View in English alphabet 
 | Monday, April 29, 2024 ..:: ዜናዎች ::.. Register  Login
  

የማ/ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል 13ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በመካሔድ ላይ ነው

(አትላንታ፤ ጆርጂያ)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሥር መንፈሳዊ እና ማሕበራዊ አገልግሎቶችን የሚሰጠው የማ/ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል 13ኛ ጠቅላላ ዓመታዊ ጉባኤውን በአትላንታ/ ጆርጂያ በመካሔድ ላይ ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና በአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ የሚገኙ አባላት በተገኙበት በመካሔድ ላይ ያለው ይህ ጉባኤ በቅዳሜ ከሰዓት በፊት ግንቦት 20/2003 ዓ.ም ውሎው የማዕከሉን የ2003 ዓ.ም ዓመታዊ የተግባር ድርጊቶች ሪፖርት ከማዳመጡም በላይ በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ውይይት አድርጓል።

ጉባኤው ከምሳ እረፍት በኋላ “የማዕከላችን የአገልግሎት ተግዳሮቶች እና የመፍትሔ አቅጣጫዎች”፣ “የማኅበሩ አባላት ማሕበራዊ ተሳትፎ” እንዲሁም “የቤተ ክርስቲያን አንድነት” በሚሉ ርእሶች ዙሪያ ትምህርቶች ተሰጥተው ውይይቶች ተደርጎባቸዋል። በመላው አሜሪካ ከሚገኙ ግዛቶች የተሰበሰቡት የማኅበሩ አባላት በዓመት አንድ ጊዜ የሚያደርጉት ይህ ጉባኤ ነገ እሑድም ቀጥሎ የሚውል ሲሆን በመርሐ ግብሩ መሠረት የ2004 ዓ.ምሕረትን ዕቅድ ገምግሞ ማስተካከያ በማድረግ ያጸድቃል። “የቤተ ክርስቲያናችንን ህልውና መጠበቅ የሁላችንም ኃላፊነት ነው” በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ ያለው ጉባኤው በተለያዩ መመምህራን ትምህርተ ወንጌል እና በመዘምራን ጣዕመ ዝማሬ የተዋበ ሆኖ በመቀጠል ላይ ይገኛል።

ተጨማሪ ፎቶ ለማየት ይህን ይጫኑ


Written By: admin
Date Posted: 5/28/2011
Number of Views: 4810

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement