View in English alphabet 
 | Sunday, May 5, 2024 ..:: ዜናዎች ::.. Register  Login
  

በዝቋላ የእሳት ማጥፋት እንቅስቃሴ ርዳታ

በዝቋላ እየተካሄደ ላለው የእሳት ማጥፋት እንቅስቃሴ ርዳታ በማድረግ ላይ ላላችሁ በሙሉ

Zekuala Fireማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል፣ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ እና ማኅበረ በዓለ ወልድ በአንድነት እያስተባበሩት ባሉት እና ዓላማው በአሁኑ ወቅት እሳቱን ለማጥፋት ከየአካባቢው በነቂስ ለወጣው ኢትዮጵያዊ ወገናችን ጉሮሮውን ማርጠቢያ ውኃ፣ ጉልበቱን መደገፊያ ዳቦ ማቅረቢያ እንዲሆን እንዲሁም በገዳሙ ጥሪታቸውን አሟጠው እንግዶቻቸው እሳት ተከላካዮችን  በማስተናገድ  ላሉት ገዳማውያን ርዳታ ማድረግ በሆነው ታላቅ እንቅስቃሴ እስካሁን በፔይፓል (http://zekuala.mahiberekidusan.org/) አካውንታችን (ይህ ጽሑፍ በተዘጋጀበት ወቅት) ሁለት መቶ ሰላሳ ወንድሞች እና እህቶች በዚህ የአጭር ጊዜ አፋጣኝ ጥሪ ምላሽ ሰጥተዋል። ሌሎችም በመለገስ ላይ ይገኛሉ። እናመሰግናለን።

ይሁን እንጂ በፔይፓል መክፈል ላልተመቻቸው ወገኖች እንዲሆን ተደጋጋሚ በቀረበው ጥሪ መሠረት Bank of America 003938182709 / Routing: 054001204 ብላችሁ የድርሻችሁን መወጣት የምትችሉ መሆኑን ወይም ቼክ መላክ ለምትፈልጉ ደግሞ በፖስታ አድራሻችን መላክ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ገንዘቡ እንደደረሰን ምላሽ የምንሰጣችሁ መሆኑን እናስታውቃለን።

እስካሁን ባለው ሁኔታ አፋጣኝ ምላሽ ለሰጣችሁ እና በፔይፓል አቅማችሁን ሁሉ ላደረጋችሁ ገንዘቡ በትክክል እንደደረሰን በኢ-ሜይል ደብዳቤ የላክንላችሁ መሆኑን እያስታወቅን ያልደረሳችሁ ካላችሁ በኢ-ሜይል ታሳስቡን ዘንድ ወይም በ 240 899 5215 ቴክስት ታደርጉልን ዘንድ እንጠይቃለን።

ለበለጠ መረጃ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ተጠቀሙ፦
• 240 899 5215 (ማኅበረ ቅዱሳን)
• 425 922 7182 (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት)
• 323 348 0820 (ማኅበረ በዓለ ወልድ)

በፔይፓል በኢንተርኔት ለምትከፍሉ፦
http://zekuala.mahiberekidusan.org/
http://www.eotc-nassu.org/

ወይም በቀጥታ በባንክ መክፈል ለምትፈልጉ Bank of America 003938182709 / Routing: 054001204

የፖስታ አድራሻ፦
8115 Fenton St. Suite 302,
Silver Spring MD 20910

በርቱ፤ ግፉበት። የምንችለውን በማገዝ ገዳሙን እና አባቶች መነኮሳትን እንታደግ!!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር


Written By: admin
Date Posted: 3/23/2012
Number of Views: 4222

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement