View in English alphabet 
 | Thursday, March 28, 2024 ..:: ፕሮጀክቶች ::.. Register  Login
  

ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው

“ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል።” መዝ 40፤1

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን!

ከሳዑዲ አረቢያ በአግባቡ ሳያስቡበትና ሳይዘጋጁ በድንገት ወደሀገራቸው በህይወት ተርፈው የተመለሱት ወገኖቻችን ባዶ እጃቸውን በመሆናቸው በአሁኑ ጊዜ ለዕለት ጉርስና ለአመት ልብስ የሚሆን በቂ ነገር የላቸውም። በመጽሐፍ እነደተገለጸው “እንጀራህን ለተራበ ትቆርስ ዘንድ፤ ስደተኞችን ድሆች ወደቤትህ ታገባ ዘንድ፤ የተራቆተውን ብታይ ታለብሰው ዘንድ” ብሎ እግዚአብሔር ያዛልና ኢሳ 58፤7 ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑን የምንገልጥበት አጋጣሚ አሁን ነው።

ማኅበራችን ማኅበረ ቅዱሳን ይህንን የወገኖቻችንን ጥሪ ተቀብሎ ከስደት ተመላሾችን ለዕለት ችግራቸው ከመድረስ ባሻገር በዘላቂነት ራሳቸውን ለማስቻል በጊዜያዊነት በቅዱሳት መካናት ማስተባበርያ ክፍል በኩል የበኩሉን እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል።  ይህንን በጎ አገልግሎት ተግባራዊ ለማድረግ እንዲያስችል ለዚህ አገልገሎት ብቻ የሚውል የልገሳ ድረገጽ http://LendHand.org/ በሚል የተዘጋጀ ስለሆነ አቅማችን የፈቀደውን ያህል ገቢ ማድረግ እንደምንችል እየገለጽን በዚህ መልኩ የሚሰበሰበው ገንዘብ ከስደት የተመለሱ ወገኖችን ለማቋቋም በማኅበሩ ለሚቀረጸው ፕሮጀክት የሚውል ሲሆን የስራው ክንውንም በማኅበሩ ደንብ መሰረት ቁጥጥርና ሪፖርት ይደረጋል።

በመጽሐፈ ምሳሌ 22፤9  “ሩኅሩህ የተባረከ ይሆናል፤ ከእንጀራው ለድሀ ሰጥቷልና” ተብሎ እንደተመለከተው እርስዎም በዚህ ታላቅ ሥራ የበኩልዎን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል


Written By: host
Date Posted: 1/3/2014
Number of Views: 4895

Return

  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement