View in English alphabet 
 | Monday, March 27, 2017 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
አማርኛ
ላክ   ተወው
ኅብረ ነገር

በስመ  አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ  አሐዱ አምላክ አሜን !

                           እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ አሸጋገራችሁ!

"የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ::"
ሕዝ 36፥26

እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ልጅ በእጆቹ አበጃጅቶ በአርአያው ከፈጠረው ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ የአባትነት ፍቅሩን ፣የፈጣሪነት ርኀራኄውን፣ የማያልቀውን ትዕግስቱን አላጓደለበትም:: ምክንያቱም እረኛችን ነውና በጎቹን፣ አምላካችን ነውና ፍጡሮቹን ፣ንጉሳችን ነውና ሕዝቦቹን አይተወንምና ነው።

ይሁንና የሰው ልጅ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ (በሮሜ 15፥20) ላይ እንደገለጸው "የማደርገውን አላውቅምና የምጠላውን ያን አደርጋለሁ፤ የምወደውን እርሱን አላደርገውም የማልወደውን ግን አደርጋለሁ። ፈቃድ አለኝና መልካሙን ግን ማድረግ የለኝም፤ የማልወደውን የማደርግ ከሆንኩ ግን ያን የማደርገው አሁን እኔ አይደለሁም በእኔ የሚኖር ኃጢያት ነው እንጂ። " በማለት የሰው ልጅ ዝንባሌ ከጽድቅ ይልቅ ኃጢያትን፣ ከሕይወት ይልቅ ሞትን፣ ከሰላም ይልቅ ሁከትን፣ ለአምላኩ ከመታዘዝ ይልቅ እንቢተኝነትን፣ እርስ በእርስ ከመፋቀር ይልቅ መጣላትን፣ ከአንድነት ይልቅ መለያየትን፣ ከመተሳሰብ ይልቅ ምቀኝነትን፣ ከቁም ነገር ይልቅ ቧልትን፣ ከመታመን ይልቅ አስመሳይነትን፣ ከእውነት ይልቅ ሐሰትን፣ ከሃይማኖተኛነት ይልቅ ከሃዲነትን እየመረጠ መላ ሕይወቱን እያናወጠ የሚጓዝ መሆኑን ያስገነዝበናል። ታዲያ የሰው ልጅ ማሰብ ሲገባው ከድካሙ ማስተዋል ሲኖርበት ከለገመ የድንጋይ ልብ አለው የሚባለው የዛን ጊዜ ነው።

  ተጨማሪ ያንብቡ


ኅብረ ነገር

በመጋቤ ጥበብ በእምነት በቀለ

ጳጉሜን ፭ ቀን ፳፻፭ ዓ/ም.

                                      የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዘመን የሚቆጠርበት ቀመር የሚቀመርበት ትምህርት ባሕረ ሐሳብ ይባላል። ባሕረ ሐሳብ ከሁለት የግእዝ ቃላት የተገኘ ነዉ። ባሕር ማለት በዘይቤ ሳይሆን በምስጢር ወይም በምሳሌው ዘመን ማለትን ያሰማል። “በመዳልው ደለወ ዓለመ ወበመስፈርት ሰፈራ ለባሕር” እንዲል። ባሕርን ሰፈራት ይላል ባሕር የሚሰፈር ሳይሆን ባሕርን ዘመን ለማለትና ዘመን በአዕዋዳት የሚታወድ፣ በቀመር የሚቀመር፣ የሚሰፈር መሆኑን ለማሳየት ነዉ። ሐሳብ ማለት ፍቺው ብዙ ቢሆንም እዚህ ላይ በአጭሩ ቁጥር ማለት ነው። “ኢትትሐሰብዎሙ ወርቆሙ ወብሩሮሙ ወለጽድቅከኒ አልቦቱ ሐሳብ - ለቸርነትህ ቁጥር ሥፍር የለውም” እንዲል አረጋዊ መንፈሳዊ፤ እንዲሁም ቅዱስ ዳዊት “ብፁዓን እለተኀድገ ሎሙ ኀጢአቶሙ ወእለኢሐሰበ ሎሙ ኩሎ ጌጋዮሙ - ኀጢአታቸዉ የተተወላቸው በደላቸው ያልተቆጠረባቸው ብፁዓን ናቸው” መዝ፤ 31፣1 ይላል። ስለዚህ ባሕረ ሐሳብ ማለት የዘመን አቆጣጠር ማለት ይሆናል። ሐሳበ ባሕርም ቢል ቁጥር ያለው ዘመን ማለት ነው።

  ተጨማሪ ያንብቡ


ኅብረ ነገር

  


ነገረ ቅዱሳንነገረ ቅዱሳን

የውዳሴ ማርያምና ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ በኮንፈረንስ ስልክ


“እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው::” ሉቃ 1፡48-49


ለተወደዳችሁ አባቶች፡ እናቶች ወንድሞችና እህቶች፡ በሙሉ :
የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን!

  ተጨማሪ ያንብቡ


Page 10 of 43First   Previous   5  6  7  8  9  [10]  11  12  13  14  Next   Last   

 የ10 ዓመት የስብከተ ወንጌል ማስፋፋፊያ ፕሮጀክት Minimize

ስለ ፕሮጀክቱ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እና ለመርዳት ይህንን ይጫኑ።


  
 ገዳማትን ይርዱ Minimize

 

Help Monastries


  
 ሶሻል ኔትወርኪንግ

Share |

  
 ግጻዌ


  
 የተላለፉ የቴሌቪዥን እና ሬዲዮ መርሃ ግብር ለመከታተል Minimize


  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement