View in English alphabet 
 | Thursday, April 25, 2024 ..:: ዜናዎች ::.. Register  Login
  

ማኅበረ ቅዱሳን በሰሜን አሜሪካ ቺካጎ ከተማ አዲስ መንፈሳዊ የቴሌቪዥን መርሐ ግብር ጀመረ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ማኅበረ ቅዱሳን በሰሜን አሜሪካ ቺካጎ ከተማ አዲስ መንፈሳዊ የቴሌቪዥን መርሐ ግብር ጀመረ
በኢቢኤስ(EBS) በመሰራጨት ላይ የሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን መርሐ ግብር በሰሜን አሜሪካ በሚገኙ 5 ከተሞች በቦስተን ፣ በካምብሪጅ ፣ በሲያትል ፣ በሚኒሶታና ሴንት ፖል ይተላለፍ የነበረውን ስርጭት በማሳደግ ስድስተኛውን ስርጭት በሰሜን አሜሪካ በመካከለኛው ምዕራብ በምትገኘው የችካጎ ከተማ ሐምሌ 25, 2007 ዓ.ም ስርጭት መጀመሩን የሰሜን አሜሪካ ማዕከል የሕትመትና ኤሌክትሮኒክስ ክፍል ገለፀ:: ስርጭቱ በችካጎና አካባቢው ለሚገኙ ምዕመናን የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማትና ለማየት በጎ ዕድል እንደሚፈጥር ሚዲያ ክፍሉ ገልጿል::

ዝግጅቱ በየሳምንቱ ቅዳሜና እሑድ በተለያየ ሰዓት ሶስት ጊዜ ይተላለፋል:: የማዕከሉ ሕትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል በያዘው ዕቅድ መሰረት ከቤተ ክርስቲያን መዋቅር ጋር በመቀናጀት ስርጭቱ በሁሉም የአሜሪካ ግዛቶች እንዲያድግና ተግባራዊ እንዲሆን የማዕከሉ አባላት አስተዋጽዖ ከፍተኛ መሆኑን ማዕከሉ ገልጿል:: ዝግጅቶችን ለማሰራጨት የየግዛቶቹ ባለስልጣናት ስቱዲዮና የሕብረተሰብ ቴሌቪዥን ሰዓት በነፃ በመስጠት ድጋፍ እያደረጉ እንደሆነ ከማዕከሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::
በአሁኑ ወቅት ማኀበረ ቅዱሳን በኢቢ ኤስ የሚያስተላልፈዉን የአንድ ሰዓት የቴሌቪዥን ስርጭት ከአንድ ሰዓት በላይ ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም በየሳምንቱ የሁለት ሰዓት የኢንተርኔት ቴሌቪዥን መርሐ ግብርና የአንድ ሰዓት የሬድዮ መርሐ ግብር እንደሚያስተላልፍ ይታወቃል::

ወስብሀት ለእግዚአብሔር::


Written By: host
Date Posted: 8/14/2015
Number of Views: 3056

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement