View in English alphabet 
 | Saturday, April 21, 2018 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
አማርኛ
ላክ   ተወው
ትምህርተ ሃይማኖት

/ኢሳ. ፶፰፥፫/
በቀሲስ ስንታየሁ አባተ

በኢሳያስ ዘመን የነበሩ እስራኤላውያን የተናገሩት ቃል ነው። እስራኤላውያን የሚጾሟቸው ብዙ አጽዋማት ነበሯቸው። ለምሳሌ ያህልም ብናይ በሳምንት ሁለት ጊዜ በሳምንት ሁለት ቀን ይጾሙ እንደነበር በሉቃ. ፲፰፥፲፪ ላይ ያለው ቃል ያስረዳል። ማክሰኞና ሐሙስ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ወደ ደብረ ሲና የወጣበትና ከዚያ የወረደበት ዕለት ለማሰብ እስራኤላውያን በሳምንት ሁለት ቀኖች ይጾሙ ነበር። በነቢዩ በዘካርያስ ትንቢትም ላይ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን እንዲህ ብሎ አዝዟቸዋል «የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሀሤትም በዓላት ይሆናል ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ወደዱ።» ተብሎ ለእስራኤላውያን ከእግዚአብሔር ዘንድ በነብዩ በኩል በተነገራቸው መሠረት የተጠቀሱትን ይጾሙ ነበር። /ዘካ. ፰፥፲፰-፲፱/።

  ተጨማሪ ያንብቡ


ስብከተ ወንጌል

“You who held fast to the Lord your God are alive today, every one of you.” /Deut.  4:4/

Fasting in the Orthodox Church is abstaining from meat and all dairy products for a certain specified period, and for certain hours during a day.
There are seven fasting periods during the year. One of these fasting periods is known as the Great Lent.

  ተጨማሪ ያንብቡ


ስብከተ ወንጌል

ከብፁዕ አቡነ ሙሳ
(የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን የወጣቶች ጉዳይ ጳጳስ)

በለብ ለብ ክርስቲያንና በኦርቶዶሳዊ ክርስቲያን መካከል ትልቅ ልዩነት አለ ምክንያቱም ኦርቶዶክስ ማለት ርቱዕ በሃይማኖቱ ርቱዕ በምግባሩ ነውና።

ኦርቶዶክስ የሚለው ቃል የግሪክ ሲሆን ኦርቶ”  ማለት የቀና የተስተካከለ ርቱዕ ማለት ሲሆን፤ ዶክስማለት ደግሞ ሃይማኖት ማለት ነው። ኦርቶዶክስ ማለትም የቀና  የተስተካከለ ርቱዕ የሆነ ሃይማኖት ማለት ነው።

  ተጨማሪ ያንብቡ


ስብከተ ወንጌል

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሰው ከቅድስት ሥላሴ ረቂቅ ልደት ሊወለድ የቻለበትን፣ ወደ ክርስቶስ ቤተሰብነትና የክርስቲያን ማኅበር አንድነት ብሎም ወደ ዘላለም ሕይወት የሚተላለፍበትን በዓለ ጥምቀትን በየዓመቱ ጥር 11 ቀን የመታሰቢያ  በዓል አድርጋ ታከብረዋለች። ቤተ ክርስቲያናችን በሥዕላዊ መልክ ከምታከብራቸው በርካታ በዓላት መካከል በዓለ ጥምቀት አንዱ ነው። ሥዕላዊ መልክ ማለት በዓሉን በማስመልከት መዝሙር መዘመር፣ ምስጋና ማቅረብ፣ በበዓሉ ዕለት የተፈጸመውን ድርጊት በኅሊና ማሰብ ብቻ አይደለም። የበዓሉን ጥንታዊ ድርጊት በሚታይ ነገርና ሁኔታ መግለጥ ማለት ነው። ይህም የረቀቀውን አጉልቶ፣ የራቀውን አቅርቦ ለማሳየት ነው። የጥንተ ክርስትናውን መሠረት ሳትለቅ ከቀደምት አበው በተላለፈው እምነትና ሥርዓት የምትጓዘው ጥንታዊት፣ ብሔራዊትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችን ስለ ጥምቀት በዓል አከባበር የራሷ ትውፊት አላት። የብሉያትና ሐዲሳት መጻሕፍት በአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥራዝ እንደሚገኙ ሁሉ ሥርዓቱንም በዓሉንም አስተባብራ ይዛ የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት።

  ተጨማሪ ያንብቡ


ስብከተ ወንጌል

አንድ ሶርያዊ ክርስቲያን የሚከተለውን ደብዳቤ በ1983 .ም ጽፎ ነበር፡፡ ደብዳቤው እንዲህ ይነበባል፡-

«እስከ 1970 .(የተወለደው በ1943 .ም ነው) «በቤተ ክርስቲያን ትምህርት መሠረት ሥጋ ወደሙ እቀበል ነበር፣ አሥራት አወጣ ነበር፣ ገዳማትን ለመርዳት የተቋቋመ ማኅበር አባል ሆኜ ሌት ተቀን እሠራ ነበር፣ ሁል ጊዜ በመንፈሳዊ ሕይወቴ ውስጥ የመለወጥ ስሜት ነበረኝ፣ ለመማር፣ ለመጾምና ለመጸለይ የነበረኝን ትጋት አስታውሰዋለሁ፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ


Page 2 of 42First   Previous   1  [2]  3  4  5  6  7  8  9  10  Next   Last   

 የ10 ዓመት የስብከተ ወንጌል ማስፋፋፊያ ፕሮጀክት Minimize

ስለ ፕሮጀክቱ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እና ለመርዳት ይህንን ይጫኑ።


  
 ገዳማትን ይርዱ Minimize

 

Help Monastries


  
 ሶሻል ኔትወርኪንግ

Share |

  
 ግጻዌ


  
 የተላለፉ የቴሌቪዥን እና ሬዲዮ መርሃ ግብር ለመከታተል Minimize


  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement