View in English alphabet 
 | Wednesday, April 24, 2024 ..:: ዜናዎች ::.. Register  Login
ዜና

  


ዜና


በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰሜን አሜሪካ አኅጉረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ 14ኛ ዓመት ጠቅላላ ጉባኤውን በአትላንታ መካነ ሕይወት አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ እና በደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ወአቡነ አረጋዊ አብያተ ክርስቲያናት ሰንበት ት/ቤቶች አዘጋጅነት ከነሐሴ 23 – 25/2006 ዓ/ም (August 29 – 31/2014) አካሄደ።።



በተለያዩ የሰሜን አሜሪካ ግዛቶች ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የመጡ የሰንበት ት/ቤት አባላት እና ተጋባዥ እንግዶች አርብ ነሐሴ 23 ረፋዱ ላይ አትላንታ የገቡ ሲሆን ፣ምሽት ላይ የጉባኤው መክፈቻ የጸሎት መርሐ ግብር በመካነ ሕይወት አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ ተከናውኗል። የደብሩ አስተዳዳሪ መላከ ሕይወት ቀሲስ እርገተ ቃል እና የአዘጋጆቹ ሰንበት ት/ቤቶች ተወካዮች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ካስተላለፉ በኋላ ለጉባኤው ተጋብዘው የተገኙት መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ የእለቱን ትምህርት አስተምረዋል። በመቀጠል የአንድነት ጉባኤው ሰብሳቢ ዲ/ን ኄኖክ ተዘራ ስለ ቀጣይ ሁለት ቀናት የጉባኤው መርሐ ግብር አጠቃላይ ገለጻ ሰጥተው የእለቱ መርሐ ግብር ተጠናቋል።   ተጨማሪ ያንብቡ



ዜና

በየዓመቱ በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የሚካሄደው በማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከል ጠቅላላ ጉባኤ በዘንድሮው ዓመትም ለአሥራ ስድስተኛ ጊዜ “አገልግሎትህን ፈጽም” በሚል መሪ ቃል በቺካጎ ኤሊኖይ ተካሄዷል ::
ከግንቦት ፳፬ - ፳፮ ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ለሦስት ቀናት የቆየው ይህ ጉባኤ ዓርብ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 5:00pm በቺካጎ ደብረ ኤዶም ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ካቴድራል በኒውዮርክና አካባቢው ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ዘካርያስ እና በካህናት አባቶች ጸሎተ ኪዳን በማድረስ የመክፈቻ መርሐግብሩ ተከናውኗል:: በማስከተልም ብፁዕነታቸው ቃለምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል:: በመቀጠልም ሕጽበተ እግር እና የእራት መስተንግዶ ከተከናወነ በኋላ  እንግዶች ወደየተዘጋጀላቸው ማረፊያ ተጉዘዋል።

  ተጨማሪ ያንብቡ


ዜና

  


ዜና

  


Page 2 of 13First   Previous   1  [2]  3  4  5  6  7  8  9  10  Next   Last   

Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement