View in English alphabet 
 | Thursday, April 25, 2024 ..:: ፕሮጀክቶች ::.. Register  Login
  

የ10 ዓመቱ የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮጀክት

 በትራክት መልክ የተዘጋጀውን መልእክት ለማግኘት እዚህ ይጫኑ

 

“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ ” ማቴ 28፥19-20

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !

ለተወደዳችሁ የክርስቶስ ቤተሰቦች !

ሠላመ እግዚአብሔር ከሁላችን  ጋር ይሁን !

ጉዳዩ : ለ10 ዓመቱ የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮጀክት ድጋፍ ስለመጠየቅ

ማኅበራችን ማኅበረ ቅዱሳን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠውን ሓላፊነት ለመወጣት በተለያዩ መንገዶች ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፤ እያደረገም ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን ሁሉንም የቤተክርስቲያን አባላት ባሳተፈ እና ሁሉም ምዕመናን የድርሻቸውን እንዲወጡ በማድረግ ችግሩን ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ፤ ስብከተ ወንጌል አገልግሎት ባልተስፋፋባቸው ገጠርና ጠረፋማ ቦታዎች፤ አኅዛብና መናፍቃን በበዛባቸው አካባቢዎች ወንጌልን ለማዳረስ የአሥር ዓመት የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ማስፋፊያ ኘሮግራም በመቅረጽ በግንቦት 19/2002 ዓ.ም. አገልግሎቱን ጀምሯል፡፡ 

ኘሮግራሙ በተመረጡ ሃያ/20/ ሀገረ ስብከቶች፣ መቶ/100/ ወረዳ ቤተክህነቶች እና ከአንድ ሺህ/1000/ በላይ አብያተ ክርስቲያናት ላይ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን፤ የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ በተያዘለት አሥር/10/ ዓመት ጊዜ ውስጥ በሃያው/20/ ሀገረ ስብከቶች፣ በአምስት/5/ የተለያዩ መንገዶች የስብከተ ወንጌል አገልግሎት መስጠት እና በሃያው/20/ ሀገር ስብከት እና በሥራቸው በሚገኙ ወረዳ ቤተክህነቶች የአቅም ማጐልበቻ ሥራ በመሥራት ስብከተ ወንጌልን በራሳቸው እንዲያስፋፉ ማስቻል ነው፡፡

መርሐ ግብሩ በተያዘለት እቅድ መሠረትና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የሚከተሉትን ተግባራት እያከናወነ ይገኛል::
1. የሕዝብ ጉባኤያትን ማዘጋጀት-
2. ሐዋርያዊ የስብከተ ወንጌል ጉዞ ማድረግ
3. በራሪ ትምህርታዊ ጽሑፎችና  የጥያቄና መልስ መድብል አዘጋጅቶ ማሰራጨት
4. በተለያዩ ቋንቋዎች የስብከተ ካሴት ማዘጋጀት፡
5. ያልተጠመቁትን ማጥመቅ
6. የቁዋሚ መምህራንና ሰባኪያን ቅጥር ማካሄድ
7. ለወረዳ ቤተክህነቶች/ አብያተ ክርስቲያናት/ካህናት የአቅም ማጐልበቻ ሥራ ( ሥልጠናዎችና ቁሳቁስ ማቴሪያል ማሟላት) መሥራት ይገኙባቸዋል::


የ 2003 ዓ/ም የሥራ ክንውን ሪፖርት
http://mahiberekidusan.org/Portals/0/sibket%20wongel%20project%202003%20report.pdf
http://mahiberekidusan.org/Portals/0/sibket%20wongel%20project%202003%20pictures.pdf

ከ2004 ዓ/ም እቅዶች መካከል
http://mahiberekidusan.org/Portals/0/sibket%20wongel%20project%20leaflet.pdf

• “የዕጣናችሁ ሸቶናል ፕሮጀክት” /የመንጃ ጎሳዎችን ለማስጠመቅ የተዘጋጀ ፕሮጀክት
• የ 10ወንበር መምህራን ቅጥር
     o በአፋር ሀገረ ስብከት ...
• ሐዋርያዊ ጉዞዎች በ15 ቦታዎች
• በተለያዩ ከተሞች የሕዝብ ጉባኤያት (በወላይታ፣ጅጅጋ ሀዲያና ሥልጢ ...)
• የካህናትን የኖሎትና የአስተዳደር ሥልጠና  በአሥር ቦታ 
    o ጂማ የካህናት ሥልጠና ፕሮጀክት ...
• በ10 ሀ/ስብከቶች የሰንበት ት/ቤቶች ስልጠና እንደዚሁም የተተኪ መምህራን እና የአስተዳደር ስልጠና  ይገኙበታል
   o የሲዳማ፤ጌዲኦ፤አማሮ እና ቡርጂ የሰ/ት/ቤቶች የተተኪ መምህራን ሥልጠና ...
ስለዚህ እንዚህና ሌሎችም የተዘጋጁና ስፖንሰር የሚፈልጉ ፕሮጀክቶችን በመያዝ የድርሻዎን መንፈሳዊ ኃላፊነት እንዲወጡ እናስታውሳለን::

ኢትዮጵያ: በማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮጀክት
አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አራት ኪሎ ቅርንጫፍ 013040- 242244-00
ስልክ: 251 0911 33 63 72 /251 0924 15 60 91  /  
2011swengel@gmail.com


በአሜሪካ ማዕከል ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል በኩል:  ለስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮጀክት በሚል ርዕስ  በገንዘብ መርዳት ለምትፈልጉ
Account number: 003938182699: Routing number: 052001633
ፕሮጀክቱን በአይነት ለመርዳት እንዲሁም ለበለጠ መረጃና ጥያቄ ይደውሉልን:: ወይም ይጻፉልን::
ይህንን ታላቅ መንፈሳዊ አገልግሎት በማገዝ የቅድስት ቤ/ክን ሐዋርያዊ አገልግሎት ይደግፉ :: ይምጡና አብረን እንሥራ !

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
በማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከል ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል
EOTCMKUSA_EDUCATION@YAHOO.COM   Tel. +1 240 899 5215 ወይም   +1 641-781-0370


Written By: host
Date Posted: 7/16/2012
Number of Views: 10446

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement