View in English alphabet 
 | Thursday, May 2, 2024 ..:: ዜናዎች ::.. Register  Login
  

የመምህራንና ዘማርያን የምክክር ጉባኤ በኮሎምበስ፣ ኦሃዮ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከል የትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል አስተባባሪነት ከጥቅምት ፲፯ እስከ ፲፰ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. በኮሎምበስ፣ ኦሃዮ ደብረ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀው የመምህራንና ዘማርያን የምክክር ጉባኤ በታላቅ ድምቀት ተካሒዷል።

ከአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶችና ከካናዳ የተገኙ የደብር አስተዳዳሪዎች ካህናትና ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም መዘምራን ታድመዋል። መርሐ ግብሩ በደብሩ ቤተ መቅደስ ጸሎተ ኪዳን በማድረስ የተጀመረ ሲሆን ጉባኤውን የተመለከተ ምስባክ ተሰብኮ ወንጌል ተነብቧል።  በመቀጠልም በሁለቱ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ ጉዳዮችና ተዛማጅ አምስት ርዕሶች ላይ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተካሒዶባቸዋል። አብዛኛዎቹ ተሳታፊዎች አስተያየት እንደሰጡት ይህ ዓይነቱ የምክክር ጉባኤ በየጊዜው ቢዘጋጅ በቤተ ክርስቲያናችን ዙሪያ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመረዳት እንዲሁም ለችግሮች መፍትሔ ለመፈለግና መንፈሳዊ አገልግሎትን ለማጠናከር ይረዳል ብለዋል።

በዕለቱ ከአዲስ አበባ የማኅበሩ ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም ማኅበሩን በመወከል ለተሳታፊዎቹ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በአንድነትና በጋራ ማገልገል እንደሚገባና የስብከተ ወንጌሉን በማስፋፋት በትጋት እንዲሠሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Written By: admin
Date Posted: 10/29/2011
Number of Views: 5242

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement