View in English alphabet 
 | Thursday, October 3, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
አማርኛ




ላክ   ተወው
ኅብረ ነገር

በዐቢይ ጾም ውስጥ ካሉት ሳምንታት መካከል አራተኛው እሑድ መጻጉዕ ይባላል፡፡ መጻጉዕ የተባለበት ምክንያት በዚሁ ሰንበት ከዋዜማው ጀምሮ  የሚዘመረው ጾመ ድጓ  ድውያንን መፈወሱን ዕራንን ማብራቱን የሚያነሣ በመሆኑ ነው፡፡  «38 ዓመት የታመመውን መጻጉዕን ኢየሱስ አዳነው»  እንዲሁም ልጁ የታመመበት የመቶ አለቃው «ጌታዬ በቃልህ እዘዝ ልጄ ይድናል፡፡ በቤቴ ጣርያ ሥር አንተ ልትገባ አይገባህም» አለው:: «ጌታ በሚያልፍበት መንገድ አንድ ዕውር ፈውሰኝ» ብሎ ጮኸ የሚመሩት ሰዎች ዝም በል አሉት፡፡ ዕውሩ ግን እምቢ ብሎ «የዳዊት ልጅ ጌታ ይቅር በለኝ ዕርዳኝ» እያለ ጩኸቱን ቀጠለ፡፡
  ተጨማሪ ያንብቡ


ኅብረ ነገር

ከዐቢይ ጾም ሳምንታት ሦስተኛው ሰንበት ምኩራብ ተብሎ የተሰየመበት ምክንያት በዚሁ ዕለት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ሰላሙ ድረስ በዕለተ ሰንበት «ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ»
«ኢየሱስ በሰንበት ቀን ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ» እያለ ኢየሱስ በአይሁድ ምኩራብ ማስተማሩን እየጠቃቀሰና እያነሣሣ ስለሚዘምር ይህን ሰንበት ለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ እየገባ ለማስተማሩና በምኩራብ የሚሸጡ የሚለውጡ ነጋዴዎችን ለማስወጣቱ ቤተ መቅደሱን ለማስከበሩ መታሰቢያ ሆኖ ስለተሰጠ ነው፡፡ የዚህም በዓል ታሪክ ዝርዝር ሁኔታው በማቴዎስ ወንጌል ምዕ 21፡12-13 ተጠቅሷል፡፡
  ተጨማሪ ያንብቡ


ዜና

በጣና ሐይቅ ዙሪያ ከሚገኙት የዘጌ ገዳማት መካከል አንዱ የሆነው የመሐል ዘጌ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን  የካቲት 5 ቀን 2002 ዓ.ም ከቀኑ  12፡00 ሰዓት ጀምሮ የአደጋዉ ምክንያት ባልታወቀ እሳት ሙሉ በሙሉ ወድሟል። እሳቱን  ለማጥፋት በገዳሙ ዙሪያ የሚገኙ ምዕመናን፣ በአካባቢው የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል እና ከባሕር ዳር ከተማ በጀልባ ተሳፍረው የሄዱ ምዕመናን ጥረት ቢያደርጉም የእሳቱን ቃጠሎ ለመከላከል እና ለማጥፋት ሳይቻላቸው ቀርቷል።

  ተጨማሪ ያንብቡ


ዜና

(በሻምበል ጥላሁን):
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር ከአሶሳ ሀገረ ስብከት ጋር በመተባበር ባደረገው ሐዋርያዊ ጉዞ ከአራት ሺሕ በላይ ሰዎች የክርስትና ጥምቀት እንዲጠመቁ ማስቻሉን አስታወቀ፡፡ "የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር" ለስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በላከው መረጃ እንዳስታወቀው፤ ሐዋርያዊ ጉዞና ጥምቀቱ የተከናወነው ከታኅሣሥ 16 እስከ 25 ቀን 2002 ዓ. ም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ፣ ሥራ አስኪያጁ ሊቀ መዘምራን ሐረገወይን ጫኔ፣ የከማሽ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ መልአከሰላም ተገኝ ጋሻው በተገኙበት ነው፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ


ዜና

(በደረጀ ትዕዛዙ)

በማኅበረ ቅዱሳን የሕንፃ ግንባታ ጽ/ቤት አሳታሚነት ለኅትመት የበቃው «እመ ምኔት» የተሰኘው የደራሲ ፀሐይ መላኩ አዲስ ረጅም ልብወለድ መጽሐፍ ተመረቀ፡፡  ጥር 9 ቀን 2002 ዓ.ም አንጋፋና ወጣት ደራሲያን፣ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በሩስያ ባህል ማዕከል /ፑሽኪን አዳራሽ/ የተመረቀው መጽሐፍ፤ በገዳማውያን ሕይወትና በውስብስብ ወንጀል ታሪክ ላይ ያተኮረ ሲሆን ደራሲዋ የመጽሐፉን ሸያጭ ገቢ ለማኅበሩ ጽ/ቤት ሕንፃ ግንባታ እንዲውል አበርክተዋል፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን ምክትል ዋና ጸሐፊ እና የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴው ተወካይ ዲያቆን ዋስይሁን በላይ በዚሁ ምረቃ ወቅት ባስተላለፉት መልእክት፤ ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ሆኖ ለበርካታ ዓመታት መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ሲያበረክት መቆየቱን ጠቅሰው ይህንኑ አገልግሎት በተጠናከረ ሁኔታ ለማከናወን የጽ/ቤት ሕንፃ ግንባታ እያካሄደ ነው ብለዋል፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ


Page 32 of 41First   Previous   27  28  29  30  31  [32]  33  34  35  36  Next   Last   

 የ10 ዓመት የስብከተ ወንጌል ማስፋፋፊያ ፕሮጀክት Minimize

ስለ ፕሮጀክቱ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እና ለመርዳት ይህንን ይጫኑ።


  
 ገዳማትን ይርዱ Minimize

 

Help Monastries


  
 ሶሻል ኔትወርኪንግ

Share |

  
 ግጻዌ


  
 የተላለፉ የቴሌቪዥን እና ሬዲዮ መርሃ ግብር ለመከታተል Minimize


  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement