View in English alphabet 
 | Friday, April 19, 2024 ..:: ዜናዎች ::.. Register  Login
ዜና

 

ተዋሕዶ (Tewahedo) የተሰኘ የiPhone አፕ በማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ አይቲ ክፍል ከዚሀ በፊት ተዘጋጅቶ ቀረቦ እንደነበር ይታወሳል::

ቃል እንደገባነው እነሆ የAndroid አቻውን አዘጋጅተን አቅርበርናል። አፑ /App/ ከሚሰጣቸው አግልግሎቶች በጥቂቱ:

1. የኢትዮጵያ እና የጎርጎሮሳዊያንን አቆጣጠር አጣምሮ የያዘ የዘመን መቁጠሪያ:: የፈለጉትን ዓመት የበዓላት እና አጽዋማት ቀናት በቀላሉ ማየት ያስችላል:: የየቀናቱን የቅዳሴ ምንባብ በመጽሐፈ ግጻዌ መሠረት ያሳያል::

2. የሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ስርጭቶችን ለአድማጭ እንዲመቹ በዓይነት ከፋፍሎ ያቀርባል:: በመቶዎች የሚቆጠሩ የቤተክርስቲያኒቱን ስርዓት የጠበቁ መዝሙራት፣ ስብከቶች፣ ትረካዎች እና ሌሎች የቤተክርስቲያንን ድምጾች በየትኛውም ጊዜና ቦታ (በመንገድ ላይ፣ ሥራዎትን እያከናወኑ፣ በእረፍትና በመዝናኛ ስፍራ) ሆነው ከስልክዎ ሊያዳምጡበት ይችላሉ!

  ተጨማሪ ያንብቡ


ዜና

“ወንጌል ለእርስዎና ለብዙዎች” በሚል ርዕስ የማኅበሩ የሲያትል ንዑስ ማዕከል የካቲት 1 እና 2 ቀን 2006 ዓ/ም ለሁለት ቀናት ባዘጋጀው የስብከተ ወንጌል መርሐግብር እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በስኬታማ ሁኔታ ተጠናቋል።

  ተጨማሪ ያንብቡ


ዜና

                 “የ፭ቱ ታቦታት የቀይ ምንጣፍ ጉዞ” በሲያትል ከተማ

በሰሜን ምዕራብ አሜሪካ ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሲያትል ከተማ የሚገኙት አምስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ማለትም የደብረ መድኃኒት ቅዱስ አማኑኤል ወአቡነ አረጋዊ ፤ የደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ፤ የደብረ ቁስቋም ቅድስት ማርያም ወደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ፤ የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል እና የደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት አብያተ ክርስቲያናት የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ጥምቀት ከሁለት ሺህ በላይ ምዕመናን በተገኙበት ጥር ፲  እና ፲፩ ቀን ፳፻፮ ዓ/ም (January 18/19 2014) በታላቅ ድምቀት አከበሩ::

  ተጨማሪ ያንብቡ


ዜና

Tewahedo የiPhone አፕ

ተዋሕዶ (Tewahedo) የተሰኘ የስልክ አፕ በማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ አይቲ ክፍል ተዘጋጅቶ ቀረበ:: ይህ የቤተክርስቲያን አገልግሎት ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን የቤተክርስቲያኒቷ ልጆች ሊያበረክቱ ለሚችሉት አገልግሎት ፋና ወጊ እንደሚሆን የታመንበት አፕ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች በጥቂቱ:-

  ተጨማሪ ያንብቡ


ዜና

የማዕከሉ የ1 ዓመት የሥራ አፈጻጸም ጠቅለል ያለ ሪፖርት በመልአከ ጽዮን ቀሲስ በላቸው ዳርጌ የቀረበ ሲሆን፣ በሪፖርቱ መግቢያ ላይ “በጊዜውም ያለጊዜውም ጽና” (2ኛ ጢሞ 4፣2)የሚለውን የሐዋርያውን ቃል በመጥቀስ ማኅበሩ በየጊዜው የሚያጋጥመውን ፈተናዎች በመቋቋም እንደ አቅሙ ከቤተ ክርስቲያን የተቀበለውን አደራ ለመወጣት የአቅሙን በመሞከር ላይ እንዳለ ካብራሩ በኋላ ማዕከሉ ካከናወናቸው ዐበይት ተግባራት መካከል የሚከተለቱ ተገልጸዋል።

  ተጨማሪ ያንብቡ


Page 3 of 13First   Previous   1  2  [3]  4  5  6  7  8  9  10  Next   Last   

Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement