታውቋል ::
በእለቱ የተሰጡ ትምህርቶችና ፎቶዎች
በመጣችሁበት ኣትመለሱ - በቀሲስ ፋሲልባልንጀራዬ ማነው - በመላከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ መልካሙን ስራችሁን ኣይተው - በቀሲስ ዘሚካኤል ወዬልኝ - በመላከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ
መዝሙራት በ ሊቀ መዘምር ይልማ በኤፍራታ ምድርበመጨረሻው እንነሳለን ከሙታን
የመርሃግበሩን ፎቶዎች ይመልከቱ::
ረድኤተ እግዚኣብሄር ኣይለየን!
Written By: host
Date Posted: 1/1/2011
Number of Views: 8349
Return