View in English alphabet 
 | Thursday, May 2, 2024 ..:: ዜናዎች ::.. Register  Login
  

ተዋሕዶ (Tewahedo) ለAndroid ተለቀቀ!

 

ተዋሕዶ (Tewahedo) የተሰኘ የiPhone አፕ በማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ አይቲ ክፍል ከዚሀ በፊት ተዘጋጅቶ ቀረቦ እንደነበር ይታወሳል::

ቃል እንደገባነው እነሆ የAndroid አቻውን አዘጋጅተን አቅርበርናል። አፑ /App/ ከሚሰጣቸው አግልግሎቶች በጥቂቱ:

1. የኢትዮጵያ እና የጎርጎሮሳዊያንን አቆጣጠር አጣምሮ የያዘ የዘመን መቁጠሪያ:: የፈለጉትን ዓመት የበዓላት እና አጽዋማት ቀናት በቀላሉ ማየት ያስችላል:: የየቀናቱን የቅዳሴ ምንባብ በመጽሐፈ ግጻዌ መሠረት ያሳያል::

2. የሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ስርጭቶችን ለአድማጭ እንዲመቹ በዓይነት ከፋፍሎ ያቀርባል:: በመቶዎች የሚቆጠሩ የቤተክርስቲያኒቱን ስርዓት የጠበቁ መዝሙራት፣ ስብከቶች፣ ትረካዎች እና ሌሎች የቤተክርስቲያንን ድምጾች በየትኛውም ጊዜና ቦታ (በመንገድ ላይ፣ ሥራዎትን እያከናወኑ፣ በእረፍትና በመዝናኛ ስፍራ) ሆነው ከስልክዎ ሊያዳምጡበት ይችላሉ!

3. በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናትን መረጃ ያሳያል:: ከፈልጉም ወደ ቤተ ክርስቲያናቱ የሚወስድ አቅጣጫ ያሉበትን ቦታ በመለየት  ይሰጥወታል!

4. የጸሎት መጻህፍት - ለጊዜው ውዳሴ ማርያም እና ውዳሴ አምላክ፣ በቀጣይ ሌሎች መጻህፍትን እንደምናስገባ መግለጽ እንወዳለን።

አፑን ጉግል ፕለይ (Google play) ውስጥ Tewahedo  ብለው ፈልገው የAndroid ስልክዎ ወይም ታብሌትዎ ላይ ይጫኑ::  iPhone/iPod/iPad ተጠቃሚዎች  አፕስቶር (App Store) በመግባት “Tewahedo” ብለው ቢፈልጉ አፑን በነጻ መጫን ይችላሉ። ሥራው የመጀመሪያ በመሆኑ ጉድለቶችን በመጠቆም ይርዱን።


ማስታወሻ: የiPhone
አፑ የቴሌቪዥን እና የጸሎት መጻህፍቱ በመሰራት ላይ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደሚካተት ለመግለጽ እንወዳለን።


 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ወስብሃት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል!

 


Written By: host
Date Posted: 2/25/2014
Number of Views: 6106

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement