View in English alphabet 
 | Friday, April 26, 2024 ..:: ዜናዎች ::.. Register  Login
  

የሕጻናትና ታዳጊ ወጣቶች የበጋ ትምህርት ምርቃት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ ማኅበረ ቅዱሳን በአሜርካ ማዕከል በዳላስ ንዑስ ማዕከል ለስምንት ሳምንታት ከሰኔ 6 2007 ዓም እስከ ሐምሌ 25 2007 ዓም ሲሰጥ የነበረውን የአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ሁለገብ ማዕከል የበጋ የሕጻናትና ታዳጊ ወጣቶች ትምህርት አጠናቆ ነሃሴ 2 2007 ዓም 50 ሕጻናት ተማሪዎችን አስመረቀ።

ተማሪዎቹን እንደ እድሜ ደረጃቸው በመክፈል በሦስት የተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ማለትም በቋንቋ ትምህርት ፤ በአብነት ትምህርት(ቅዳሴ ተሰጥዎ)እና በትምህርተ ሃይማኖት ዘርፍ ንዑስ ማዕከሉ በዳላስ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሲሰጥ ቆይቷል። 

በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው ለሕጻናቱ የምስክር ወረቀት የሰጡት የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃን ቀሲስ መስፍን ደምሴ ይህ ትምህርት ተጠናቅሮ እንዲቀጥልና በከተማው ያሉት አጥቢያዎች ተቀናጅተው በሕጻናትና ታዳጊዎች ላይ እንዲሰሩም አሳስበዋል። የደብሩ ካህናትና ወላጆች እንዲሁም በበጋ ሥልጠናው በማስተማር ያገዙት ምእመናንና የማኅበሩ አባላት በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል።

ንዑስ ማዕከሉ በአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ሁለገብ ማዕከል የበጋ ትምህርት መርሐ ገብርን በተሻለ ዝግጅት እንደሚቀጥል የገለጸ ሲሆን፣ በመደበኛው የትምህርት ዘመን ሊሰሩ የሚገባቸውን መርሐ-ግብሮች ለይቶ ለመተግበር በዝግጅት ላይ ይገኛል::


Written By: host
Date Posted: 8/10/2015
Number of Views: 2775

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement