View in English alphabet 
 | Friday, September 20, 2024 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
አማርኛ




ላክ   ተወው
ፕሮጀክቶች

“ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል።” መዝ 40፤1

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን!

ከሳዑዲ አረቢያ በአግባቡ ሳያስቡበትና ሳይዘጋጁ በድንገት ወደሀገራቸው በህይወት ተርፈው የተመለሱት ወገኖቻችን ባዶ እጃቸውን በመሆናቸው በአሁኑ ጊዜ ለዕለት ጉርስና ለአመት ልብስ የሚሆን በቂ ነገር የላቸውም። በመጽሐፍ እነደተገለጸው “እንጀራህን ለተራበ ትቆርስ ዘንድ፤ ስደተኞችን ድሆች ወደቤትህ ታገባ ዘንድ፤ የተራቆተውን ብታይ ታለብሰው ዘንድ” ብሎ እግዚአብሔር ያዛልና ኢሳ 58፤7 ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑን የምንገልጥበት አጋጣሚ አሁን ነው።

  ተጨማሪ ያንብቡ


ነገረ ቅዱሳን

በዚችም ቀን (ሕዳር ፳፮) የተመሰገነና የከበረ ንጹሕም የሆነ የኢትዮጵያዊ አባታችን የሀብተ ማርያም የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። የዚህ ቅዱስ አባት የትውልድ አገሩ የራውዕይ በምትባል በስተምሥራቅ ባለች ሀገር ውስጥ ነው፤ በዚያም ስሙ ፍሬ ቡሩክ የሚባል አንድ ሰው ነበረ። ይህም ክቡራንና ታላላቅ ከሚባሉት ከዚች አገር ታላላቅ ሰዎች አንዱ ነው። እጅግም ሀብታም ነበር፤ ብዙ ንብረትም አለው በሕጋዊ ጋብቻም ስሟ ዮስቴና የምትባል ብላቴና ድንግልን አገባ። ይቺም የተመረጠች በበጎ ሥራ የተሸለመችና ያጌጠች ናት። ነገር ግን አስቀድመን በዚህ ዓለም ከሕግ ባሏ ጋር በንጹሕ ጋብቻ እግዚአብሔርን በመፍራት ምጽዋትን በመስጠት የዋህነትን ትሕትናን ፍቅርን ትዕግሥትን ገንዘብ አድርጋ በጾም በጸሎት ተወስና እንደኖረች እንነግራችኋለን።
  ተጨማሪ ያንብቡ


ፕሮጀክቶች

ስትመጣ . . . መጻሕፍቱንም ይልቁንም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ ፪ ጢሞ ፬፡፲፫

"የአኮቴት እና የስጦታ ሰሞን"

በዋናው ማእከል ማኀበረ ቅዱሳን የቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት ክፍሉን በዘመናዊ መልኩ ለማደራጀት እና አገልግሎቱን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ከአሜሪካውያን ታንክስ ጊቪንግ (የአኮቴት ቀን) ህዳር 16 እስከ ኢትዮጵያውያን የገና በአል ታህሳስ 29 የሚቆይ የስጦታ ማሰባሰቢያ ቀን ተዘጋጅቷል።

  ተጨማሪ ያንብቡ


ነገረ ቅዱሳን

ቅዱሳን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ከቤቱ ጀምሮ በጽላቱ በጠበሉ ይታሰባሉ። ቤቱ፥ ጽላቱ፥ ጠበሉ የእግዚአብሔር ሲሆን የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን፥የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ጽላት፥ የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ጠበል ይባላል። በዚህ ሁሉ ስማቸው እየተጠራ እንዲታሰቡ ያደረገ እግዚአብሔር ነው።
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
  


ነገረ ቅዱሳን

ጥቅምት ፲፬ ቀን የቁስጥንጥንያ ንጉሥ የቴዎዶስዮስ ልጅ የቅዱስ ገብረ ክርስቶስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ይህም ቴዎዶስዮስ እግዚአብሔርን የሚፈራ ነው ሚስቱም በጎ የምትሠራ እግዚአብሔርንም የምትፈራ ናት ስሟም መርኬዛ ነው። እነርሱም ልጅ ስለሌላቸው ያዝኑ ነበር:: ወደ ኢየሩሳሌምም ሒደው ስእለትን ተሳሉ ቸር መሐሪ ወደሆነ እግዚአብሔርም ለመኑ እርሱም ልመናቸውን ተቀብሎ ይህን ያማረ ልጅ ሰጣቸው ስሙንም አብደልመሲህ ብለው ሰየሙት ትርጓሜውም ገብረክርስቶስ ማለት ነው። የቤተክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ የሥጋዊንም ትምህርት አስተማሩት።
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ በስተቀኝ ያለውን ምልክት ይጫኑ 

Click the icon to the right to read about Saint Gabra Krestos
 
  


Page 7 of 41First   Previous   2  3  4  5  6  [7]  8  9  10  11  Next   Last   

 የ10 ዓመት የስብከተ ወንጌል ማስፋፋፊያ ፕሮጀክት Minimize

ስለ ፕሮጀክቱ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እና ለመርዳት ይህንን ይጫኑ።


  
 ገዳማትን ይርዱ Minimize

 

Help Monastries


  
 ሶሻል ኔትወርኪንግ

Share |

  
 ግጻዌ


  
 የተላለፉ የቴሌቪዥን እና ሬዲዮ መርሃ ግብር ለመከታተል Minimize


  
Copyright 2016 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement