View in English alphabet 
 | Thursday, January 23, 2025 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
አማርኛ




ላክ   ተወው
ኪነ ጥበብ

በዲ/ን አብነት አረጋ

ምድር እንኳ በመስከረም
ምንም እርሷ ብታረምም
በአበቦች ኅብረ ቀለም
አረንጓዴ ለብሳ ለምለም
  ተጨማሪ ያንብቡ


የቤተ ክርስቲያን ታሪክ

በሊቀኅሩያን ከፈለኝ ወልደጊዮርጊስ
በትራክት መልክ የተዘጋጀውን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ

እንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ዓውደ ዓመት፣ ዘመን መለወጫ፣ ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ /ከአራቱ ወንጌላውያን አንዱን/ እየተባለ ቢጠራም ሁሉም ያው አዲስ ዓመትን ከታሪክና ከትርጉም ጋር የሚገልጹ ስያሜዎች ሆነው እናገኛቸዋለን።
  ተጨማሪ ያንብቡ


ዜና

ቅዱስ ሲኖዶስ ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ ወሰነ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ነሐሴ 30/2004 ዓ.ም. ለመገናኛ ብዙኅን በሰጠው መግለጫ ከጳጉሜ 1 ቀን 2004 ዓ.ም. እስከ መስከረም 10/2005 ዓ.ም. ድረስ ምእመናን ለሁለት ሱባኤያት በመላዋ ኢትዮጵያና በውጭ ሀገር በሚገኙ አህጉረ ስብከቶች በሚገኙ ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት  ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ ወስኗል፡፡


ቅዱስ ሲኖዶስ ጸሎተ ምኅላውን ያወጀበት ምክንያት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በነበሩበት ዘመን በሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ  ሰፊ ሥራ የሠሩ አባት እንደነበሩ ጠቅሶ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ፤ ለሀገሪቱ ሰላምና አንድነት የሚበጅ ተተኪ አባት(ፓትርያርክ) እግዚአብሔር ባወቀ መርጦ እንዲያስቀምጥ ካህናትና ምእመናን  በጸሎተ ምኅላው እንዲሳተፉ አሳስቧል፡፡

ምንጭ፦ http://www.eotc-mkidusan.org/site/
  


ዜና

በእንዳለ ደምስስ

ስንክሳርንና ግብረ ሕማማትን እንዲሁም ሌሎችን መጻሕፍት ከግእዝ ወደ አማርኛ የተረጎሙት ታላቁ የመጻሕፍት ሊቅ ሊቀ መዘምራን ላእከ ማርያም ወልደ ኢየሱስ በተወለዱ በ90 ዓመታቸው ነሐሴ 1 ቀን 2004 ዓ.ም. በሞተ ስጋ ከዚህ ዓለም ተለዩ፡፡


ሊቀ መዘምራን ላእከ ማርያም ወልደ ኢየሱስ በአርሲ ክፍለ ሀገር በጢዮ ወረዳ ልዩ ስሙ ጨቢ አቦ በተባለ አካባቢ ከአባታቸው መምህር ወልደ ኢየሱስ ዘነበ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ወለተ ሩፋኤል ብስራት ነሐሴ 16 ቀን 1915 ዓ. ም. ተወለዱ፡፡

ከአባታቸው ከመምህር ወልደ ኢየሱስ ዘነበ ንባብ፤ ውዳሴ ማርያም ንባብና ዜማ ፤መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ዲቁና በመማር ለስልጣነ ክህነት ከበቁ በኋላ በአካባቢያቸው በሚገኘው ዱግዳ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በዲቁና ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

   ተጨማሪ ያንብቡ
  


የቤተ ክርስቲያን ታሪክ

በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ

ቤተ ክርስቲያን አንዲት፣ ቅድስት፣ ኩላዊትና ሐዋርያዊት መሆኗን ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያን ሁሉ ይቀበላሉ፤ በመሠረተ እምነታቸው ውስጥም አካትተው በጸሎትና በአስተምህሮ ይጠቀሙበታል፡፡የዚህ መሠረታዊ ምክንያቱ ደግሞ ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ይህ ትምህርት ቢኖርም ነገር ግን መልእክቱን በአግባቡ ካለመረዳት የተነሣ እነ አርዮስና መቅዶንዮስ በትውፊት ከሐዋርያት ጀምሮ የመጣውን የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜ መሠረት መቀበልን ቸል ብለው በራሳቸው መንገድ ሔደው ስለሳቱ በጉባኤ ኒቅያ በማያሻማ መንገድ ቤተ ክርስቲያን አንዲት፣ቅድስት፣ ሐዋርያዊት እና ኩላዊት መሆኗን አስቀመጡ፡፡

   ተጨማሪ ያንብቡ
  


Page 14 of 41First   Previous   9  10  11  12  13  [14]  15  16  17  18  Next   Last   

 የ10 ዓመት የስብከተ ወንጌል ማስፋፋፊያ ፕሮጀክት Minimize

ስለ ፕሮጀክቱ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እና ለመርዳት ይህንን ይጫኑ።


  
 ገዳማትን ይርዱ Minimize

 

Help Monastries


  
 ሶሻል ኔትወርኪንግ

Share |

  
 ግጻዌ


  
 የተላለፉ የቴሌቪዥን እና ሬዲዮ መርሃ ግብር ለመከታተል Minimize


  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement